Logo
Getu Temesgen
🎉 ጭጋጉ ተገፏል፤ ብራው ወጥቷል! እንኳን ለ"ቢስት ባር" በዓል አደረሳችሁ! 🎉
#ethiopia | ​ታላቁ የቤንች ብሔር የማንነት መገለጫ የሆነው የ “ቢስት ባር” በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኛለሁ!

​🌼 ቢስት ባር ምንድን ነው?

ይህ በዓል ተፈጥሮ አዲስ ልብስ ለብሳ፣ ጭጋጉ ተገፎና ብራው ወጥቶ የሚከበር የድልና የምስጋና በዓል ነው። የክረምቱ ዳመና በብሩህ ፀሐይ ሲተካ፤ የቤንች ምድር በአረንጓዴ ምንጣፍ አጊጣ አዲሱን ዘመን ትቀበላለች።

​በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ ጀግናውና ኩሩው የቤንች ሕዝብ የቤንችቴት፣ የሜሪቴት እና የሼይቴት አብራክ ክፋዮች ባህላቸውን አንግበው፣ በማንነታቸውን ደምቀው ያከብሩታል።

​🌾 የላብና የጥረት በዓል

ቢስት ባር ዝም ብሎ በዓል አይደለም፤ የጥረት ውጤት፣ የላብ መፍሰስና የአዝመራ መሳካት በዓል ነው።

​"ከድካሙና ከላቡ ውጭ ያልዘራውንና የጥረት ወጤቱን ያልሆነውን የሚበላ በቤንቾች ዘንድ እንደተረገመ ይቆጠራል።"
​ስለዚህ አርሶ አደሩ ድካሙን በአንድነት የሚያጣጥምበት፣ እህሉን ሰብስቦ “የበኩሩን” ለፈጣሪና ለታላላቆች የሚያቀርብበት የምስጋና በዓል ነው።

​👴🏽 የትውልድ ቅብብሎሽ

በማንነቱ እና በክብሩ የማይደራደረው የቤንች ሕዝብ፣ ይህንን በዓል ሲያከብር የታላላቆችን ምርቃት በመቀበል ነው።

የወጣቱ ጉልበት ከሽማግሌዎች ጥበብ ጋር የሚገናኝበት፣ ታሪክ ለትውልድ የሚተላለፍበት፣ የሰላም እና የአንድነት ቃል ኪዳን የሚታደስበት ልዩ በዓልም ነው።

​አዲሱ ዓመት "ቢስት ባር" ለሁላችንም የደስታና የሰላም ይሁንልን!

​✍️ ጌታቸው ባይባ (ሚዛን አማን)

​#bistbar #benchpeople #newyear #harvestfestival #ethiopianculture #mizanaman #gratitude

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.