በኢትዮጵያ የምግብ ፍላጎት መጨመር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
📌ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችላትን የ10 ዓመት የጥምር ደን እርሻ (አግሮፎርስትሪ) ስትራቴጂ ይፋ አደረገች
#ethiopia | የግብርና ሚኒስቴር የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን ብሔራዊ የአግሮፎርስትሪ (ጥምር ደን እርሻ) ስትራቴጂ ይፋ አደረገ።
ይህ ከ2026 እስከ 2035 እ.ኤ.አ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የሚያገለግለው ስትራቴጂ፣ ሚኒስቴሩ ከበርካታ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ተገልጿል።
የስትራቴጂው አስፈላጊነት፦🖊
በግብርና ሚኒስቴር የሥራ አመራር ተወካይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ጫላ ሆርዶፋ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የአፈር መሸርሸር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እና እየጨመረ የመጣው የምግብ ፍላጎት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
ይህ ስትራቴጂም፦🔎
* የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል፣
* የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን በሳይንሳዊ መንገድ ለመምራት፣
* የተቀናጀ የግብርና ስራን ለማስፋፋት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በረሃማነትን የመከላከል ፋይዳ፦
በስትራቴጂው ዝግጅት ላይ የተሳተፈው የዓለም ጥምር ደን እርሻ ምርምር ማዕከል (ICRAF) ኮሚኒኬሽን ኦፊሰር አቶ እዮብ ጌታሁን ለብስራት ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል እርጥበት አዘል የነበሩ አካባቢዎች ወደ ደረቅ መሬትነት እየተቀየሩና በረሃማነት እየተስፋፋ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይፋ የሆነው ስትራቴጂ አርሶ አደሮች ዛፎችን ከሰብልና ከእንስሳት እርባታ ጋር አጣምረው እንዲያለሙ (Agroforestry System) በማድረግ፣ የመሬትን ምርታማነት እንዲጨምሩና የአካባቢን አየር ንብረት እንዲያስተካክሉ ይረዳል ተብሏል።
ስትራቴጂው ተግባራዊ መደረጉ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሯን በዘላቂነት ለማስቀጠል ለምታደርገው ጥረት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #agriculture #agroforestry #climatechange #greenlegacy #foodsecurity #sustainablefarming #news

9 months ago