የሕይወት ጥራትን እና የዜጎችን ክብር ከፍ እያደረገ ያለው ራዕይ
*******************
በኢትዮጵያ በከተሞች አካባቢ የተጀመሩት አመርቂ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አሁን ላይ መልክና ቅርጻቸውን አስፍተው ወደ ገጠር መንደሮች በስፋት እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።
የገጠሩን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተጀመረው ይህ ልማት ወደ ገጠር መንደሮች በስፋት ዘልቋል።
በሀገራችን የተመዘገቡትን ታላላቅ የልማት ተሞክሮዎች መነሻ በማድረግ የተጀመረው ይህ የገጠር ኮሪደር ልማት የሀገራችንን ዕድገት ሚዛናዊ ለማድረግ ያለመ ነው።
ይህ አዲስ ንቅናቄ ከተማን ብቻ ሳይሆን የገጠሩንም ማኅበረሰብ ያማከለ ዘመናዊ የኑሮ ዘይቤ ለመፍጠር የታለመ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
ፕሮጀክቱ እያንዳንዱን ዜጋ ማዕከል ያደረገ ሰው ተኮር ልማት ማሳያ መሆኑንም በአብነት የተገነቡት የገጠር መንደሮች አረጋግጠዋል።
በዚህም ንጹሕ የመጠጥ ውኃን፣ መብራትን፣ ጤናን እና ትምህርትን ወደ አርሶ አደሩ ደጃፍ በማምጣት የሕይወት ጥራትን እና የዜጎችን ክብር ከፍ ያደርጋል።
ይህ ፕሮጀክት በመንግሥት በጀት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን፣ ባለፉት ዓመታት በትጋት ሲገነባ የቆየው የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እና የሕዝብ አጋርነት ፍሬ ነው።
ወጣቶች፣ ባለሀብቶች እና ባለሙያዎች ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን በበጎ ፈቃደኝነት በማስተባበር የገጠር መንደሮችን ገጽታ በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየሩ ይገኛሉ።
ልማቱ ከአረንጓዴ ዐሻራ፣ ከሌማት ትሩፋት እና ከግብርና ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ነው።
ይህ ደግሞ አርሶ አደሩ ምርቱን በዘመናዊ መንገድ እንዲያመርት እና በመኖሪያ መንደሩም እንደ ከተማው ሁሉ ምቹና ዘመናዊ ኑሮን እንዲለማመድ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።
የገጠር ኮሪደር ልማት፣ ባለፉት ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት ከተከናወኑት አበረታች ሥራዎች ጋር ተዳምሮ፣ የተጀመረው ልማት ለእያንዳንዱ ዜጋ ተደራሽ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሕያው ምስክር ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #ruralcorridordevelopment #voluntarismethiopia #ruralmodernization

1 month ago