6 months ago
የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ የጸሎት መርሐ-ግብር ተዘጋጀ
📌 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጸሎት ይደረጋል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እና የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል በማስመልከት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማኞች የሚሳተፉበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በመጪው እሁድ ሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በይፋ አስታውቋል።
ይህ ታላቅ መድረክ ከሃይማኖታዊ ስነ-ሥርዓት ባለፈ፣ መጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በታማኝነት እንዲጠናቀቅ "የአደባባይ ጸሎት" የሚደረግበት ልዩ ሀገራዊ መርሃ-ግብር እንደሆነም በሰፊው ተገልጿል።
ህብረቱ በ1968 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የመጀመሪያውን ጉባኤ ካካሄደበት ጊዜ አንስቶ ያለፈባቸውን አምስት አስርት ዓመታት ለመዘከር ልዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ የዕለቱ ዝግጅትም የዚህ ታሪካዊ ጉዞና የኢዮቤልዩ በዓል አንድ አካል ተደርጎ ተወስዷል።
የህብረቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ደረጀ ታፈሰ እንደገለጹት፣ ዋናው የኢዮቤልዩ በዓል በሐምሌ ወር የሚከበር ቢሆንም፣ በትንሳኤ በዓል ዕለት የሚከናወነው ጉባኤ የህብረቱን ምስረታ የሚዘክሩ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽኖች እና የታሪክ ምስክርነቶች የሚቀርቡበት ይሆናል።
ፓስተር ደረጀ ቤተክርስቲያን ለሀገር መረጋጋትና ለአንድነት ያላትን ኃላፊነት በይፋ እንደምትወጣ አረጋግጠው፣ በሃይማኖትና በብሔር ስም የሚነሱ የመለያየት አስተምህሮዎችን ህብረቱ በጽኑ እንደሚቃወም ገልጸዋል።
እውነተኛው የወንጌል አስተምህሮ ሰላምና ፍቅር እንጂ መቃቃር እንዳልሆነ በመጠቆም፣ በመጪው ምርጫ ዙሪያ አደባባይ ላይ የሚደረገው ጸሎት ለሀገር ትልቅ ሰላምን የሚያመጣ መሆኑን በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።
በተጨማሪም ህብረቱ "ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሪ በማድረግ፣ በዕለቱ የተቸገሩ ወገኖችን የመርዳትና የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል። ይህ ማህበራዊ አገልግሎት ህብረቱ በየዓመቱ በታላላቅ በዓላት የሚያከናውነው ልማድ ሲሆን፣ ዘንድሮም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።
ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስቴዲየም በሚካሄደው በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ፣ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማኞች ተገኝተው የትንሳኤውን በዓል በጋራ እንዲያከብሩና ስለ ሀገር ሰላም እንዲጸልዩ ጥሪ ተላልፏል።
#ethiopia #easterinethiopia #evangelicalchurchesfellowship #nationalprayer #goldenjubilee #addisababastadium #peaceandunity #resurrectionpower

8 months ago
ሀገር አቀፍ የጾምና ጸሎት ጥሪ አዋጅ ቀረበ
📍 ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 የጾም ወቅት ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ለሚገኙ ምዕመናን ሁሉ የጾምና ጸሎት ጥሪ አዋጅ ቀርቦአል።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሰጡት መግለጫ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአንድ ወር የሚቆይ ጾም ጸሎት ማወጇን አስታውቀዋል።
መግለጫውን የሰጡት የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ ምክትል ፕሬዚደንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፣ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ተመስገን አዋኖ እንዲሁም የስራ አመራር ቦርድ ጸሐፊ መጋቢ የኋላእሸት ሙኩሉ በጋራ በመሆን ነበር።
የመግለጫውን የመጀመሪያ ክፍል ያቀረቡት
የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደነት መጋቢ ላኮ በዳሶ የቤተ ክርስቲያኒቱ የስራ አመራር ቦርድ ከጥር 21 እስከ ጥር 23 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ፣ አገልጋዮች እና ምዕመናን ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 ድረስ ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እና ስለሀገር እንዲጸልዩ እና እንዲጾሙ መወሰኑን አስታውቀዋል።
ስለ ጾምና ጸሎቱ አጠቃላይ ይዘት ያቀረቡት የቤተ ክርስቲያኒቱ የስራ አመራር ቦርድ ጸሃፊ የሆኑት መጋቢ የኋላእሸት ሙኩሉ ቤተ እምነቷን እና ሀገሪቷን አስመልክቶ የንስሃ ፣ የምስጋናና እና የምልጃ ጸሎቶች እንደሚደረጉ ጠቅሰዋል።
በየሳምንቱም ሳምንታዊ የጸሎት ርዕሶች በቤተ ክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ እንደሚለቀቁም ተናግረዋል።
#fullgospelbelieverschurch #nationalprayer #fastingandprayer #unityinprayer #ethiopianchurch #intercession #faithingod #prayerfornation

Comments