14 days ago
ላንድማርክ ሆስፒታል የታካሚዎች ደህንነት ቀንን አከበረ
#ethiopia | ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀንን ለ8ኛ ጊዜ አከበረ። የዘንድሮው መርሃ ግብር በተለይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ለሚጠቁ ታካሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምናና እንክብካቤ ማረጋገጥ ላይ አተኩሯል።
የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል መስራች ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከ11 ታካሚዎች አንዱ በሕክምና ሂደት ወቅት ከደህንነት ጉድለት ጋር በተያያዘ ለጉዳት ሊዳረግ እንደሚችል የዓለም አቀፍ መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። በታዳጊ ሀገራት ደግሞ ችግሩ የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና ለማረጋገጥ የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች ጥራት፣ የሕክምና መሣሪያዎች ተገቢ አጠቃቀምና ጥገና፣ የጤና ባለሙያዎች ብቃትና ሥልጠና እንዲሁም የጤና ተቋማት የአሠራር ሥርዓት ወሳኝ መሆናቸውን ፕሮፌሰር ከበደ አስረድተዋል። የታካሚዎች ደህንነት እንዲረጋገጥም የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች፣ ቤተሰቦች፣ ማህበረሰብና መንግሥት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በዘንድሮው የታካሚዎች ደህንነት ቀን ትኩረት የተሰጠው በተለይ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታና ሥር የሰደዱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ጨምሮ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚጠቁ ታካሚዎች የሚያገኙት ሕክምና አስተማማኝ እንዲሆን ነው። በጊዜ መመርመር፣ ተገቢ ሕክምና መስጠትና ቀጣይነት ያለው ክትትል ማድረግ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ መሆኑ ተጠቁሟል።
የታካሚዎችና የቤተሰቦቻቸው ተወካይ ኢንጂነር ፈቲያ መሐመድ በበኩላቸው፣ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ከታካሚው ጋር በቅርበት ስለሚገኙ በሕክምና ሂደት ውስጥ ቀድመው ሊያስተውሏቸው የሚችሉ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል። የታካሚዎችንና የቤተሰቦችን ድምፅ መስማትና ማክበር የታካሚዎችን ደህንነት ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በዕለቱ ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የሚደረገውን ሕክምና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የጋራ የትብብር ስምምነት ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል።
የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀን ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን፣ ዓላማው በሕክምና ሂደት የታካሚዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ ግንዛቤ ማሳደግና በዘርፉ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ነው።
#patientsafety #safecare
#worldpatientsafetyday #safehealthcare #healthcaresafety #patientcare #healthcarequality #healthforall

Comments