“የኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የማግኘት ጉዳይ አይቀሬ ነው”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የማግኘት ጉዳይ አይቀሬ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ገለፁ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ትናንት ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የማግኘት ጉዳይ አይቀሬ ነው ብለዋል።
ለብዙ ሀገራት በተናጠል በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ለጉዳዩም ቅድሚያ የሚሰጠው ሰላምና ንግግር ስለሆነ በንግግር መፍትሔ እንዲመጣ ጠይቀዋል።
የኤርትራ ህዝብ አሁንም ወንድም ህዝብ ነው፤ ሀገሩን ለቅቆ እየተሰደደ ያለ ህዝብ ነው ከዚህ ህዝብ ጋር በጋራ መሥራት ፍላጎታችን ነው፤ በፍጹም የውጊያ መሻት የለንም ብለዋል።
የቀይ ባህር ጉዳይ የተነሳው የውስጥ ጉዳዩን ለመሸፈን ነው ተብሎ የተነሳው ትክክል እንዳልሆነ፤ የሚሸፍን የውስጥ ጉዳይም እንደሌለ፤ ያለው ልማት መሆኑን አመልክተዋል።
#ጋዜጣፕላስ

8 months ago