አዲሱ የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ
📌በአሜሪካ ትልቋ ከተማ ኒው ዮርክ ለከንቲባነት በመመረጥ የመጀመሪያው ሙስሊም በመሆን ታሪክ ሠርቷል።
#ethiopia | ዞህራን ምርጫውን ካሸነፈ በኋላ ባደረገው ንግግር ቤተሰቦቹን እና ባለቤቱን አመስግኗል።ድምጻቸውን የሰጡት የኒው ዮርክ ነዋሪዎች "ለውጥ እንዲመጣ መፍቀዳቸውን" እንዳሳዩት ተናግሯል።
ዞህራን የኒው ዮርክ ከንቲባ እንዲሆን ንቅናቄ ያደረጉ እና ድምጽ የሰጡ ነዋሪዎችንም በንግግሩ ሳይጠቅስ አላለፈም።
"የመናውያን የመደብር ባለቤቶች፣ ሴኔጋላውያን የታክሲ ሹፌሮች፣ ኡዝቤክስታናውያን ነርሶች እና ኢትዮጵያውያን 'አክስቶች' " ሲል ድጋፍ የሰጡትን ዘርዝሯል።
ዞህራን ባደረገው የ30 ደቂቃ ንግግር "በዚህ ጨለማ የፖለቲካ ዘመን ኒው ዮርክ ብርሃን ትሆናለች" ብሏል።
"ዶናልድ ትራምፕ [ንግግሬን] እየተመለከትክ እንደሆነ አውቃለሁ። አራት ቃላት ልናገር እፈልጋለሁ። ድምጹን ከፍ አድርገው። እኛ ጋር ለመድረስ ሁላችንንም ማለፍ አለብህ" ሲልም ዞህራን ተናግሯል።
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ገጻቸው ". . . ተጀምሯል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዞህራን አንጋፋው ፖለቲከኛ እና የቀድሞ የኒው ዮርክ ከንቲባ የሆኑት አንድሪው ኩዎሞን አሸንፎ የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ መሆኑ በርካታ የፖለቲካ ታዛቢዎችን ማስደነቁ ይታወሳል።
የግራ ዘመም ፖለቲከኛ፣ የፍልስጤማውያን መብት ተሟጋች፣ የስደተኛ ልጅ፣ ሙስሊም የሆነው ዞህራን የበርካታ ዓመታት ልምድ እንዲሁም የቢሊዮነሮች ድጋፍ ያላቸውን አንድሪው ኩሞን ያሸንፋል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር።#ባለገሩ

7 months ago