አንጋፋ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች የሚሳተፉበት ልዩ የገና ጨዋታ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር፤ የዘንድሮን የገና በዓል አስመልክቶ ልዩ የገና ጨዋታ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
ይህ ልዩ የበዓል መዳረሻ ኹነት፤ የፊታችን እሁድ ታኅሣሥ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በድምቀት ይከናወናል።
በዝግጅቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት የሥራ አመራሮች፣ እውቅናን ያተረፉ አንጋፋ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች በጨዋታው ላይ በይፋ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
የገና ጨዋታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ቀጥተኛ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቁርኝት ያለው ነው። ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ዜናውን የሰሙ እረኞች በደስታ ብዛት፣ በእጃቸው በያዙት በትር (ዱላ) እና ሩር እንደተጫወቱ የሃይማኖት ሊቃውንት ያስረዳሉ።
ይህ መርሐ ግብርም ታኅሣሥ 29 ለሚከበረው በዓል እንደ መዳረሻ እና ይህንን ቱባ ባህል ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

7 months ago