7ኛዉ የዓለም የታካሚ ደህንነት ቀን" በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ 5ኛ ጊዜ በድምቀት ተከበረ!።
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ዓመታዊ የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በዓል በድምቀት አክብሯል።
በዝግጀቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ደህንነት አማካሪ ሚኒስተር ዴታና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክቡር ዶ/ር ቀንአ ያደታ ፣ የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ ፣ የጤና ሚኒስቴር ዴታ ክብርት ሰሀረላ አቡዱላሂ ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ ፣የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ መልካሙ ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕ/ር ነፃነት ወርቅነህ ፣ በጤና ሚኒስተር የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አባስ ሐሰን ፣ የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ ፣ እንዲሁም የጤና ሙያ ማህበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች፣ጥሪ የተደረገላቸው የላንድማርክ ሆስፒታል ሰራተኞችና ታካሚዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ ተቋሙ ለአስተማማኝ የህክምና ተግባራት እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት አፅንኦት ሰጥቶ በመስራት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት እየተካሄደ ያለውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት የአለም አቀፍ የታካሚ ደህንነት መስፈርቶችን ባማከለ መልኩ ለጤና አጠባበቅ ልህቀት ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጡ ገልፀዋል ። የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ የታካሚዎችን ደህነነት ለማሳለጥና የጤና አጠባበቅ አሰጣጥን ለመምራት የአለም አቀፍ የደህንነት ደረጃዎች እና መመዘኛዎች ያለውን ጠቀሜታ አስምረውበታል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ወክለው የተገኙት አቶ መልካሙ ጥሩነህ በከተማ አስተዳደሩ የታካሚዎች ደህንነት ማስጠበቅ እርምጃዎች አፈጻጸም ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አቡዱላሂ በበኩላቸው መንግስት ለታካሚዎች ደህንነት የሚሰጠውን ትኩረት እንደ ሀገራዊ የጤና እንክብካቤ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አረጋግጠዋል።
በዝግጅቱ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች መልአክት ፣ የሰራተኞች ቁርጠኝነት እና የታዩ የታካሚ ምስክርነቶችን ጨምሮ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለታካሚ ተኮር እንክብካቤ ያለውን ሁለንተናዊ አቀራረብ አጉልተዋል።
በመጨረሻም የሆስፒታሉን የታካሚ ደህንነት-ተኮር መሠረተ ልማት እና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በማየት የጨቅላ ህፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ፣ የቀዶ ህክምና ክፍል ፣የኩላሊት እጥበት ፣ የምግብ እና የልብስ ማጠቢያ አገልግሎቶችን ጨምሮ የሆስፒታል ማስፋፊያ ስራ ጎብኝተዋል። ዝግጅቱ የታካሚ ደህንነትን በሚመለከት የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን በመጎብኘት ተጠናቋል።
#worldpatientsafetyday #patientsafety #landmark #landmarkhospital #maternalandchildhealth

8 months ago