ሳውዲ አረቢያ ኤምሬትስን የብሔራዊ ደህንነቴን አደጋ ላይ ጥላለች ስትል ከሰሰች፤ ከየመን እንድትወጣ አጭር ጊዜ ሰጥታለች
በሳውዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የየመን ሪፐብሊክ ያቀረበችውን “ሙሉ በሙሉ የመውጣት” ጥያቄ በአስቸኳይ እንድትቀበል ጠይቃለች።
የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በየመን ውስጥ “እጅግ አደገኛ እርምጃዎችን” እየወሰደች መሆኑንና ይህም በቀጥታ የሳውዲን ብሔራዊ ደህንነት የሚፈታተን መሆኑን ነው ብሏል ።
የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ “ወንድም” በተባለችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ድርጊት ጥልቅ ቅሬታ መሰማቱን ገልጿል።
ኤምሬትስ የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት ኃይሎች በሳውዲ ደቡባዊ ድንበር ላይ፣ በተለይም በሀድራማውት እና በአል-መሀራ ግዛቶች ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሂዱ ጫና እያደረገች መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
“ቀይ መስመር” እና በመረጋጋት ላይ የተጋረጠ ስጋት
መግለጫው እንደሚለው፣ እነዚህ እርምጃዎች በየመን ሕጋዊነትን ለመመለስ የተመሰረተው የሕብረ ብሔር ጥምረት ከተመሰረተባቸው መርሆዎች ጋር የሚጋጩ ናቸው።
ሳውዲ እንደለገፀችው ፣ የጦር መሣሪያዎችንና የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን የጫኑ መርከቦች ከአል-ፉጃይራ ወደ አል-ሙካላ ወደብ ያለ ጥምር ጦር ዕዝ ይፋዊ ፈቃድ መንቀሳቀሳቸው የስምምነቱ ቀጥተኛ ጥሰት ነው።
የሪያድ ማስጠንቀቂያ እንዲህ ይላል፦ “መንግሥቱ በብሔራዊ ደህንነቱ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውንም ስጋት እንደ ‘ቀይ መስመር’ ይቆጥረዋል። ሳውዲ አረቢያ እንዲህ ያለውን ስጋት ለመጋፈጥና ለማክሸፍ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ ለመውሰድ ወደኋላ አትልም።”
ሁኔታው እጅግ የከረረው ሳውዲ አረቢያ፣ ኤምሬትስ የየመን ሪፐብሊክን ጥያቄ ተቀብላ በአስቸኳይ እንድትወጣ ባቀረበችው ጥያቄ ነው።
“የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የየመን ሪፐብሊክ ያቀረበችውን ጥያቄ በመቀበል፣ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሁሉንም ኃይሎቿን ከየመን ግዛት እንድታስወጣ እና በየመን ውስጥ ለማንኛውም ወገን የምታደርገውን ወታደራዊም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ እንድታቆም መንግሥቱ ያሳስባል” ሲል ሰነዱ ይገልጻል።
ለየመን አንድነት የሚሰጥ ድጋፍ
ምንም እንኳን ውጥረቱ ቢኖርም፣ ሪያድ ለፕሬዚዳንታዊ የአመራር ምክር ቤት ሰብሳቢ እና ለየመን መንግሥት ያላትን ሙሉ ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጣለች። ለየመን ደህንነት፣ መረጋጋት እና ሉዓላዊነት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልጻለች።
በተጨማሪም ሳውዲ አረቢያ “የደቡብ ጥያቄ” ታሪካዊና ማህበራዊ መሰረት ያለው ፍትሃዊ ጥያቄ መሆኑን ብታምንም፣ መፍትሄው ሊገኝ የሚችለው በውጭ አካላት በሚገፋፋ ወታደራዊ ግጭት ሳይሆን፣ ሁሉን አቀፍ በሆነ ፖለቲካዊ ውይይት ብቻ መሆኑን አጥብቃ አሳስባለች።
መግለጫው የተጠናቀቀው በባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት (GCC) አባል ሀገራት መካከል ጥበብና የወንድማማችነት መርሆዎች እንዲሰፍኑ ጥሪ በማቅረብ ነው። ኤምሬትስ በእነዚህ እርምጃዎች ምክንያት ክፉኛ የተናወጠውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ትወስዳለች የሚል ተስፋም ተገልጿል።

5 months ago