Logo
SeledaPost
በአሜሪካ መወለድ ብቻውን አንድ ሺህ ዶላር ያስገኛል

ለአሜሪካ ህጻናት የተከፈተው ''ትራምፕ አካውንት"

ከመጪው የፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 2026 የአሜሪካ የነጻነት ቀን ጀምሮ፣ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በአሜሪካ የሚወለዱ ህጻናት ''ትራምፕ አካውንት" በተሰኘ የባንክ ሂሳብ፣አንድ ሺህ ዶላር ይበረከትላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፊርማቸውን በማኖር ባስጀመሩት በዚህ መርሐ ግብር መሰረት፣ በመገባደድ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2025 የተወለደች አንዲት ህጻን በመጪው ሐምሌ አንድ ሺህ የአሜሪካ ዶላር የያዘ የባንክ ደብተር ይኖራታል።

በመርሐ ግብሩ መሰረት፣ለእዚች ልጅ፣ወላጆቿ፣ ቤተሰቦቿ ወይንም ሌሎች መሥሪያ ቤቶች በባንክ ቁጥሯ፣በዓመት እስከ አምስት ሺህ ዶላር ድረስ ሊቆጥቡላት ይችላሉ። በዚህ ስሌትም፣ ይህች ልጅ 18 ዓመት ሲሆናት፣ 170 ሺህ ዶላር ይኖራታል፡፡

''ይሄ የትራምፕ አካውንት፣ከ18 አመት በታች ያሉ ህጻናትን ይመለከታል። አካውንቱ በገንዘብ ግምጃ ቤት የግብር ክፍል የሚከናወን ሲሆን፤ በዚህ ዓመት 2025 ከጥር አንድ ቀን ጀምሮ፣ አሜሪካ ውስጥ ለተወለዱ ወይም የአሜሪካ ዜግነት ላላቸው ህጻናት አንድ ሺ ዶላር የሚሰጥ ነው። ይህ አንድ ሺህ ዶላር በባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው የሚገባ ነው። እስከ 2028 ድረስ የሚቀጥል ነው፤በትራምፕ ዘመን ማለት ነው።" ሲሉ በአትላንታ ጆርጂያ የታክስ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አስገዶም ተመልሶ ለዶቸ ቬለ አብራርተዋል፡፡

አቶ አስገዶም እንደሚሉት፣ልጆቹ 18 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ፣ይህንን ገንዘብ ከባንክ ሂሳባቸው ማውጣት አይችሉም። ''18 ዓመት እስኪሞላቸው፣አይነካም፤ማውጣት አይችሉም። እና እያደገ እያደገ ይሄዳል።18 ዓመት ሲሞላቸው፣በቂ ገንዘብ ይኖራቸዋል የሚል እሳቤ ነው።'' ብለዋል፡፡
seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.