1 month ago
ክህደት፣ መዘንጋት እና የከሸፈ ምኞት የኢትዮጵያ ጠላቶች የማይሳካ የሴራ ስሌት
********************
ኢትዮጵያ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ የተደቀኑባትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በህዝቧ ታሪካዊ ጽናት የማይበገር አንድነት እና በጠንካራ ዲፕሎማሲ እያሸነፈች ዛሬ ላይ የደረሰች ታላቅ ሀገር ነች።
የዚህችን ሀገር ገናና ታሪክ እና የማይናወጥ ህልውና ያልተረዱ ባላንጣዎቿ ዛሬም በሉዓላዊነቷ ላይ በከንቱ ቅዠት የታጀበ ሴራ ሲሸርቡ ይስተዋላል።
የሀገራችን ተቃዋሚዎችና ታሪካዊ ጠላቶች የሚከተሉት ስልት በሶስት ዋና ዋና የተሳሳቱ ስሌቶች ላይ የተመሰረተ ነው፤ እነሱም እውነታውን መካድ፣ ተቋማዊና ታሪካዊ አቅማችንን መዘንጋት እና የከሸፈ የከንቱ ምኞት እስረኛ መሆን ናቸው።
የመጀመሪያው የተሳሳተ ስሌታቸው ኢትዮጵያ በከርሰ ምድር እና በገጸ ምድር የታደለችውን ተፈጥሯዊ ሀብት የጂኦ-ፖለቲካዊ ብልጫ እና ለማንኛውም ወረራ የማይንበረከከውን የወርቅ ህዝቧን እውነተኛ አቅም ለመቀበል አይኖቻቸውን መሸፈናቸው ነው።
በካራማራ እና በዓድዋ የተመዘገበውን ድል እና የነጻነት ተጋድሎ እውነታ በካደ ቅዠት ውስጥ መኖርን መርጠዋል። ሁለተኛው ስህተታቸው ደግሞ የኢትዮጵያን የሺህ ዓመታት ተቋማዊ ልምድ፣ ምቹ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና ሀገሩን ለማስከበር እንደ እሳት የሚነደውን ወጣት ሀይል መዘንጋታቸው ነው። በጊዜያዊ ፈተናዎች የምትናወጥ ሀገር ስላልሆነች የኢትዮጵያን ውድቀት ማቀድ በፍጹም አይቻለውም።
ሶስተኛው እና መጨረሻው መገለጫቸው ደግሞ በሀገር ውስጥ ያሉ ባንዳዎችን በጥቅም በመግዛት ኢትዮጵያን ማዳከም ይቻላል ብሎ ማሰብ ሲሆን፤ ይህም ከእውነታው የራቀ፣ ጊዜ ያለፈበት እና መሬት ላይ ካለው የማይበገር የኢትዮጵያውያን አንድነትና እያደገ ከመጣው የመከላከያ አቅም ጋር በፍጹም የማይጣጣም ባዶ ህልም ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የትናንት ታሪኳን እና ፈተናዎቿን ወደ ትምህርት ቀይራ፣ ሉዓላዊነቷን በጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ የመከላከያ HAይል እንዲሁም በብልህ ዲፕሎማሲ እያረጋገጠች ትገኛለች፤ የትኛውም አካል ሊፈጥር የሚችለው ስጋት ሳይኖር ሉዓላዊነቷ በህዝቧ ታሪካዊ ክንድ ተከብሮና ተፈርቶ ይኖራል።
በበርከት ሽመልስ
#ethiopiansovereignty #adwalegacy #strongethiopia #nationalunity #ethiopiandiplomacy #ebc

Comments