" ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " - የሟች ወላጅ
አቶ ባና ቦና ይባላሉ ነዋሪነታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ቡንቲ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ባና ቦና ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ልጃቸው አብነት ባና ቦና ከጓደኛዉ ጋር ሆነዉ ሞተር ሳይክል ለማስጠገን ወደ አርባምንጭ ከተማ እንደሄዱ ገልጸዋል።
ሞተር ሳይክላቸውን አስጠግነዉ ሲመለሱ ግን በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበል በኖ ቀበሌ ' ሆልቴ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሲደርሱ የፖሊስ አባልን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሚኒባስ አስቁመዉ ተሳፋሪዎችን እያወርዱ ያገኟቸዋል።
እነሱንም ሞተር እንዲያቆሙ ሲጠይቁ ከቆሙ በኋላ ገንዘብና ስልኮቻቸዉን ከዘረፉ በኋላ ጥቃት ፈፅመዉባቸዉ ልጃቸዉ መገደሉን አቶ ባና ቦና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ሟች አብነት ባና ገና የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን ታናናሹቹ እንዲማሩ ትምህርቱን አቋርጦ በእርጅና ዉስጥ ያሉ አባትና እናቱን በማገዝና በመጦር ላይ የነበረ ወጣት እንደሆነ ወላጅ አባቱ ተናግረዋል።
" ልጄ መገደሉን የሰማሁት ስንፈልገዉ አድረን ጥቃቱ በተፈፀመ ማግስት በአከባቢው በሚገኝ አንድ የበቆሎ ማሳ ዉስጥ በዘግናኝ ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቶ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ተደዉሎልን ነዉ " ብለዋል።
ወላጅ አባት " ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " ሲሉ በታላቅ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉ ተናግረዋል።
" ልጃችን በምን ጥፋቱ ገና በለጋ ዕድሜው እንደተገደለ የምናዉቀዉ ነገር የለም " የሚሉት አባት ስለተፈጠረዉ ሁኔታ ከሞት አፋፍ የተረፈዉ ጓደኛዉና አብሮ አደጉ ካሳሁን መንገድ ላይ ከወደቀበት ሹፌሮች አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ካደረሱት በኋላ ለቤተሰቡ መደወሉን ሰምተን የጋርዱላ ዞን ፖሊስን ደጋግመን ጠይቀናል ብለዋል።
" የዞኑ ፖሊስ ተጎድቶ አርባምንጭ ከገባዉ ልጅ ውጪ የተጎዳም ሆነ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ሲገልፁ ቆይተዉ በማግስቱ አስክሬኑ ጋርዱላ ሆስፒታል መሆኑን በመግለፅ ወደ ጉማይዴ ወሰን አከባቢ በሚትገኝ ሀይቤና ቀበሌ በፖሊስ አጅበዉ በማምጣት ከማስረከብ በስተቀር 'ስለ ገዳዮቹም ሆነ አሟሟቱ የዞኑ ፖሊስ በግልፅ የነገረን ነገር የለም' " ብለዋል።
ከጥቃቱ የተረፈዉ ካሳሁን ምን አለ?
" በዕለቱ አርባምንጭ ሞተር አሰርተን በሰላም ወደ ቤታችን እየተመለስን ነበር።
ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበልበኖ ኦልቴ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ስንደርስ አንድ አነስተኛ ሚኒባስ ቆሞ ተሳፋሪዎች ሲወርዱ እኛንም ሞተር እንድናስቆም ጠየቁን።
የደንብ ልብስ የለበሰ ፖሊስ በቦታዉ ስለነበር ምንም ጥርጣሬ ዉስጥ ሳንገባ በቆምንበት ነበር የያዝነዉን።
ገንዘብና የእጅ ስልካችንን በግድ ከወሰዱብን በኋላ 'ሄደዉ ለጉማይዴዎች ያቃጥራሉ፤ማንነታችንን ስላዩ እንግደላቸዉ' መባባል ሲጀምሩ እኔም በፊናዬ ጓደኛዬም በፊናው በእግር መሸሽ ጀመርን ለመጨረሻ ጊዜ ማስታዉሰዉ አብነትን ከጥቃት ፈፃሚዎቹ አንዱ በያዘዉ ስለት ማጅራቴን ሲወጋኝ ነዉ።
በደመነፍስ ስሮጥ ከወደቅኩበት ስነሳ በቆሎ ማሳ ዉስጥ ነበርኩ፤ እንደምንም አቅሜን አሟጥጬ ወደ መንገድ ወጣሁና አንድ መኪና አስቁሜ ወደቅኩኝ እግዚአብሔር ይስጣቸው አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ትንሽ ስሻለኝ ለቤተሰብ ደዉዬ የደረሰብኝን ነገርኳቸው።
የጓደኛዬን ሞት የሰማሁት በማግስቱ ቤተሰብ መጥቶ በጀልባ ወደ ቤት ከወሰዱኝ በኋላ ነዉ " ብሏል።
ኮሬ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን ይላል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገራቸው የኮሬ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ዙሪያ ወረዳ ሁለት የኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ቡንቲ ቀበሌ ወጣቶች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ወጣት አብነት መገደሉንና ሌላኛው ጓደኛዉ መትረፉን ገልፀዋል።
የጋርዱላ ዞን ፖሊስ ጥቃት አድራሾችን አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ የጋራ መድረክ ፈጥረዉ መነጋገራቸውን ገልፀዋል።
የጋርዱላ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ወደ ጋርዱላ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታዬ ታምሩ የእጅ ስልክ ደዉሎ ቢያነጋግራቸዉም አጠቃላይ የፀጥታ ጉዳዮችን አስመልክቶ መረጃ መስጠት የሚችሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግንኙነት ኪታሞን ቢያነጋግሯቸውም ለጊዜው በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል።
ቀናትን ጠብቆ ድጋሚ ብንደዉልላቸዉም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸው በዚህ ዘገባ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

5 months ago