8 months ago
ሀገር አቀፍ የጾምና ጸሎት ጥሪ አዋጅ ቀረበ
📍 ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 የጾም ወቅት ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ለሚገኙ ምዕመናን ሁሉ የጾምና ጸሎት ጥሪ አዋጅ ቀርቦአል።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሰጡት መግለጫ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአንድ ወር የሚቆይ ጾም ጸሎት ማወጇን አስታውቀዋል።
መግለጫውን የሰጡት የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ ምክትል ፕሬዚደንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፣ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ተመስገን አዋኖ እንዲሁም የስራ አመራር ቦርድ ጸሐፊ መጋቢ የኋላእሸት ሙኩሉ በጋራ በመሆን ነበር።
የመግለጫውን የመጀመሪያ ክፍል ያቀረቡት
የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደነት መጋቢ ላኮ በዳሶ የቤተ ክርስቲያኒቱ የስራ አመራር ቦርድ ከጥር 21 እስከ ጥር 23 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ፣ አገልጋዮች እና ምዕመናን ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 ድረስ ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እና ስለሀገር እንዲጸልዩ እና እንዲጾሙ መወሰኑን አስታውቀዋል።
ስለ ጾምና ጸሎቱ አጠቃላይ ይዘት ያቀረቡት የቤተ ክርስቲያኒቱ የስራ አመራር ቦርድ ጸሃፊ የሆኑት መጋቢ የኋላእሸት ሙኩሉ ቤተ እምነቷን እና ሀገሪቷን አስመልክቶ የንስሃ ፣ የምስጋናና እና የምልጃ ጸሎቶች እንደሚደረጉ ጠቅሰዋል።
በየሳምንቱም ሳምንታዊ የጸሎት ርዕሶች በቤተ ክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ እንደሚለቀቁም ተናግረዋል።
#fullgospelbelieverschurch #nationalprayer #fastingandprayer #unityinprayer #ethiopianchurch #intercession #faithingod #prayerfornation

Comments