በእጁ ላይ የታሰሩ ሚሊዮን ዶላሮች
📌የደራው መጽሔት
#ethiopia | በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ታሪክን የጻፈው ክርስቲያን ሮናልዶ፣ ከሜዳ ውጭ ደግሞ በልዩ የቅንጦት አኗኗሩ ይታወቃል። በተለይም ለሰዓቶች ያለው ፍቅርና የሚሰበስባቸው ብርቅዬ ቁሶች የብዙዎችን ቀልብ ይስባሉ። የሮናልዶ የሰዓት ስብስብ (Watch Collection) ብቻውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ሰዓቶቹ የራሳቸው ወግ አላቸው።
1. ጃኮብ ኤንድ ኮ (Jacob & Co.) - የግል ማህተሙ
ሮናልዶ የዚህ ታዋቂ ብራንድ አምባሳደር ከመሆኑም በላይ፣ በስሙ የተሰሩ ልዩ ሰዓቶች አሉት።
* Jacob & Co. Caviar Flying Tourbillon: ይህ ሰዓት በሙሉ በከበሩ የ"ሳፋየር" ድንጋዮች የተሸፈነ ሲሆን፣ ዋጋው ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ይገመታል።
* CR7 Epic X: የሮናልዶን ምስልና ፊርማ የያዘው ይህ ሰዓት፣ የእሱን ስብዕና በሚገልጽ መልኩ የተሰራ ሰዓት ነው።
2. ፍራንክ ሙለር (Franck Muller) - የአልማዞች ስብስብ
ሮናልዶ እጅግ ውድ ከሚባሉ የፍራንክ ሙለር ሰዓቶች አንዱ ባለቤት ነው። Franck Muller Invisible Setting Imperial Tourbillon የተሰኘው ሰዓቱ፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ አልማዞች (Baguette-cut diamonds) ያጌጠ ነው። ይህ ሰዓት በሮናልዶ የእጅ አንጓ ላይ ሲታይ የእግር የኳስ ጌትነቱን ብቻ ሳይሆን የሀብት ማማ ላይ መሆኑን ይመሰክራል።
3. ሮሌክስ (Rolex)
"GMT-Master II"
ሮናልዶ ካሉት የሮሌክስ ሰዓቶች መካከል Rolex GMT-Master II Ice ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ይህ ሰዓት ሮሌክስ እስካሁን ካመረታቸው ሰዓቶች ውድ የሚባለው ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ በ18 ካራት ነጭ ወርቅና በአልማዝ የተለበጠ ነው። ዋጋውም ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ገደማ ይገመታል።
4. ቡጋቲ ቺሮን (Bugatti Chiron Tourbillon)
ሮናልዶ ካለው የቡጋቲ መኪና ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ በጃኮብ ኤንድ ኮ የተሰራለት ሰዓት ነው። የሰዓቱ ውስጣዊ ክፍል ልክ እንደ መኪናው ሞተር የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ለሮናልዶ ልዩ ፍላጎት ተብሎ የተመረተ ድንቅ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።
የደራው መጽሔት
''ፀሐይ አትጠልቅም''

8 months ago