Logo
Getu Temesgen
ፍቅር እስከ ባህር
#ethiopia | በምዕራባውያን አቆጣጠር 2011 ጃፓናውያን አስከፊ በሆነ ሱናሚ የተባለ የባህር ወጀብ ተመቱ፡፡ ያ ሱናሚ ሊገመትም እንደሚቻለው የብዙዎችን ሕይወት ቀጠፈ፣ ቤቶች ብቻ ሳይሆን መንደሮችን አፈራረሰ፡፡ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችም የደረሱበት ሳይታወቅ ጠፍተዋል፡፡

ታዲያ በሱናሚው ምክንያት የደረሱበት ከጠፋ ሰዎች መሃከል የአንዱ ቤተሰብ ታሪክ፣ ይኼው ዛሬ ከአደጋው 14 ዓመታት በኋላም መነጋገሪያ ሆኖ ዘልቋል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው…
የባንክ ባለሙያዋ ዩኮ እና የልዩ ጥበቃ አባል ወታደሩ ያሱዎ ባለትዳሮች ናቸው፡፡ በ1988 የተመሠረተው ትዳራቸው ለአካባቢው ሰው ሁሉ ምሣሌ ነበር፡፡ አንድ ዕለት ያሱዎ፣ ባለቤቱ ዩኮን እስከ መሥሪያ ቤቷ በር ያደርሳትና፣ የሚስቱን እናት አማቹን ደግሞ በዕለቱ ለነበራቸው የሕክምና ክትትል ሐኪም ቤት ወሰዳቸው፡፡

እርሣቸውን ሐኪም ቤት አስገብቶ ወደ ሥራው ለመኼድ መንገድ ከጀመረ ከአፍታ በኋላ ግን፤ ለስድስት ደቂቃዎች የዘለቀ ከባድ ርዕደ-መሬት ተከሰተ፡፡ ያሱዎ በመኪናው ውስጥ ያለውን ሬዲዮ ሲከፍት ርዕደ-መሬቱ ከበድ ያለ ሱናሚ ማስከተሉ እየተዘገበ አደመጠ፡፡

ይህን ሲሰማ አስቀድሞ ወደ ወንድ ልጁ ደወለ፤ ደህና እንደሆነም አረጋገጠ፡፡ የባለቤቱ እና ሴት ልጁን ሥልክ መስመር ግን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ አንድ ሊያገኝ የቻለው ነገር ባለቤቱ በደምጽ የተወችለት መልዕክት ነው፡፡

‹‹አስፈሪ ሁናቴ ውስጥ ነኝ፤ ቶሎ ወደቤቴ መመለስ እፈልጋለሁ፡፡›› ይላል፡፡

ያሱዎ የባለቤቱን ዳና ፍለጋ በሆስፒታል፣ መጠለያ ጣቢያ ሁሉ ተሰማራ፡፡ ምንም ሊያገኝ አልቻለም፤ ከአንድ ወር በኋላ የሚስትህ ዩኮ የእጅ ሥልክ ተገኝቷል ተብሎ ተጠራ፡፡ ሥልኳ ላይ ‹‹ሱናሚው እጅግ ያስፈራል›› የሚል መልዕክት ጽፋ የነበረ ቢሆንም ለእርሡ አልደረሰውም፡፡ ከዚህ በቀር ሚስቴን አፋልጉኝ ብሎ በየቦታው ቢፈልግ አንዳችም መረጃ ሳይሰማ ቀናት፣ ሣምንታት፣ ወራት አለፉ፡፡

ይኼው ዘንድሮ 14 ዓመታቸው፡፡

ያሱዎ ግን ተሥፋ አልቆረጠም፡፡ ዜናውን የነገረን ዴይሊ ሚረር እንደዘገበው አቶ ያሱዎ ላለፉት 14 ዓመታት 50 እና 60 ሜትር ድረስ ጥልቀት ያለው ባህር ውስጥ ጭምር ከ400 ጊዜያት በላይ ዋኝቶ ሚስቱን እየፈለገ ነው፡፡

ስለተግባሩ ለጠየቁትም
መፈለግ እኔ መች ሰለቸኝ፣ ገና ብዙ ይቀረኛል
ሚስቴን እስካገኝ ድረስ መቼ ድካም ይሰማኛል
ብሏል አሉ፡፡
#tirtafm

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.