1 month ago
"ሜሲ" የሚለው የስም መጠርያ ለማንም እንዳይሰጥ!
#ethiopia | የሊዮኔል ሜሲ የትውልድ ከተማ የሆነችው ሮሳሪዮ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚለውን ስም እንዳይሰጡ ከለከለች።
በአርጀንቲናዋ ሮሳሪዮ ከተማ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚለውን ስም የመጀመሪያ ስም አድርገው እንዳይሰጡ መከልከሏ ተገለጸ።
አርጀንቲና "ሊዮኔል ሜሲ" የሚለውን ስም በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለማንም የማይሰጥ እና ወደፊትም የማይደገም ልዩ አድርጋዋለች።
በ2014 ከሮዛሪዮ ውጪ የሚኖር አንድ አባት ልጁን "ሜሲ ዳንኤል ቫሬላ" ብሎ ለመሰየም ልዩ ፈቃድ ካገኘ በኋላ ነበር ይህ ክልከላ የወጣው።
ይህንን ተከተሎ የሮሳሪዮ ከተማ ባለሥልጣናት ተመሳሳይ ነገር በከተማቸው መደበኛ በሆነ መንገድ የማይፈቀድ መሆኑን የሚገልጽ መመርያ ያወጡት።
ይህ ለእሱ ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት መግለጫ ነው ተብሏል።
በሜሲ በትውልድ ከተማ ሮዛሪዮ አካባቢ ግራ መጋባትን ለመቀነስ የሕፃናትን ስም "ሜሲ" ብሎ መሰየምን የሚከለክል ሕግ በ2014 ነበር ተደንግጎ የወጣው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #argentina #rosario #messi #football #name

የአስፈሪዉ ጊዜ የመጀመሪያዉ ደወል ዛሬ ተሰማ፤
እርሱ እንደ ልቤ የሚላት እና ሁሉ ነገሩንና ሁሉን ነገር ሰጥቷት እንኳን ገና ምና አድርጌልሽ የሚላትን ሀገሩን ዉብ መለያ ከዚህ በኋላ እንደማይለብስ ይፋ አደረገ።
እመኑኝ ይህ ዉሳኔ ዉስጤ ድረስ ገብቶ እየጎዳኝ ያለ ለመወሰን በጣም ከባዱ ዉሳኔ ሲሆን ገና ወደፊትም የሚጎዳኝ ነዉ ሲል እርሱነቱን ሽተዉ ከሀገር ሀገር የዞሩ ወዳጆቹን፣ አይናቸዉ እስኪጠፋ እና ጆሯቸዉ እስኪደማ ስለ እርሱ ሲሉ እንቅልፋቸዉንና እልፍ ተግባራትን የሰዉለትን እግር ኳስ አፍቃሪያን ልብ ቀጥ የሚያደርገዉን የመጀመሪያዉን ደወል አሰማ።
አዎ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ኩኩቲኒ ከዚህ በኋላ በአርጀንቲና መለያ ላንመለከተዉ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን አግልሏል።
በዚህ ዉብ ሰማያዉይ እና ነጭ መለያ ብዙ ታሟል፤ ብዙም ታምቷል፤ አንተ እኮ ስፔናዊ እና የባርሳ ብቻ ንጉስ ነህ ተብሎም በማራዶና እና ኬምፔስ ሚዛን ተመዝኖ ተዘልፏል። አብዝቶ ከሚወዳት ሀገሩ ገና በጠዋት ራሱን እስከ ማግለልም ደርሶ ነበር።
ከዚያ ሁሉ ህመም እና ሲቃ በኋላ ግን፤ እርሱ አዎ እርሱ በካታላን መንደር የከወናቸዉን ተዓምራት ወደ ሀገሩም አምጥቶ ከኮፓ እስከ ታማበት የአለም ዋንጫ ክብር አርጀንቲናዊያንን ጮቤ አስረግጧል። በእነ ማራዶና ትዝታ ሲቆዝሙ ለነበሩ የቼ ሰዎች ህልም ሚመስል ከፍታን ከአመት አመት በስኬት ባህር ላይ አስዋኝቶ አሳይቷቸዋል።
በመጨረሻም በአስፈሪዉ የመጀመሪያ ደወሉ እንዲህ አለ፤ ከዚህ በኋላ ልሰጣችሁ የምችለዉ የለምና ላለፉት 20 እና ከዚያ በላይ አመታት ለሰጣችሁኝ ጥልቅ ፍቅር አመሰግናለሁ አለ።
ያለፈዉ ትዉልድ እናንተ ማራዶናን አላያችሁም ፔሌንም አልተመለከታችሁም፤ ክራይፍና ጋሪንቻን፤ ዴስቲፋኖና ፑሽካሽንም አላጣጣማችሁም፤ ሰር ቦቢና ጆርጅ ቤስትን ለመመልከት አልታደላችሁም ሊለን ከዳዳዉ የምንመዘዉ የመጀመሪያዉ ካርዳችን እርሱ ነዉ፤ አዎ እርሱ።
ፒተር ድሩሪ በዉብ አንደበቱ እንደገለፀዉ ነዉ፤ Lionel Messi has conqured his final peak. Lionel Messi has shaken hands with paradise. The little boy from Rosario has pitched up in heaven. He climbs in to a galaxy of his own .
Mucha Gracias ኩኮ
Via: Newayemariam

Comments