12 days ago
ላንድማርክ ሆስፒታል የታካሚዎች ደህንነት ቀንን አከበረ
#ethiopia | ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀንን ለ8ኛ ጊዜ አከበረ። የዘንድሮው መርሃ ግብር በተለይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ለሚጠቁ ታካሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምናና እንክብካቤ ማረጋገጥ ላይ አተኩሯል።
የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል መስራች ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከ11 ታካሚዎች አንዱ በሕክምና ሂደት ወቅት ከደህንነት ጉድለት ጋር በተያያዘ ለጉዳት ሊዳረግ እንደሚችል የዓለም አቀፍ መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። በታዳጊ ሀገራት ደግሞ ችግሩ የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና ለማረጋገጥ የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች ጥራት፣ የሕክምና መሣሪያዎች ተገቢ አጠቃቀምና ጥገና፣ የጤና ባለሙያዎች ብቃትና ሥልጠና እንዲሁም የጤና ተቋማት የአሠራር ሥርዓት ወሳኝ መሆናቸውን ፕሮፌሰር ከበደ አስረድተዋል። የታካሚዎች ደህንነት እንዲረጋገጥም የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች፣ ቤተሰቦች፣ ማህበረሰብና መንግሥት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በዘንድሮው የታካሚዎች ደህንነት ቀን ትኩረት የተሰጠው በተለይ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታና ሥር የሰደዱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ጨምሮ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚጠቁ ታካሚዎች የሚያገኙት ሕክምና አስተማማኝ እንዲሆን ነው። በጊዜ መመርመር፣ ተገቢ ሕክምና መስጠትና ቀጣይነት ያለው ክትትል ማድረግ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ መሆኑ ተጠቁሟል።
የታካሚዎችና የቤተሰቦቻቸው ተወካይ ኢንጂነር ፈቲያ መሐመድ በበኩላቸው፣ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ከታካሚው ጋር በቅርበት ስለሚገኙ በሕክምና ሂደት ውስጥ ቀድመው ሊያስተውሏቸው የሚችሉ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል። የታካሚዎችንና የቤተሰቦችን ድምፅ መስማትና ማክበር የታካሚዎችን ደህንነት ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በዕለቱ ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የሚደረገውን ሕክምና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የጋራ የትብብር ስምምነት ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል።
የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀን ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን፣ ዓላማው በሕክምና ሂደት የታካሚዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ ግንዛቤ ማሳደግና በዘርፉ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ነው።
#patientsafety #safecare
#worldpatientsafetyday #safehealthcare #healthcaresafety #patientcare #healthcarequality #healthforall

19 days ago
በአለም በየአመቱ 134 ሚሊዮን የሕክምና ስህተቶች ይፈፀማሉ!
#ethiopia | ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም የሕሙማን ደኅንነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።
እለቱን አስመልክቶ የአለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 134 ሚሊዮን የሕክምና ስህተቶች እንደሚፈጸሙና ይህም ለ2.6 ሚሊዮን ዜጎች ሕይወት ህልፈት ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል።
ዛሬ መስከረም 7 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሕሙማን ደኅንነት ቀን ምክንያት በማድረግ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ችግሩ በተለይም በታዳጊና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ አመላክቷል።
ድርጅቱ ጥንቃቄ በጎደለውና ጥራቱን ባልጠበቀ የሕክምና ምርመራ መድኃኒት አሰጣጥ እንዲሁም የአገልግሎት ግድፈት ምክንያት ነው የሚከሰተው ብሏል።
ይህ ችግር በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ በየዓመቱ 1.6 ትሪሊዮን ዶላር የምርታማነት መጓደልና የኢኮኖሚ ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ የዓለም ባንክና የሕክምና ተቋማት ጥናቶች ጠቁመዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለፀው አብዛኞቹ የሕክምና ስህተቶች በቅድመ ጥንቃቄና በዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶች ሊቀነሱ የሚችሉ ናቸው ብሏል።
በመሆኑም በዘርፉ ላይ የሚደርሰውን የሰውና የኢኮኖሚ ኪሳራ ለማስቀረት የሕሙማንን ደኅንነት መጠበቅ የጤና አገልግሎት ዋነኛ አካል ማድረግ ይገባል ሲል ገልጿል።
የሕክምና ተቋማትን በዲጂታልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት ያስፈልጋል ነው ያለው።
እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበትና ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ተጠቅሷል።
የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት የጤና ዘርፋቸውን በማዘመን የዜጎችን የማምረት አቅም እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል።
ስምንተኛው የዓለም የህሙማን ደህንነት ቀን በሀገራችን ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በዘውዲቱ መታሰብያ ሆስፒታል በተለያዩ መርሀግብሮች ተከብሮ ውሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #worldpatientsafetyday #who #patientsafety #healthnews

1 year ago
7ኛዉ የዓለም የታካሚ ደህንነት ቀን" በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ 5ኛ ጊዜ በድምቀት ተከበረ!።
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ዓመታዊ የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በዓል በድምቀት አክብሯል።
በዝግጀቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ደህንነት አማካሪ ሚኒስተር ዴታና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክቡር ዶ/ር ቀንአ ያደታ ፣ የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ ፣ የጤና ሚኒስቴር ዴታ ክብርት ሰሀረላ አቡዱላሂ ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ ፣የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ መልካሙ ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕ/ር ነፃነት ወርቅነህ ፣ በጤና ሚኒስተር የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አባስ ሐሰን ፣ የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ ፣ እንዲሁም የጤና ሙያ ማህበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች፣ጥሪ የተደረገላቸው የላንድማርክ ሆስፒታል ሰራተኞችና ታካሚዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ ተቋሙ ለአስተማማኝ የህክምና ተግባራት እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት አፅንኦት ሰጥቶ በመስራት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት እየተካሄደ ያለውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት የአለም አቀፍ የታካሚ ደህንነት መስፈርቶችን ባማከለ መልኩ ለጤና አጠባበቅ ልህቀት ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጡ ገልፀዋል ። የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ የታካሚዎችን ደህነነት ለማሳለጥና የጤና አጠባበቅ አሰጣጥን ለመምራት የአለም አቀፍ የደህንነት ደረጃዎች እና መመዘኛዎች ያለውን ጠቀሜታ አስምረውበታል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ወክለው የተገኙት አቶ መልካሙ ጥሩነህ በከተማ አስተዳደሩ የታካሚዎች ደህንነት ማስጠበቅ እርምጃዎች አፈጻጸም ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አቡዱላሂ በበኩላቸው መንግስት ለታካሚዎች ደህንነት የሚሰጠውን ትኩረት እንደ ሀገራዊ የጤና እንክብካቤ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አረጋግጠዋል።
በዝግጅቱ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች መልአክት ፣ የሰራተኞች ቁርጠኝነት እና የታዩ የታካሚ ምስክርነቶችን ጨምሮ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለታካሚ ተኮር እንክብካቤ ያለውን ሁለንተናዊ አቀራረብ አጉልተዋል።
በመጨረሻም የሆስፒታሉን የታካሚ ደህንነት-ተኮር መሠረተ ልማት እና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በማየት የጨቅላ ህፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ፣ የቀዶ ህክምና ክፍል ፣የኩላሊት እጥበት ፣ የምግብ እና የልብስ ማጠቢያ አገልግሎቶችን ጨምሮ የሆስፒታል ማስፋፊያ ስራ ጎብኝተዋል። ዝግጅቱ የታካሚ ደህንነትን በሚመለከት የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን በመጎብኘት ተጠናቋል።
#worldpatientsafetyday #patientsafety #landmark #landmarkhospital #maternalandchildhealth

Sponsored by
Surafel
Comments