22 days ago
አለምን የሚያሽከረክሩት ባለሀብቶች ከ3000 አይበልጡም ተባለ
#ethiopia | በአለም አቀፍ ደረጃ የቢሊየነሮች ቁጥር ባለፉት ጥቂት አመታት ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በተፈጠረው ፈጠራ እና በዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያ መጨመር ምክንያት የበርካታ ግለሰቦች የሀብት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል።
በአሜሪካ እና በቻይና የሚገኙ ቢሊየነሮች አሁንም የአለምን የሀብት አቅጣጫ በመቆጣጠር ላይ ቢሆኑም በአዳጊ ሀገራት የቢሊየነሮች ቁጥር መጨመር አዲስ የኢኮኖሚ ተለዋዋጭነትን እየፈጠረ ይገኛል።
ሆኖም ይህ የሀብት ክምችት በትንሽ ግለሰቦች እጅ መሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የሀብት ክፍፍልን በተመለከተ ክርክሮችን እያነሳ ነው።
በጾታ ረገድ ሴት ቢሊየነሮች ቁጥር በየአመቱ መጠነኛ እድገት እያሳየ ቢሆንም በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው የሀብት ልዩነት አሁንም ሰፊ ነው።
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በሴቶች የሚመሩ ስራ ፈጣሪዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም የቢሊየነር ደረጃ ላይ ለመድረስ አሁንም ብዙ ይቀራል ይላሉ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ የቢሊየነሮች ሀብት መጨመር ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ቢኖረውም አሁን ያለው የሀብት ክፍፍል አለመመጣጠን ለቀጣይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መረጋጋት ፈተና ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldrichestpeople #americachinaindia #forbesmagazinenews

Comments