በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ጋዜጣዊ
መግለጫ
የጤና ሚኒሰቴር፥ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን እንዳይከሰቱ የመከላከል እና ከተከሰቱም በአፋጣኝ የማረጋገጥና የተቀናጀ የቅኝትና የምላሽ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic fever) በሽታ መከሰቱን የቅኝት መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች(08) በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑ ታውቋል።
በዚህም መሰረት የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው በመላክ የመስክ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ ሲሆን በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣ የንክኪ ልየታ፣የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል።
በመሆኑም መላዉ ሕብረተሰባችንና የሚመለከታቸዉ የባለድርሻ አካላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምክረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
👉በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልክት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣
👉ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣
👉 ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት፣
👉ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቫይራል ሄሞሬጅክ ፊቨር (Viral Hemmoragic fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ ማከም እና ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል
ተጨማሪ መረጃዎችን ወደ 8335 እና 952 ነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ማግኘት ይቻላል፡ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር

9 months ago