Logo
FastMereja
ነጻ ዋይፋይ ያለው፣ ክፍያ በQR code የሚቀበለው፣ ወላድ እና አካል ጉዳተኛ ነጻ የሚያሳፍረው ታክሲ
#fastmereja I Boliya Taxi ይባላል በአዲስ አበባ የታክሲ ስራን ከዘመናዊነት ጋር እያለማመደ የሚገኝ የታክሲ ሾፌር ነው።

ተሳፋሪዎች በካሽ መክፈል ካልፈለጉ አልያም ካሽ ካልያዙ ምንም አያሳስብም QR code በማዘጋጀት በንግድ ባንክ እና በቴሌብር መክፈል የሚችሉበት ታክሲ ነው ቦሊያ ታክሲ።

በተጨማሪም አዲስ አበባን Boliya Taxi በተሰኘው በቲክቶክ ገጹ ቀጥታ ስርጭት እያስጎኘ ስራውን እየሰራ ይገኛል።

እንዲሁም የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለተሳፋሪ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ይገኛል።

ቦሊያ ወላድ እናት እና አካል ጉዳተኞችን በነጻ ትራንስፖርት ይሰጣል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.