4 months ago
ቱርክ በሶማሊያ የባህር ክልል የነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር ነው
#ethiopia | በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰውን ስትራቴጂካዊ ስምምነት ተከትሎ፣ የቀጠናውን የኢነርጂ ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የነዳጅ ቁፋሮ በይፋ ሊጀመር ነው።
“ቻግሪ ቤይ” መርከብ፦ ግዙፏ የቱርክ የነዳጅ ቁፋሮ መርከብ የ45 ቀናት የባህር ጉዞዋን አጠናቅቃ በመጪው አርብ መቃዲሾ ትደርሳለች።
የመርከቧ ስራዋን የምትጀምረው “ኩራድ-1” በተሰኘው ጥልቅ የባህር ውስጥ የነዳጅ ጉድጓድ ላይ ይሆናል።
በ2024 በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈረመው ስምምነት መሰረት፣ በ16,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ያረፉ ሶስት ዋና ዋና ብሎኮች የፍለጋ ስራ ይካሄድባቸዋል።
ይህ ፕሮጀክት ለሶማሊያ አዲስ የኢኮኖሚ ምንጭ ከመሆን ባለፈ፣ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፅዕኖ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በተለይ በቀይ ባህርና በሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ያለውን የሀይል ሚዛን ሊቀይረው እንደሚችል ተገምቷል።
#getu #turkeysomalia #oilexploration #chagribey #energygeopolitics #hornofafrica #mogadishu #blueeconomy #strategicpartnership #ቱርክ #ሶማሊያ #ነዳጅ #ኢነርጂ #አፍሪካቀንድ #ጌጡተመስገን #getutemesge

6 months ago
"ቱርክ በሶማሊያ የጠፈር ጣቢያ ልትገነባ ነው"
የቱርክ የጦር ዝሆን በሞቃዲሾ የአንካራ ስትራቴጂካዊ ጥልቀት ወይንስ አዲስ የአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ ሽኩቻ?
[የኔታ ሚዲያ - ሞቃዲሾ]
በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ትኩሳት በጨመረበት በዚህ ወቅት ቱርክ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የጦር ታንኮችን እና የኤፍ-16 (F-16) ተዋጊ ጄቶችን ወደ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ማስገባቷ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ በክልሉ ያለውን ወታደራዊ ሚዛን ሊቀይር የሚችል ትልቅ ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።
ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የቱርክ የባህር ኃይል መርከቦች ግዙፍ የጦር ታንኮችን በሞቃዲሾ ወደብ ሲያራግፉ ታይተዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ የቱርክ የጦር ጄቶች በሶማሊያ ሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ መታየታቸው አንካራ በሶማሊያ ያላትን ወታደራዊ አሻራ ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሯን ማሳያ ሆኗል።
የየኔታ ሚዲያ የዜና ክፍል ጉዳዩን ሲመረምር የቱርክ ግዙፍ ወታደራዊ ዝግጅት ከሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ግቦች ጋር የተያያዘ መሆኑን ተረድቷል
ቱርክ በሶማሊያ ምድር ላይ የሳተላይት መተኮሻ (Spaceport) እና የሚሳኤል መፈተኛ ጣቢያ ለመገንባት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መድባለች። ይህንን ውድ ፕሮጀክት ከአል-ሸባብ ጥቃት ለመከላከል ታንክና ጄት የግድ አስፈላጊዎቿ ናቸው።
በቅርቡ ቱርክ በሶማሊያ ባህር ዳርቻ የነዳጅ ቁፋሮ ለመጀመር ከሞቃዲሾ ጋር ስምምነት ተፈራርማለች። ይህንን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስከበር የባህርና የየብስ ኃይሏን እያጠናከረች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ ቱርክ ከሶማሊያ ጎን በመቆም በባህር ዳርቻውና በየብሱ ላይ ያላትን ተጽዕኖ በማሳደግ የቀጠናው ቁልፍ ተዋናይ ለመሆን እየጣረች መሆኑ ይነገራል።
የአል-ሸባብ ስጋት እና የ"ጎርጎር" ኃይሎች
እንደ የደህንነት ምንጮች ገለጻ እነዚህ የቱርክ ጦር መሣሪያዎች በታችኛው ሸበሌ እና መካከለኛው ሸበሌ አካባቢ የአል-ሸባብን ይዞታዎች ለመደምሰስ ከሶማሊያ የ"ጎርጎር" (Gorgor) ልዩ ኃይሎች ጋር በቅንጅት ስራ ይጀምራሉ።
ይሁን እንጂ ኤፍ-16 ጄቶቹ በቱርክ መኮንኖች ቁጥጥር ስር መሆናቸው ጉዳዩ ከሽብርተኝነት መከላከል ባለፈ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ይዘት እንዳለው ያመላክታል።
የቱርክ ወታደራዊ መስፋፋት ለሶማሊያ መንግስት የደህንነት ዋስትና ቢሆንም ለጎረቤት ሀገራት ግን "አንካራ በአፍሪካ ቀንድ ምን እያሰበች ነው?" የሚል ስጋት ማጫሩ አልቀረም።
የየኔታ ሚዲያ ጉዳዩን በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል።
የኔታ ሚዲያ - እውነታውን ለናንተ!
#yenetamedia #turkeysomalia #hornofafrica

Comments