Logo
Getu Temesgen
የሊቢያ ትልቁ ሙዚየም ከጋዳፊ መውደቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከፍቷል
#ethiopia | በትሪፖሊ የሚገኘው አስ ሳራያ አል ሃምራ በመባል የሚታወቀው የሊቢያ ብሔራዊ ሙዚየም ከ14 አመታት ቆይታ በኋላ ዳግም ተከፍቷል።

የሊቢያ ትልቁ ሙዚየም በ2011 የወቅቱ የሃገሪቱ መሪ በነበሩት ሙሐመር ጋዳፊ ላይ አመፅ መቀስቀሱን ተከትሎ ተዘግቶ ቆይቷል።

በ2021 ወደ ስልጣን የመጣው መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው የብሔራዊ አንድነት መንግስት በ2023 የሙዚየሙን እድሳት ያስጀመረ ሲሆን የዚህ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዲቤቢያ የሙዚየሙ መከፈት ሊቢያ ተቋማቷን ዳግም እየገነባች ስለመሆኗ ማሳያ ነው ብለዋል።

በ10,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሙዚየም ግንባታው በ1980ዎቹ ሲደረግ ሙዚየሙ አሁን ለተማሪዎች ብቻ መከፈቱንና በመጪው አዲስ አመት ለሁሉም ሰው ክፍት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከጋዳፊ መውደቅ በኋላ ትርምስ ውስጥ የከረመችው ሊበያ በዩኔስኮ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ 5 መስህቦች አሏት።

ሊቢያ በአሁኑ ጊዜ ተመድ እውቅና በሚሰጠውና በዋነኝነት በቱርኪዬ በሚደገፍ መቀመጫውን ትሪፖሊ ባደረገ መንግስትና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ግብፅ እንደዚሁም ሩሲያ በሚደገፈው መቀመጫውን ቤንጋዚ ባደረገው የካሊፋ ሃፍታር መንግስት እየተመራች ትገኛለች ያለው ቲክቫህ ነው።

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.