7 days ago
ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ በወል ትርክት እና በጋራ ርዕይ ላይ ጠንክሮ መሥራት ይገባል
***********************
ኢትዮጵያውያን የብዝኃ ባህል፣ ቋንቋ እና ሃይማኖት ባለቤት መሆኗ የልዩነትና የግጭት ምንጭ ሳይሆን፤ የትብብር፣ የወንድማማችነትና አብሮ የማደግ መሠረት ተደርጎ መታየት እንዳለበት በአውሮፓ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አስተባባሪ ኤፍሬም ዘውዱ ገለጹ።
ይህን እሳቤ ለማጠናከር የጋራ ተቋማትን እና የወል ማንነትን መገንባት እንደሚያስፈልግ የገለጹት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሮብሰን ባልቻ በበኩላቸው፣ ይህ የጋራ ማንነት ግንባታም የተለያዩ ባህሎች እና ማንነቶችን የኢትዮጵያውያን የጋራ ባህል አካል በማድረግ ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
በዚህ ረገድ የተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን እና ማንነታቸውን እንደጠበቁ በጋራ የሚሳተፉባቸው የባህል መድረኮች፣ ልዩነትን ወደ የወል ሀብት ለመቀየር የሚያግዙ አጋጣሚዎች መሆናቸውን አቶ ኤፍሬም እና መምህር ሮብሰን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አስተባባሪ አቶ ኤፍሬም በዚሁ ወቅት፥ በልዩነቶች ላይ ያተኮሩ ትርክቶችን ተከትሎ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በኃይል ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች ዘላቂ መፍትሄ እንዳላመጡ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ያሉ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶችን ጨምሮ በታሪክ ሂደት የተፈጠሩ የዘመናት ቅራኔዎችን በተለያየ ጊዜ እና መንገድ በውይይት እየፈቱ መሄድ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሮብሰን ባልቻ በበኩላቸው፥ በብሔራዊ ጥቅምና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መሰባሰብ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፤ በጋራ ሀገር፣ በወል ትርክት እና በጋራ ርዕይ ላይ ጠንክሮ መሥራት ብሔራዊ መግባባትን እና ሀገራዊ አንድነትን ያጠናክራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደትም የጋራ ትርክትን ለመገንባት ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ መሆኑን በማንሳት፣ ሥር የሰደዱ ችግሮችን በማከምና የጋራ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት በመፍጠር ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ውይይት የማይተካ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የሀገራችንን እምቅ ሀብቶች በሚገባ በመጠቀም የበለጸገች እና የተከበረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የውስጥ ልዩነቶችን በውይይት እየፈቱ ተቀራርቦ በጋራ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ከጠንካራ ተቋማት ግንባታ ጎን ለጎን አሰባሳቢ ትርክቶችን ማጉላት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ፣ የተለያዩ ክልሎችና ማኅበረሰቦች በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የሚገናኙበትን መንገድ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በዚህ መንገድ ሕዝብን በብሔራዊ የጋራ ርዕይ ዙሪያ በማሰባሰብ፣ የኢትዮጵያን አንድነትና ልማት ማጠናከር እንዲሁም ሁሉም ዜጎች ተጠቃሚ የሆኑባትን የጋራ ሀገር መገንባት የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባው ገልጸዋል።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #peaceanddialogue #nationalconsensus #sharedidentity #nationalunity #ethiopiandiaspora #ebc

Comments