1 day ago
"ከ44 ሚሊዮን በላይ መምህራን ያስፈልጋሉ!"—ዩኔስኮ
#ethiopia | ዩኔስኮ "በ2030 ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ለማዳረስ እስከ 44 ሚሊዮን መምህራን ያስፈልጋሉ!" ብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንዳመለከተው በዓለም ዙሪያ ሁለንተናዊ የትምህርት ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ ከ44 ሚሊዮን በላይ መምህራን ያስፈልጋሉ ብሏል።
በዓለም ዙሪያ ከ90 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መምህራን በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ድረስ እያገለገሉ ይገኛሉም ብሏል።
ከዚህ ቁጥር ውስጥ ከ13 ሚሊዮን በላይ መምህራንና ፕሮፌሰሮች በኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች እያስተማሩ እንደሚገኙ ሪፖርቱ ገልጿል።
በዓለም ዙሪያ ያለው የመምህራን ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም አሁንም ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ለማዳረስ ከ44 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ መምህራን ያስፈልጋሉ።
የመምህራን እጥረቱ በዓለም ደረጃ እኩል ባይሆንም ከፍተኛው ጫና የሚገኘው በታዳጊ ሀገራት ላይ እንደሆነ አመላክቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚፈለገው 44 ሚሊዮን ተጨማሪ የመሠረታዊና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን መካከል 15 ሚሊዮኑ ወይም አንድ ሶስተኛው የሚያስፈልገው ከከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ነው ተብሏል።
ይህ ማለት የቀጣናው ሀገራት እስከ 2030 ድረስ ያለውን የልማት ግብ ለማሳካት አሁን ካላቸው የመምህራን ኃይል በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አካዳሚክ ሰራተኛ መቅጠር ማሰልጠንና በስራ ላይ ማቆየት ይጠበቅባቸዋል ሲል ድርጅቱ አመላክቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #unesco #teacher #worldteachersday #education #africa #teachershortage

Comments