Logo
SeledaPost
በአሜሪካ 1.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት እጅግ ግዙፍ የሊቲየም ክምችት ተገኘ

በአሜሪካ ኦሪገን እና ኔቫዳ ግዛቶች ድንበር ላይ በሚገኝና ከ16 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በፈነዳ “ሱፐርቮልካኖ” (Supervolcano) ስር፣ በዓለም ላይ በግዝፈቱ ቀዳሚ ሊሆን የሚችል የሊቲየም ማዕድን ክምችት መገኘቱን ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

“ማክደርሚት ካልዴራ” ተብሎ በሚጠራው በዚህ ጥንታዊ የእሳተ ገሞራ ተፋሰስ ውስጥ የተገኘው ማዕድን፣ ከ20 እስከ 40 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚመዝን ሊቲየም ሊይዝ እንደሚችል ተገምቷል።

ይህም በገንዘብ ሲሰላ እስከ 1.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ አሜሪካ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪና ለቴክኖሎጂ ምርቶች የሚያስፈልጋትን የሊቲየም አቅርቦት በአገር ውስጥ ለመተካት ትልቅ ዕድል የሚፈጥርላት ነው።

ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ በፈሳሽ መልክ የነበረው ሊቲየም በእሳተ ገሞራው አመድና በጭቃማ ድንጋዮች (Claystone) ውስጥ ተከማችቶ ለሚሊዮን ዓመታት ቆይቷል።

 “ሃይቴክ ሚነራልስ” የተባለው ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የአሰሳና የቁፋሮ ሥራዎችን የጀመረ ቢሆንም፣ የማዕድን ቁፋሮው በአካባቢው ሥነ-ምህዳር፣ በውኃ አቅርቦትና በሀገር በቀል ማህበረሰቦች ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እያጋጠመው ይገኛል።

ሊቲየም ለታዳሽ ኃይልና ለዘመናዊ መከላከያ መሣሪያዎች ቁልፍ ግብዓት በመሆኑ፣ ግኝቱ በዓለም አቀፍ የኃይልና የጂኦፖለቲካ መድረክ ላይ የአሜሪካን ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳድግ እንደሚችል ተነግሯል።

ሆኖም ማዕድኑን ከጭቃማ ድንጋይ ውስጥ ለይቶ ለማውጣት የሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ውስብስብነትና የአካባቢ ጥበቃ ሥጋቶች ለፕሮጀክቱ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ ተመልክቷል።

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.