Logo
YenetaTube
ቻይናን መግታትና ማስቆም የሚችል አቅም እየገነባሁ ነዉ !/ ታይዋን /

ታይዋን መጣሁ መጣሁ እያለች ያለዉን የቻይናን "ወረራ " ለመመከት የሚያስችል
ውጤታማ መከላከያን እየገነባችና ራስን የመከላከል እና የመምታት አቅሟን ለማጠናከር የሚሳኤል ስርአት ጨምሮ አስተማማኝ ሀይል እየገነባሁ ነዉ ማለቷ ተነገረ ።

የታይዋን ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ በአሁኑ ጊዜ 3,500 በላይ ታይዋንን እንዳልነበረች የሚያደርጉ ሚሳኤሎች እንደታጠቀ የሚነገርላትን የቻይናን ወታደራዊ "ወረራ "ለመከላከል ታይዋን የራሷን የሚሳኤል ትጥቅ በማደራጀት በማጎልበት እና የቤጂንግን ወታደራዊ ስጋቶች በብቃት ለመግታት የሚያስችል የመልስ ምት ለመስጠት እየተዘጋጀች መሆኑን ገልጿል ።

ቻይና ከ1,500-2,500 ኪሎ ሜትሮች ተምዘግዝገዉ በምእራብ ፓስፊክ ውቅያኖስ የአሜሪካ አየር ሰፈሮችን እና መርከቦችን ማደባየት የሚችሉትን DF-17፣አዲስ ሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤል በታይዋን አቅራቢያ በሚገኘው የህዝብ ነፃ አውጪ ጦር የሮኬት ሃይል (PLARF) ጣቢያ ማሰማራቷን ተከትሎ የታይዋን የብሄራዊ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቺያኦ ፉ ቹን (喬福駿) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጋራ የመረጃ፣ የክትትልና የስለላ አቅሞችን በመጠቀም የ PLARFን ስምሪት በቅርበት እየተከታተለ ነው። ሲል ተናግሯል ።

ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ከሆነ ፦ታይዋን በአሁኑ ጊዜ የቻይናን ዋና መሬት ለመምታት የሚችሉ በርካታ አይነት ሚሳኤሎች ያሏት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ዩንፌንግ ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳይል ጨምሮ በርካታ ሚሳኤሎች ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል ።

ካኦ ከዚህም በተጨማሪም( ናሽናል ቹንግ ሻንሲስት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት)፣NCSIST ባለፈው ወር በታይፔ ኤሮስፔስ ኤግዚቢሽን ላይ ይፋ የሆነው የቺያንግ ኮንግ ("ጠንካራ ቀስት") ከምድር-ወደ-አየር ኢላማዎችን ሊመታ የሚችል አዲስ ሚሳኤል በማዘጋጀት ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል ።

አክሎም፦ ታይዋን ውጤታማ መከላከያን እንድትዘረጋ የቻይናን ፈጣን መስፋፋት ለመግታት ራስን የመከላከል እና የመምታት አቅሟን በማሳደግ የሚሳኤል መሳሪያዋን "በከፍተኛ ሁኔታ ማስፋት" አለባት ሲል አሳስቧል።

ቻይና በአሁኑ ጊዜ ወደ 1,000 የሚጠጉ የአጭር ርቀት ሚሳኤሎች ታይዋን ላይ ያነጣጠሩ እንደሆኑ 300 የሚጠጉት
በኦኪናዋ የሚገኘውን የካዴና አየር ቤዝ ያሉ መርከቦችን እና የአሜሪካ አየር ማረፊያዎችን በምእራብ ፓስፊክ ለመምታት የሚችሉ መሆናቸው ለዚህም ተመጣጣኝ መከላከያ መገንባት ወሳኝ መሆኑን ካኦ ገልጿል።

"ታይዋን በንቃት መከላከያዎች ላይ ሙሉ በሙሉ መታመን አትችልም፣ ያሉት ሚኒስትሩ ታይዋን ለቻይና ወታደራዊ ጥቃት ለመከላከል አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባና የዋሽንግተን ድጋፍ ምላሾችን ማብዛት አስፈላጊ መሆኑን አበክሮ ገልጿል። ሲሉ ያስነበቡት ታይዋን ትሪቡን ኒውዮርክ ታይምስ ፎከስ ኒዉስ ናቸዉ ።
#የኔታ_ቲዩብ_ዘጋቢ#ታዴ_የማመይ_ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.