Logo
Getu Temesgen
♦️የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ አሠልጣኞች ማህበር መግለጫ አውጥቷል

♦️በህግ እንዲጠየቁ፣ማገገሚያ እንዲገቡ፣በምክር እንዲመለሱ ውሳኔ ተላልፏል

♦️የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

✍ለመላው የማህበሩ አባላት በሙሉ፦
#ethiopia | ሰሞኑን ከሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘውን ጉዳይ በትኩረት እና በንቃት እየተከታላችሁት እንደሆነ እናውቃለን ምክንያቱም ይህ ጉዳይ በቀጥታ ከሥራችን ጋር ተያያዥነት ስላለው በመሆኑም ምንም እንኳን ቀደም ባሉት ጊዚያት በዚህ ጉዳይ ማህበራችን ሰፊ ውይይትና ክርክር በማካሄድ አንድ እልባት ላይ መደረስ እንዳለበት ስንነጋገር ቆይተናል።

እነሆ ጉዳዩ ለሚዲያ በቅቶ በህብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።ጉዳዩ በመንግሥት አካላት ትኩረት አገኝቶ ከሰሞኑ ውይይት ተደርጎ መንግስትም ለዚህ አፀያፊ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ለጉዳዩም የሚመለከታቸውን አካላት ጠርቶ አወያይቷል በዚህም ስብሰባ ላይ

-የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን

-የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

-ስፖርት ኮሚሽን

-የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ አሠልጣኞች የሙያ ማህበር

-የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር

-የCD ስፖርት አዘጋጆች
ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዷል።

በውይይቱ እንደተገለፀው ጉዳዩን የሚያጣራ የምርመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደሥራ መገባቱን ለዚህ አፀያፊ ተግባር መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ ተመላክቷል።

በዚህ ተግባር ተሳታፊ ሆነው ጉዳያቸው በማስረጃ የተረጋገጠ ተጨዋቾች ላይ ከዚህ እንደሚከተለው በየደረጃው ውሳኔ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል👇

1.በህግ እንዲጠየቁ

2.ማገገሚያ እንዲገቡ

3.በምክር እንዲመለሱ የሚደረግ ሲሆን ይህንንም ጉዳይ በሚገባ ለመከታተል ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የሚገኙበትን አድራሻ ለፓሊስ እንዲያሳውቁ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።

በዚህም ሂደት ፖሊስና ኢንሳ በፈለጉበት ጊዜና ሰዓት በክለቦቹ በመገኘትምርመራ እንደሚያደርጉ ተገልጿል ።
የፓሊስና የኢንሳ የምርመራ ቡድን

-የክለብ ባለቤቶችን

-አሠልጣኞችን
-ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አካላት እንደሚያነጋግሩ ተገልጿል ።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በእለቱ በስብሰባው ላይ በአፅንኦት እንደገለፀው ለዚህ አፀያፊ ተግባር በቂ እርምጃ እንደሚወሰድና
1.በጉዳዩ ላይ በቂ ማስረጃ የተገኘባቸው በየትኛውም ክለብ ገብተው እንደማይጫወቱና እነዚህንም የተቀበለ ክለብ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው

2.አሰፈላጊ ሆነ ከተገኘ ፌዴሬሽኑ ሊጉን እንደሚዘጋና ትውልዱን ለማዳን የትኛውንም ዋጋ እንደሚከፈል አሳውቋል።በአጠቃላይ በተካሄደው ስብሰባ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ አሰፈላጊው የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባቱ ተገልጿል ።

በመሆኑም መላው የማህበራችን አባላት ቀደም ሲል ስንጮህለት የነበረው ጉዳይ አጋዥ በማግኘታችን መንግስት ለሚጠይቀው ጥያቄ ተባባሪ በመሆን ይህንን ሀገርን እና እግር ኳሳችንን የሚጎዳ ተግባር ልናጠፋ እንደሚገባ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ስለሆነም ከላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ተባባሪ እንድትሆኑ ስንጠይቅ በዚህ መሀል ንፁህ ለሆኑ ተጫዋቾች ከለላ ልንሆንላቸው ይገባል።

ቀደም ሲል ስንል እንደነበረው ማህበራችን ይህንን በሁሉም መስኩ ጎጂ የሆነን ተግባር በፅኑ እንደሚያወግዝ እያረጋገጥን ንፁህ ዜጋና ንፁህ እግር ኳስ በሴቶች እንዲኖር እንደሚሠራ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የትኛውንም አይነት ጥቃት እንደሚያወግዝ ለመግለፅ ይወዳል።
ህዳር 10/03/18 ዓ/ም
የኢ/የሴ/እ/አሠ/የሙያ ማህበር

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.