አባቱ አብዩድ ወይም ይሥሐቅ እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ።
ሚያዝያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ የነበረው አጎቱ ጌዴዎን እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ለሰባት ዓመት ተምሮ ፈቀቅ ባለማለቱ አንድ ቀን አጎቱ ተቆጥቶ ገርፈው፡፡ መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ሄዶ ተደበቀ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዛፍ ስር አርፎ እያለ አንዲት ትል ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ስትወጣና ስትወርድ ከቆየች በኃላ በሰባተኛው ዛፉ ላይ ወጥታ የዛፉን ፍሬ ስትበላ ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ትሏ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበችውን ስታሳካ ተመልክቶ ራሱን በመውቀስ ወደ መምህሩ ተመልሶና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡
ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ በመሔድም ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በጣም በአጭር ጊዜም 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችንና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ ዜማ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በስልት እያነበቡ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ኅዳር 5 ቀን 527 ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ፤ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝልና በአራራይ ዜማ ማዜምን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ገልጹለት፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን….” ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡
ሃሌ ሉያ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው” ማለት ነው፡፡ በ534 ዓ.ም ኅዳር 6 ቀን ወደ ሰማይ ተነጠቀ፤ በሰማይ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ጣዕመ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ሰማ፡፡ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ አክሱም ጽዮን ውስጥ ወደ ምሥራቅ በኩል በመዞር ከሰማይ የሰማውን ዝማሬ ዘመረ፤ አርያም ብሎም ሰየመው፡፡ በዚሁም በ538 ዓ.ም ቅዱስ ያሬድ ማኅሌት ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ የሚያገለግሉ ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ የሚባሉ አምስት የዜማ መጻሕፍትም ደርሷል፡፡ ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” ይባላል፡፡
ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡ ይህን ዜማ ከፍ አድርጎ ሲያዜም ሰው፣ እንስሳና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ልዩውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ብሎም የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራችም ነው፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃዉንት እያጣቀሰ መንፈሳዊ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በመጨረሻ በተወለደ በ75 ዓመቱ በገዳማዊ ሕይወት በኖረበት በሰሜን ተራሮች ደብረ ሐዊ ገዳም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡
ገዳማውያን እንኳን ዓለማዊ ደስታ ሊመኙ መንፈሳዊ ክብራቸውም በሰው ፊት እንዲገለጽ አይሹም፡፡ ለኛ ለደካሞቹ ግን ሁሌም ይጸልዩናል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እየደግፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

8 months ago