1 month ago
የሕይወት ጥራትን እና የዜጎችን ክብር ከፍ እያደረገ ያለው ራዕይ
*******************
በኢትዮጵያ በከተሞች አካባቢ የተጀመሩት አመርቂ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አሁን ላይ መልክና ቅርጻቸውን አስፍተው ወደ ገጠር መንደሮች በስፋት እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።
የገጠሩን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተጀመረው ይህ ልማት ወደ ገጠር መንደሮች በስፋት ዘልቋል።
በሀገራችን የተመዘገቡትን ታላላቅ የልማት ተሞክሮዎች መነሻ በማድረግ የተጀመረው ይህ የገጠር ኮሪደር ልማት የሀገራችንን ዕድገት ሚዛናዊ ለማድረግ ያለመ ነው።
ይህ አዲስ ንቅናቄ ከተማን ብቻ ሳይሆን የገጠሩንም ማኅበረሰብ ያማከለ ዘመናዊ የኑሮ ዘይቤ ለመፍጠር የታለመ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
ፕሮጀክቱ እያንዳንዱን ዜጋ ማዕከል ያደረገ ሰው ተኮር ልማት ማሳያ መሆኑንም በአብነት የተገነቡት የገጠር መንደሮች አረጋግጠዋል።
በዚህም ንጹሕ የመጠጥ ውኃን፣ መብራትን፣ ጤናን እና ትምህርትን ወደ አርሶ አደሩ ደጃፍ በማምጣት የሕይወት ጥራትን እና የዜጎችን ክብር ከፍ ያደርጋል።
ይህ ፕሮጀክት በመንግሥት በጀት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን፣ ባለፉት ዓመታት በትጋት ሲገነባ የቆየው የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እና የሕዝብ አጋርነት ፍሬ ነው።
ወጣቶች፣ ባለሀብቶች እና ባለሙያዎች ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን በበጎ ፈቃደኝነት በማስተባበር የገጠር መንደሮችን ገጽታ በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየሩ ይገኛሉ።
ልማቱ ከአረንጓዴ ዐሻራ፣ ከሌማት ትሩፋት እና ከግብርና ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ነው።
ይህ ደግሞ አርሶ አደሩ ምርቱን በዘመናዊ መንገድ እንዲያመርት እና በመኖሪያ መንደሩም እንደ ከተማው ሁሉ ምቹና ዘመናዊ ኑሮን እንዲለማመድ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።
የገጠር ኮሪደር ልማት፣ ባለፉት ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት ከተከናወኑት አበረታች ሥራዎች ጋር ተዳምሮ፣ የተጀመረው ልማት ለእያንዳንዱ ዜጋ ተደራሽ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሕያው ምስክር ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #ruralcorridordevelopment #voluntarismethiopia #ruralmodernization

የኢትዮጵያ የገጠር ኮሪደር ልማትና የአርሶ አደሩ ሁለንተናዊ የኑሮ ሽግግር
******************
የመደመር መንግሥት በከተሞች የጀመረውን ውጤታማ የኮሪደር ልማት ስኬቶች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ በማስፋፋት፣ የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየር የሚያስችል ታላቅ ሀገራዊ የልማት ሪፎርም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነትና አነሳሽነት ተግባራዊ በማድረግ በየክልሎቹ አመርቂ ውጤቶችን እያሳየ ይገኛል።
ይህ ስትራቴጂካዊ ንቅናቄ በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የዕድገት ልዩነት በማጥበብ የዘላቂ ብልጽግናን መሠረት ለመጣል ያለመ ነው።
የጥንታዊ ሥልጣኔ የዘመናት ታሪካዊ ክብር ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ የትናንቱን የአክሱም ሐውልቶች ዘመን አይሽሬ የኢንጂነሪንግ ጥበብ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና የጀጎል ግንብ የኪነ-ሕንጻ ምጥቀት ከነገው የብልጽግና ተስፋ ጋር በማገመድ፣ አቅዶ የመፈጸም ባህልን በተጨባጭ ምድር ላይ እያረጋገጠችና ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የታሪክ አሻራዋን እያሳረፈች ትገኛለች።
ይህ የገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት መሠረተ ልማትን ከማዘመን ባለፈ፣ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ አበይት ሥራዎችን በተጨባጭ መሬት ላይ ማሳየት የጀመረ የመደመር መንግሥት ቁልፍ የለውጥ እሳቤ ነው። ልማቱ የከተማ ውበትና የኮሪደር ልማት ስኬቶችን ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ በማስፋፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በሌማት ትሩፋት የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ እየሠራ ይገኛል።
ልማቱ የገጠር ነዋሪዎችን ከተበታተነ አሰፋፈር ወደ ተቀናጁ የገጠር መንደሮች በማምጣት ንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ መብራት፣ ጤና እና ትምህርት ቤት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፤ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማት አካባቢውን ለቱሪዝምና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ማዕከልነት እያሸጋገረው ይገኛል።
ቀደም ሲል የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ረጅም ሰዓታት በእግር ይጓዙ የነበሩ የገጠር መንደሮች፣ አሁን ላይ ደረጃቸውን በጠበቁ የጠጠርና የአስፋልት መንገዶች መገናኘት ችለዋል።
በዚህም በእናቶችና ሕፃናት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ መሻሻል የተፈጠረ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የገጠር አባወራዎች የንጹሕ መጠጥ ውኃ ማግኘት ችለዋል። በተጨማሪም አማራጭ የኢነርጂ እና የፀሐይ ብርሃን መብራቶች በየመንደሮቹ በመስፋፋታቸው የገጠሩን የምሽት ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመቀየር ላይ ይገኛል።
ይህ ስትራቴጂካዊ የልማት ስልት አነስተኛ ወጪ በሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኑ ግብዓቶች የሚገነቡ፣ ነገር ግን ምቹና ሞዴል በሆኑ መኖሪያ ቤቶች የአርሶ አደሮችን ሕይወት የሚለውጥ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዘመናዊ የእንስሳት ማደሪያዎች፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እና ባዮ ጋዝን በማሟላት ለሕይወት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ያስችላል።
ከዚህ ጎን ለጎን የተተከሉ የፍራፍሬና የጓሮ አትክልቶችን ከንብ እርባታ፣ ከእንቁላል፣ ከወተትና ከሥጋ ምርት ጋር በማቀናጀት አርሶ አደሩ የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት እንዲኖረውና ምርታማነቱ አድጎ ለራሱ ፍጆታ ከመብቃቱ ባለፈ፣ ለገበያ በማቅረብ ገቢውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሳድግ ይረዳል።
ይህ የመሠረተ ልማትና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ለልጆች ትምህርትና ለቤተሰብ ዘመናዊ መረጃ ተደራሽነት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፤ በገጠር የተሻለ የኑሮ ሁኔታ በመፈጠሩ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የገጠር ኮሪደር ልማት ተራ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሳይሆን የኢትዮጵያን ገጠር መልክ የሚቀይር የትውልድ ፕሮጀክት በመሆኑ፣ የተጀመረው ዘላቂ ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ይበልጥ እንዲያሳድግ አመራሩ፣ አርሶ አደሩ እና ባለሀብቶች በጋራና በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል።
በብሌን ደምበሎ
#ebc #ethiopia #ruralcorridordevelopment #ruraldevelopment #infrastructure

Comments