ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነገደቡ በፊት ማሟላቱ ተገለፀ!!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉን በማሳደግ ብር 5 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልፀዋል፡፡ ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ102 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ባንኩ ባንኮች ካፒታላቸውን 5 ቢሊዮን ብር እንዲያደርሱ በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን አቅጣጫ ከጊዜ ገደቡ በፊት ማሳካት መቻሉ በባለአክሲዮኖቹ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2024/2025 በጀት ዓመት ከ 5.56 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለፀ ሲሆን ዘንድሮ የተመዘገበው የባንኩ ገቢ ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተነግሯል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደተናገሩት ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ለደንበኞቻችን ከፍ ያለ አገልግሎት በመስጠት፣ የገበያውን ተለዋዋጭነት በመረዳትና በዚሁ መሰረት የሚንቀሳቀስ የስራ አመራር በመገንባት እንዲሁም ሀብት ለማሰባሰብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በጁን 30, 2025 በተዘጋው በጀት ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ከ 34.4 ቢሊየን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 42 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 7.53 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ 41 በመቶ ብልጫ በማሳየት የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን ወደ ብር 25.75 ቢሊዮን ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከዓለም አቀፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ጋር ተዳምሮ በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ሁኔታው አለመረጋጋት ያሳየ ቢሆንም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ 1.17 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል፡፡
የባንኩ ቅርንጫፎች ከባንክ አገልግሎት ተጠቃሚውና ከሰፊው ሕብረተሰብ ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች ከመሆናቸውም በላይ የባንኩን የአገልግሎት ጥራት ደረጃ ልኬት የሚወስኑ እንዲሁም የባንኩን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያንጸባርቁ መሆናቸው ታምኖበት ቅርንጫፎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ልዩ አቅጣጫ ተቀይሶ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም መሰረት ጁን 30, 2025 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 12 አዳዲስ ቅርንጫፎች ተከፍተው የባንኩን ቅርንጫፎች ብዛት ወደ 237 አድርሶታል፡፡
ባንኩ ለዋና ዋና ደንበኞች የተለየና ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ የሚሰጥባቸው ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ፕሪሚየም ቅርንጫፍን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ፕሪሚየም ቅርንጫፎችን በዋና መስሪያ ቤቱ ስታዲየም ቅርንጫፍ እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ መስሪያ ቦታ ላይ በሚገኘው ሜክሲኮ ፕሪሚየም ቅርንጫፍ የላቀ ፈጣንና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ባንኩ ዘመኑ የደረሰበትን የኮር ባንኪንግ አገልግሎት በመጠቀም ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ የዲጂታል ባንኪንግ ማለትም የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የአጭር መልዕክት (USSD) አገልግሎት በመስጠት ከ 636,048 በላይ ደንበኞችን አፍርቷል፡፡
ከካቻ ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር በመተባበር የዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎትን እየሰጠ ሲሆን@ እንዲሁም በአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኢንሹራንስ አረቦን ብድር አገልግሎት በመጀመር ከተለያዩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር በጋራ በመስራት የፋይናንስ አካታችነትን እያበረታታ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ደንበኛ ተኮር የሆነ እጅግ ዘመናዊ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል በማዘጋጀት ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዶክተር ተስፋዬ ቦሩ እንደተናገሩት ባንኩ የሸሪዓን ህግ እና ደንቦች መሰረት ያደረገ ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሆነና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በተለያዩ ቅርንጫፎች ለዚሁ አገልግሎት በተመደቡ 237 መስኮቶች እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ ስድስት ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ወደፊትም ዘርፈ ብዙ ከወለድ ነፃ የባንክ አግልግሎቶችን ለመስጠት በቁርጠኝነት በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ‹‹ለጋራ ስኬታችን›› የሚለውን መሪ ቃል በተግባር መሬት ላይ በማውረድና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በአካባቢ ጥበቃ፣ በማህበራዊ ደህንነት፣ በሰብዓዊ እርዳታና በልማት ስራዎች አሻራውን ያሳረፈበት ስኬታማ የበጀት አመት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የያዘውን የዕድገትና የስኬት ጉዞ በማስቀጠል ከፋይናንስ ነክ ስኬቶቹ በተጨማሪ በ2025 የአፍሪካ ባንክና ኢንሹራንስ አዋርድ ላይ የአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ሽልማትን ያገኘ ሲሆን ከዓለም አቀፍ ስትራቴጂክ አሊያንስ ማዕከል ደግሞ አዲስ የዲጂታል የፈጠራ እና ልህቀት ሽልማትን አግኝቷል፡፡
እነዚህ ዕውቅና እና ሽልማቶች ባንኩ በቁጠባ እና በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ላይ ያለውን ጠንካራ አመራር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ከባንክ ነክ ስራዎች ባሻገር የባንኩ የእግር ኳስ ቡድን በአዲስ አበባ በባንኮች መካከል በተካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ሻምፒዎን በመሆን ባንኩ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን የነቃ ተሳትፎ ማሳየት ተችሏል፡፡
ባንኩ ታህሳስ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ 13ኛ መደበኛ እንዲሁም 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል፡፡

6 months ago