2 months ago
ፕሬዝዳንቱ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ሆነው ቀረቡ!
#ethiopia | የፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ለ2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ሆነው መቅረባቸው ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቷል።
በኖርዌይ ኦስሎ ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖት ጥናት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ዳግ ኦይስቴይን ኤንድስዮ ጥቆማውን በጥር ወር ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፕሮፌሰሩ ጥቆማውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት የዩክሬን ሕዝብ ከ2014 ጀምሮ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ከ2019 ጀምሮ አገራቸውን ከውጭ ወረራ በመጠበቅ ያሳዩት ፅናት ለዚህ ሽልማት እጩ እንዲሆኑ እረድቷቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ዜሌኒስኪ የራሳቸውን ሰላም ብቻ ሳይሆን የመላው አውሮፓን ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ እሴቶች ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ገልጸዋል።
ለ2026ቱ የኖቤል የሰላም ሽልማት በርካታ እጩዎች የቀረቡ ሲሆን የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ አሸናፊውን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #ukraine #russia #usa #europe #war #nobel #peace #prize

1 year ago
የሰላም ሽልማት ለእኔ ካልተሰጠ ለአሜሪካ ትልቅ ስድብ ነው !/ ትራምፕ /
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በሩሲያና በዪክሬን መካከል ያለውን ጦርነት እንዲቆም አደርጋለሁ ቢሉም እስካሁንም ያልተሳካላቸው ከቻይ ጋር የኢኮኖሚ ከሰሜን ኮርያ ከኢራን እና ሌሎች ግጭቶች ጀርባ አሉ የሚል ሀሜት የሚቀርብባቸው ዶናልድ ትራምፕ ዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለእኔ ካልተሰጠ ለአሜሪካ ትልቅ ስድብ ነው ማለታቸው ተሰማ ።
ትራምፕ ማክሰኞ በኳንቲኮ ለሚገኙ ወታደራዊ መሪዎች ባደረጉት ንግግር የጋዛን ግጭት ለማስቆም ያቀደውን እቅድ በመጥቀስ "እኛ ለአለም ሰላም እየተጋን እንገኛለን ከሰባት በላይ አለም አቀፍ ግጭቶችን ለማስቆም ችያለሁ ስለዚህም የኖቤል ሽልማት ይገባኛል ማለታቸው ነዉ የተነገረው ።
የኖቤል ሽልማትን የማይረባ ነገር ላላደረገ ሰው ይሰጡታል። ስለ ዶናልድ ትራምፕ አእምሮ እና ጦርነቱን ለመፍታት ምን እንደወሰደ መጽሐፍ ለጻፈ ሰው ይሰጣሉ… የኖቤል ሽልማት ለፀሐፊዎች ያደላል ፣ አዎ ይገባኛል ።
አሜሪካ እንደዚህ ያለ ሽልማት ስለሚገባት አገሪቷ እንድታገኝ እፈልጋለሁ።
እስቲ አስቡት። ስለዚህ ይህ (የጋዛን ግጭት የማስቆም እቅድ) ከእኔ ዉጪ ማን ይሳካዋል ? ሕይወቴ በሙሉ የተመሰረተው በዚህ ላይ ነው” የኖቤል የሰላም ሽልማት ካልተሰጠኝ አሜሪካ ላይ ትልቅ ስድብ ነዉ ግን የሚሆነውን እናያለን ሲሉ ተናግረዋል ።
የኖብል ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በ1901 እ.ኤ.አ ሲሆን ሽልማቱም የተሰየመው Alfred Nobel በተሰኘ እና በ1896 እ.ኤ.አ ሕይወቱ ያለፈ ሲውዲናዊ የኬሚስትሪ ባለሙያ እና ኢንጂነር የነበረው ከበርቴ ነጋዴ ሰው ስም እንደሆነ የሚነገርለት ሽልማቱ ሰላምን ጨምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰዎች የሚሰጥ እና ትልቅ አለም አቀፍ እውቅናን እና ተቀባይነትን ያገኘ ሽልማት ነው ።
በእስራኤል እና በሀማስ እንዲሁም በእስራኤል እና በኢራን መካከል የነበረው ግጭት እንዲቆም፤ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሆነው የማደራደር ተግባራት ላይ መሳተፋቸውን ጨምሮ ሰባት ጦርነቶች እንዳቆሙ የሚናገሩት ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዘንድሮው የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት እንደሚገባው ደጋግመው ገልፀዋል ።
ዶናልድ ትራምፕ በብዙ ሀገራትና ቀጠናዎች ሰላም እንዲሰፍን ገንቢ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን እናዉቃለን ያሉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ጨምሮ በርካታ መሪዎች
የሰላም ኖቤል ሽልማት እጩ እንዲሆኑ ጥቆማ ማቅረባቸውን ገልፀዋል ።
ለዘገባዉ ዘኢንዲያን ፕረስ ቴሌግራፍ ሲቢሲ የዜና ወኪሎች ተጠቅመናል ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments