Logo
Getu Temesgen
በግመል ስፖርት ብቅ ያለው ፖል ፖግባ
#ethiopia | ፖል ፖግባ በሳዑዲ አረቢያ የግመል ውድድር ስፖርት ውስጥ መጠነኛ ድርሻ መግዛቱን አሳውቋል፡፡ ፈረንሳዊው አማካይ በሳዑዲ አል ሀቡብ የተሰኘ የግመል ውድድር ቡድንን ድርሻ በመግዛት ብዙም በላልተለመደው ስፖርት መከሰቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

አል ሀቡብ የተሰኘው በዓለም የመጀመርያው ፕሮፌሽናል የግመል ውድድር ቡድን በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሌሎች የባህረ ሰላጤው ሀገራት ወስጥ የሚካሄድ ትልቅ ፉክክር የሚደረግበት ነው፡፡

የሞናኮው አማካይ የቡድኑ አምባሳደር ከመሆኑ በተጨማሪ የተወሰነ ድርሻ ያላው ሲሆን ስፖርቱን ከዚህም በላይ ማሳደግ እና ማዘመን እንደሚፈልግ ተዘግቧል፡፡

የግመል ውድድርን በተደጋጋሚ በዩቱብ ይከታተል እንደነበር የገለጸው የ32 ዓመቱ ተጫዋች ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ብዙ ጥናቶችን ማድረጉንም ይፋ አድርጓል፡፡

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እና ጁቬንቱስ አማካይ ሁሉም ስፖርቶች ቁርጠኝነትን እና የጋራ ስራን እንደሚጠይቁት ሁሉ የግመል ስፖርትም ከዚያ የተለየ አይደለም ብሏል፡፡

የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ኮከብ የአበረታች ቅመም ተጠቃሚነት ቅጣቱን ካጠናቀቀ በኋላ በሀገሩ ክለብ ሞናኮ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ባህል የሚቆጠረውን የግመል ውድድር በይፋ ተቀላቅሏል፡፡
#ebcdotstream

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.