የአሜሪካና የኢራን ውጥረት አየር መንገዶችን እያስተጓጎለ ነው! ✈️🚫
#ethiopia | "ኤር ፍራንስ፣ ሉፍታንዛ፣ ኤር ካናዳ እና ኬኤልኤም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ሰረዙ"
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመራ ይችላል በሚል ስጋት፤ ታዋቂ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ወደተለያዩ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የሚያደርጓቸውን በረራዎች መሰረዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የተሰረዙ በረራዎች እና መዳረሻዎች:
ኤር ፍራንስ (ፈረንሳይ)፣ ሉፍታንዛ (ጀርመን)፣ ኤር ካናዳ እና ኬኤልኤም (ኔዘርላንድስ) እንዲሁም ስዊስ ኤር እስከ እሁድ ድረስ ወደሚከተሉት ሀገራት አይበሩም፡-
🇮🇱 እስራኤል
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
ወደ ኢራን የሚደረጉ በረራዎች:
የጀርመኑ ሉፍታንዛ እስከ መጋቢት መጀመሪያ ድረስ እንዲሁም የኦስትሪያ አየር መንገድ እስከ የካቲት አጋማሽ ድረስ ወደ ኢራን የሚያደርጉትን በረራ መሰረዛቸው ታውቋል።
የሀገራቱ ምላሽ:
ምንም እንኳን አየር መንገዶቹ በረራ ቢሰርዙም፤ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴርም ሆነ የኢራን ሲቪል አቪየሽን "የአየር ክልላችን ክፍት ነው፤ የተለወጠ ነገር የለም" ሲሉ መረጃውን አስተባብለዋል።
ወደ እነዚህ ሀገራት የጉዞ እቅድ ያላችሁ መረጃዎችን እንድትከታተሉ ይመከራል።
ቢቢሲ
#aviationnews #middleeast #flightcancellation #iran #usa #lufthansa #airfrance #travelalert

6 months ago