Logo
Getu Temesgen
"ቡድኖቹ ለሶማሊላንድ እውቅና መንገድ ከፍተዋል"ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
#ethiopia | የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፣ አሸባሪ ቡድኖቹ አልሸባብና ISIL የሶማሊያን ሕዝብ ደህንነትና ኑሮ በማውደም ረገድ ቀዳሚ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ለአልጀዚራ በሰጡት ልዩ ቃለ
ምልልስ እንዳመለከቱት፤ እነዚህ አሸባሪ ቡድኖች በሶማሊያ ውስጥ የሚፈጥሩት አለመረጋጋትና ውድመት ሀገሪቱን ለውጭ ጣልቃ ገብነትና ለተለያዩ የፖለቲካ ቀውሶች አጋልጧታል::

ፕሬዝዳንት ስለ ሰሞኑን ሁኔታ ምን አሉ 🔎

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በንግግራቸው ውስጥ ትኩረት የሚስብ ወቀሳ ሰንዝረዋል። የአሸባሪ ቡድኖቹ እንቅስቃሴ ሀገሪቱን በማዳከም "እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጥ በር ከፍተዋል" ሲሉ ከሰዋል። ይህም ቡድኖቹ ከሚያደርሱት ቀጥተኛ የጥፋት እርምጃ ባሻገር፣ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነትና አንድነት ስጋት መሆናቸውን አመልክተዋል።

ሶማሊያ አልሸባብን ከሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ ቡድኖቹ በሀገሪቱ ጂኦ-ፖለቲካ ላይ እያሳደሩት ያለውን ተጽዕኖ በግልጽ ያሳየ መሆኑ ተመልክቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#somalia #hassansheikhmohamud #alshabaab #isil #somaliland #regionalsecurity #aljazeera #hornofafrica

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.