Logo
Getu Temesgen
🎨 "ትስስር" - ከቨርጂኒያ ወደ አዲስ አበባ

የ3 ትውልድ ቀለማት በ"አዲስ የሲኒማ ማዕከል"
#ethiopia | ​በአንጋፋው ሰዓሊ ልዑል ሰገድ ረታ አስተባባሪነት፤ ባለፈው ነሐሴ ወር በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ቀርቦ አድናቆትን ያገኘው "ትስስር" (Connection) የተሰኘው የሥነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን አሁን በቤታችን አዲስ አበባ ለእይታ በቅቷል!

​የሦስት ትውልድ ውህደት!
ይህ አውደ ራዕይ የተለያዩ የአሳሳል ጥበቦችን እና የዘመናት ተሞክሮዎችን ያቀናጁ 6 ምርጥ ኢትዮጵያውያን ሰዓሊያንን ስራዎች በአንድነት ይዞ ቀርቧል፦

​አንጋፋው ሰዓሊ ልዑል ሰገድ ረታ
​ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ
​ሰዓሊ ስዩም አያሌው
​ሰዓሊ ዑስማን ሀሰን
​ሰዓሊ ታምራት ስልጣን
​ሰዓሊ ያሬድ ኦሌቪሊ

​📍 ቦታ: ሰንጋተራ በሚገኘው አዲሱ የሲኒማ ማዕከል ጋለሪ
📅 ቀን: ከጥር 7 እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ለአንድ ወር)
​የቀለማትን ውህደት እና የጥበብን ጥልቀት ለማድነቅ እርሶም ተጋብዘዋል! በስራ ሰዓት ጎራ ይበሉ።

​#tisisir #artexhibition #ethiopianart #addiscinemacenter #lulsegedretta #fineart #addisababa

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.