♦" ሦስት ሀገር ሆነን ነው የሄድነው ። አንተዋወቅም ። "
አትሌት ሠለሞን ባረጋ
#ethiopia | ኢትዮጵያ በቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ34 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ወርቅ ሜዳልያ ማጠናቀቋን ተከትሎ፣ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለውድቀቱ ዋነኛ ምክንያት የነበረውን የውስጥ ችግር በዝርዝር አጋልጧል። ሰለሞን ከ"ኢትዮ ራነርስ" ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ፣ በቡድኑ ውስጥ የነበረው "አብሮ አለመስራት" እና የዝግጅት ክፍተቶች ለውጤቱ መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆናቸውን በምሬት ተናግሯል።
"ትልቁ ችግራችን እና የውጤት መጥፋት ምክንያት አብሮ አለመስራታችን ነው" ያለው ሰለሞን፣ በ10,000 ሜትር ውድድር ላይ ከበሪሁ አረጋዊ እና ከዮሚፍ ቀጀልቻ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሲገልጽ "ሶስታችን ሶስት ሀገር ሆነን ነው የሄድነው" ብሏል።
"አንተዋወቅም፤ አያውቀኝም፤ አላውቀውም። ውድድሩ ስንገባ አልተነጋገርንም" ሲል በግልጽ ተናግሯል። ይህም በቡድን መሮጥ በሚጠይቅ የረጅም ርቀት ውድድር ላይ አትሌቶቹ ምንም አይነት የጋራ ስልት እንዳልነበራቸው ያሳያል።
ሰለሞን የፌዴሬሽኑን የዝግጅት ሂደትም በጽኑ ተችቷል። "ሆቴል መግባታችን ትልቁ ዓላማው አብሮ ለመስራት ነው" ያለው አትሌቱ፣ ነገር ግን አሰልጣኞቻቸው ከእነሱ ጋር እንዳልነበሩ እና የጋራ የልምምድ እቅድ እንዳልነበራቸው ገልጿል።
"ቶኪዮ ሆነን እኮ ትሬኒንግ በራሳችን እንደፈለግን ነው የምንወጣው። ማንም የሚያዝ፣ ማንም የሚከታተል የለም" በማለት በሻምፒዮናው ወቅት እንኳን የነበረውን የቁጥጥር መላላት አጋልጧል።
አትሌቶቹ በቀደሙት ውድድሮች (ለምሳሌ ኦሎምፒክ) ይቀርብባቸው የነበረውን ትችት በመስጋት በውድድሩ ወቅት ውሳኔ ለመውሰድ እንደተቸገሩ ሰለሞን ተናግሯል። "ትላንት የተወቀስንበትን እናውቃለን፤ ያንን እያሰብክ ገብተህ እንደገና ስህተት እሰራለሁ ብለህ ትጠነቀቃለህ" ብሏል። ሰለሞን በቀጣይ ሀገሩን ወክሎ ሲሮጥ "ነገሮች ካልተስተካከሉ በቀር" በዚህ መልኩ እንደማይቀጥል ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፏል።
የአትሌት ሰለሞን ቃለ-መጠይቅ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውድቀት ከግለሰብ አትሌቶች ብቃት በላይ የሆነ የቡድን ስራ፣ የዝግጅት እና የአመራር ችግር ውጤት መሆኑን ያጋለጠ ነው። ፌዴሬሽኑ በቀጣይ እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ምን አይነት እርምጃ ይወስዳል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።
#zehabesha

11 months ago