1 month ago
1501u129bu12cd u12e8u1218u12cdu120au12f5 u1260u12d3u120d u12a0u12a8u1263u1260u122d
#mawlidalnabi #prophetmuhammad #mawlid1501 #ethiopi ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
1501ኛው የመውሊድ በዓል አከባበር
#mawlidalnabi #prophetmuhammad #mawlid1501 #ethiopi
1 month ago
1501ኛው የመውሊድ በዓል የእዝነት እና የብርሃን ድምቀትና መንፈሳዊ ፍቅር
******************
አላህ ለዓለማት እዝነት አድርጎ የላካቸውን የታላቁ ነቢይ መሐመድን (ሰዐወ) ልደት የሚዘክረው 1 ሺህ 501ኛው የመውሊድ በዓል በሙስሊም ማኅበረሰቦች ዘንድ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት፣ በሶላት፣ በዱዓ እና በበጎ አድራጎት ሥራዎች እየተከበረ ይገኛል።
ይህ ታላቅ ዕለት የነቢዩን (ሰዐወ) መልካም ምግባር፣ ትህትና፣ ፍቅርና አስተምህሮ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ እንዴት ልንተገብረው እንደሚገባ የምናስብበትና ራሳችንን የምንፈትሽበት አጋጣሚ ነው።
ነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) በምድር ላይ የነበራቸው ተልዕኮ የሰውን ልጅ ከነበረበት የጨለማ ዘመን ወደ እውቀትና እምነት ብርሃን፣ ከበደልና ከአድልዎ ወደ ፍትህና እኩልነት ማሸጋገር ሲሆን፤ የሰው ልጅ በዘሩ፣ በቆዳ ቀለሙና በሀብቱ ሳይሆን በትቅዋውና በመልካም ምግባሩ ብቻ የሚመዘንበትን መለኪያ አስተምረዋል።
የመውሊድ በዓል ይህንን ታላቅ እዝነት የምናስታውስበት፣ የነቢዩን (ሰዐወ) ፍቅር በልባችን የምናድስበትና የመቻቻልን እሴት ለዓለም የምናሳይበት ወቅት ነው።
በመሆኑም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በመስጂዶች በጋራ ተሰብስቦ የነቢዩን (ሰዐወ) ታሪክ የሚያወድሱ መንዙማዎችን እና ሶላቶችን የሚያደርስበት፣ የሰላምና የአንድነት መልዕክት የሚያስተላልፍበት ሆኗል።
ከዚህ ባለፈም የነቢዩን (ሰዐወ) አስተምህሮ መሠረት በማድረግ የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የጎደላቸውንና ወላጅ የሌላቸውን ህጻናት እንዲሁም አቅመ-ደካሞችን በመደገፍና በሰዎች መካከል ያሉ ቅሬታዎችን በመፍታት ወንድማማችነትን በማጠናከር የሚከበር ታላቅ እሴት ነው።
በዓሉን ስናከብር የነቢዩን (ሰዐወ) የሕይወት ታሪክ በጥልቀት ማወቅና ለተከታዩ ትውልድ ማስተላለፍ ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል።
የበዓሉን ደስታ ከጎረቤቶች እና ከአቅመ ደካሞች ጋር በማካፈል እውነተኛውን የእዝነት መንፈስ ማሳየት ይጠበቅብናል።
ከማንኛውም ጊዜ በላይ እርስ በእርስ በመከባበር፣ በመደጋገፍ እና አብሮነትን በማጠናከር የነቢዩን (ሰዐወ) የሰላምና የፍትህ አስተምህሮ በተግባር ማሳየት የሁላችንም ኃላፊነት ሲሆን፤ ይህ 1 ሺህ 501ኛው የመውሊድ በዓል ለሀገራችንና ለዓለም በሙሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የጤና ወቅት እንዲሆን እንመኛለን።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #mawlid #prophetmuhammad #mawlidalnabi #peaceandunity #ethiopia

የማህበራዊ ትስስር እና የአብሮነት ገመድን የሚያጠናክረው የመውሊድ በዓል
***********
ነገ በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት ቀን (መውሊድ) በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት፣ በፍቅር እና በደስታ በድምቀት ይከበራል።
በዓሉ የታላቁን ነቢይ ሕይወት፣ መልካም አርዓያነትና አስተምህሮ የምንዘክርበት ነው።
መንደሮች በመንዙማ (በነቢዩ ሙሐመድ ውዳሴ) ድምፅ ሲደምቁ፣ የመኖሪያ ቤቶች ደጃፎች በቡና እና በዕጣን መዓዛ ሲታወዱ፣ የደስታ መንፈስ እያንዳንዱን ማዕዘን ይሞላዋል።
በመስጂዶች፣ በታሪካዊ ሐድራዎች እና በመኖሪያ ቤቶች የነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ምጡቅ ስብዕና፣ ገድል፣ ፍቅርና እዝነት የሚዘክሩ መንዙማዎች (ውዳሴዎች) ይከናወናሉ።
በሀገራችን የመውሊድ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደጠበቀ፣ ከተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊ ትውፊቶች ጋር ተዋህዶ የሚከበርበት መንገድ ለየት ያለ ኅብረ-ብሔራዊ ውበትን አጎናፅፎታል።
ከሐረር ጀጎል ታሪካዊ ግንቦች እስከ ወሎ የእስልምና ትምህርት ማዕከላት፣ ከጅማና ባሌ ሐድራዎች እስከ አዲስ አበባ መስጂዶች በዓሉ በየአካባቢው በድምቀት ይከበራል።
በየመንደሩ የሚደረጉ የጋራ ማዕድ ዝግጅቶች እና መስተንግዶዎች የኢትዮጵያውያንን የቆየ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው።
መውሊድ ከመንፈሳዊነቱ በተጓዳኝ አቅመ-ደካሞችን በመደገፍና ማዕድ በማጋራት እንዲሁም የቲሞችን (ወላጅ አልባ ህፃናትን) በማስደሰት የማህበራዊ ትስስር እና የአብሮነት ገመድን እያጠናከረ ያለ ነው።
የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሰላም፣ የፍትህ እና የሰብዓዊነት አስተምህሮ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና አንድነት አስፈላጊ እሴት በመሆኑ፣ ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር ልዩነቶችን በመደማመጥና በምክክር በመሻገር ሊሆን ይገባል።
መልካም የመውሊድ በዓል!
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #mawlid #mawlidalnabi #peace #justice #mawlidmubarak #ebc

Sponsored by
Surafel
Comments