ቤት መግዛት ማለት የመኖር ተስፋን መግዛት ነው። ይህ ተስፋ ደግሞ በውል ሰነድ ላይ በሚሰፍር ፊርማ ብቻ ሳይሆን፣ በተግባር በሚታይ ግንባታና በታማኝነት ሊረጋገጥ ይገባል። ያለበለዚያ ግን፣ ዜጎች በገዛ አገራቸው "የሕልም ነጋዴዎች" ሰለባ ሆነው ማለቃቸውን ይቀጥላሉ። የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ ይህንን ሰንሰለት ለመስበር የሚችልበት አቅም የሚለካው በወረቀት ላይ በሚሰፍሩ ቃላት ሳይሆን፣ በሚሰጡት ፈጣንና ፍትሐዊ ውሳኔዎች ብቻ ይሆናል።
ወደፊት በዘርፉ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ፣ እያንዳንዱ አልሚ በዓመት ስንት ቤት አስረከበ? ስንት የሕግ ክርክር አለበት? የሚለው ዳታ ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት። መረጃ ኃይል ነው፤ ገዢዎች መረጃ ሲኖራቸው በአታላዮች የመያዝ ዕድላቸው ይቀንሳል። ይህ ስምምነት ወደ መረጃ ግልጽነት (Transparency) የሚወስድ ድልድይ መሆን አለበት።

7 months ago