7 mins. ago
Join Ethiopian Aviation University and prepare for a bright future in your aviation career.
https://eau.edu.et/ #ethiopianaviationuniversity #ethiopianairlines

6 hours ago
Enjoy a 10% discount on flights from Entebbe to Ethiopian Airlines' global destinations! Don't miss out on this limited-time offer. Book your flight today!
https://www.ethiopianairli...
#ethiopianairlines #flightdeals
https://www.ethiopianairli...
#ethiopianairlines #flightdeals
9 hours ago
በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንዲቀርበለት የሚያዘው ደንብ በስራ ላይ ውሏል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ ያወጣው ደንብ ቁጥር 594/2018 በስራ ላይ ውሏል።
ደንቡ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ በሂደት እየቀነሰ የሚሄድ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚመደብበትን ሥርዓት ያካተተ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎቻቸውና ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻቸው በመነሳት በበጀታቸው በነፃነት እንዲጠቀሙና ተልዕኳቸውን በጥራት እንዲወጡ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ያስረዳል።
ደንቡ ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው ዓመታዊ የብሎክ ግራንት እንደ አግባብነቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል፣ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ነገር ግን የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው ማስተማሪያ ሆስፒታሎች አማካኝነት፣ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች እና በነፃ ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻልም ሊመደብ እንዲሚችል ይገልጻል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን የምርምርና ጥናት፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንስ ድጋፍ ሊመደብ እንደሚችል ተደንግጓል።
በዚህ ደንብ መሠረት አጠቃላይ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት ድልድል የግብዓት፣ የውጤትና የፍትሐዊነት መስፍርቶችን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ይህም
• የመማር-ማስተማር ሂደቱን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር፣
• የሳይንሳዊ ምርምር ውጤትና ተፅዕኖን፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም
• ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን እና የተቋማቱን መልክዓ-ምድራዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደርጋል።
ይህ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር እንደ አስፈላጊነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማጣጣም በየሁለት ዓመቱ ክለሳ ይደረግበታል።
በተለየ መልኩ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተደንግጓል።
ይህ ድጋፍ ሆስፒታሎቹ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶችና ተጠቃሚ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ሲሆን፤ ድልድሉም በሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ብዛት፣ የህክምና አልጋዎች ቁጥር፣ የአገልግሎቶቹ ውስብስብነት እንዲሁም ለመድኃኒትና ለአላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች የሚወጣውን ወጪ መሠረት በማድረግ ይወሰናል።
በዚህም ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገኘው ዓመታዊ ድጋፍ አጠቃላይ የመማር-ማስተማርና የምርምር በጀቱን እንዲሁም ለማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚመደበውን ልዩ በጀት በአንድ ላይ ያካተተ የተቀናጀ የብሎክ ግራንት ሆኖ ይቀርባል።
የበጀት ጥያቄ አቀራረብና አስተዳደርን በተመለከተ፣ ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የበጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት እና የተፈቀደው በጀትም በቀጥታ ወደ ተቋማቱ ፈሰስ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርም ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም ውል በመፈራረም በዓመት ሁለት ጊዜ ሁለንተናዊ ግምገማ እንደሚያካሂድ ተደንግጓል።
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዎቹ የብሎክ ግራንት ሒሳብ በፌደራል ዋና ኦዲተር እንደሚመረመርና የሒሳብ ሰነዶችም ቢያንስ ለአስር ዓመታት ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

ኢትዮጵያ ኤርትራን ወራር በመፈጸም የከሰሰች ሲሆን ወታደሮቿ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን ኢትዮጵያ አሳውቃለች።
እነዚህ የኤርትራ ኃይሎች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ ግዛት እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።
ለ ' ብሉምበርግ ' ቃላቸውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ፣ " በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የውጭ ኃይሎች በአስቸኳይ ሊወጡ ይገባል " ብለዋል።
በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ግዛት ሳይዘገዩ በፍጥነት ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

10 hours ago
" ከዚህ ቀደም በነበረ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለምናውቅ በቀላሉ ለመለየት ችለናል " - ነዋሪዎች
የ2013ቱን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ገብተው የነበሩትና ከዛ በኋላ የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ይዘው የሚገኙ የኤርትራ (ሻዕቢያ) ወታደሮች አሁን ላይ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው እየገቡ ናቸው።
ከህወሓት ጋር የተሰለፉት የሻዕቢያ ወታደሮች ትግራይ ክልል ውስጥ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።
ቢቢሲ ዛሬ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች ትግራይ ውስጥ ዘልቀው ገብተዋል።
" ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች ከረቡዕ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ በዓዲግራት በኩል ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በጭነት ተሽከርካሪዎችና በእግራቸው ሲያቋርጡ ተመልክተናል " ብለዋል።
ነዋሪዎች ከኤርትራ ድንበር 40 ኪሎ ሜትር የምትርቀውን ዓዲግራት ከተማን በማለፍ የኤርትራ ወታደሮች ወደ መቐለ አቅጣጫ ሲጓዙ ማየታቸውን ገልጸዋል።
" ወታደሮቹ በጭነት መኪኖችና በእግራቸው ወደ መቐለ መስመር ወዳለችው እዳጋ ሐሙስ አልፈው ሲሄዱ ተመልክተናል " ብለዋል።
በአካባቢው የትግራይም ሆነ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት አባላት ባለመኖራቸውና ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለሚያውቁ በቀላሉ ለመለየት እንደቻሉ ገልጸዋል።
ወታደሮቹ ከመኪና በተጨማሪ በእግርም የሚጓዙ ስለነበሩ ለመለየት ያልተቸገሩት ነዋሪዎቹ፣ ነጣ ያለ እና ቅጠልያ ወደታራዊ ልብስ የለበሱ ናቸው።
" መኪኖቻቸው ሲኖ የሚመስሉ የጭነት መኪኖች እና የኤርትራ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው ናቸው " ብለዋል።
በቀደሙት ቀናት ከኤርትራ ተነስተው በዛላምበሳ በኩል ፋጺ ወደሚባል አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን ሲሰሙ እንደነበርም አመልክተዋል። ዛሬ ደግሞ ዓዲግራትን ሲተልፉ ነበር።
ነዋሪዎቹ ወታደሮቹን ጭነው የገቡት የጭነት መኪኖች "በግምት ከ40 በላይ" እንደሚሆኑና በእግር ሲጓዙ የነበሩት "ብዙ" መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
አንድ የዓዲግራት ከተማ ባለሥልጣን ስማቸው ሳይጠቀስ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ወታሮች ለቀናት በአካባቢው እንደነበሩና " ሕዝቡ ስጋት እንደተፈጠረበት " ገልጸዋል።
አንድ የዐይን ምስክር ደግሞ " በትላልቅ የጭነት መኪኖች፣ በክፍት መኪኖች እና በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የኤርትራ ወታሮች ከከባድ መሣሪያዎች ጋር " ከዓዲግራት በስተደቡብ እያመሩ መሆናቸውን ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ሮይተስ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች በከተማዋ በኩል በሁለት የጭነት መኪኖች የተጫኑ በርካታ የኤርትራ ወታደሮችን ረቡዕ ጠዋት ማየታቸውን ገልጸዋል።
ለሮይተርስ ቀላቸውን የሰጡ የታጠቁ ግጭቶች ቦታና ክስተቶች መረጃ ፕሮጀክት (ACLED) የምስራቅ አፍሪካ ባለሙያ የኤርትራ ኃይሎች በዛላምበሳ በኩል ድንበር አልፈው ዓዲግራት መድረሳቸውን ገልጸዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የኢትዮጵያ ጦር እነዚህ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በጉዋዳ አካባቢ በድሮን መምታቱን ተናግረዋል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት የማነ ገብረመስቀል ፤ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ተገኝረዋል መባሉን ውድቅ አድርገዋል።
በከዚህ ቀደሙ ጦርነት ወቅትም ኤርትራ ሰራዊቷ በኢትዮጵያ እንደሌለ፣ ጦሯ የሚወነጀልባቸውን ግፎች እንዳልፈጸመ በተደጋጋሚ ስትክድ እነደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ። የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ምድር፣ ትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መግባቱን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ፥ ወታደሮቹ ወደ መቐለ መስመር / አቅጣጫ ሲያመሩ እንደተመለከቱ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች " በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች…

12 hours ago
#ችሎት
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና መብት እንዲከበር ብያኔ ሰጠ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ በዳኞች ፈረቃ መቀያየርና መዝገብ ባለመቅረቡ ምክንያት በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት መቆየቱ ይታወሳል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም፤ እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመመርመር የፌደራል ፖሊስ ያደራጀውን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ሲመለከት ቆይቷል።
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት፣ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቷል።
በዚህም መሠረት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ይስሓቅ ወልዳይ፣ አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ብያኔ መሰጠቱን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ፖሊስ የፎረንሲክ ውጤቶችን ለመጠበቅና ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት በሚል የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው በ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን እስከዛሬ መስከረም 27/2019 ዓም ድረስ በእስር ላይ ሆነው ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳያገኝ ለአርብ ተቀጠረ። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም? እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚሉትን ነጥቦች ለመመልከት የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል። ይሁን…

14 hours ago
Escape to Nacala, Mozambique on our inaugural flight and enjoy the coastal paradise with our exclusive 4 Nights/5 Days package. Make unforgettable memories in one of Mozambique’s hidden gems. https://www.ethiopianholid... #flyethiopian
Sponsored by
Surafel
16 hours ago
Build a Trustworthy Digital Ethiopia!
Join our Digital Saturdays session : Cyber Month on Data Protection, Design Ethics, and Cybersecurity. Connect with policymakers, tech professionals, entrepreneurs, and the wider digital community as we explore the future of secure and ethical technology
📅 Oct. 17, 2026 | 8:30 AM
📍 The Urban Center, Addis Ababa
🔗 Register Now: https://bit.ly/3W9ZnJO
🤝 Hosted by The Urban Center & Ethio telecom
👉 Level up your digital safety! Reserve your spot now!
#ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia #cybersecurity #dataprotection #digitaltrust #digitalsaturday

18 hours ago
Enjoy enhanced connectivity to/from Entebbe as we introduce five additional weekly flights and increase our frequency to 35. Book your flight now and start getting ready for your journey.
https://www.ethiopianairli...
#flyethiopian #entebbe
https://www.ethiopianairli...
#flyethiopian #entebbe
19 hours ago
#ebola⚠️
በጎረቤት ሃገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መሞቱ ሲረጋገጥ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳውቋል።
• የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ " በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች በሙሉ የቀጠሉ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ (ቡንዲቡግዮ) ቫይረስ በሰው ላይ መገኘቱና የታካሚው ሕይወት ማለፉ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ ላለፉት ሰባት ዓመታት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ዲ.አር.ሲ) ይኖር የነበረ የኬንያ ዜጋ ነው።
ግለሰቡ ከዲ.አር.ሲ በየብስ ጉዞ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ካመራ በኋላ፣ ኦክቶበር 3 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) በአውሮፕላን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ ተገልጿል።
በሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም፣ በብሔራዊ የቫይሮሎጂ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ (NVRL) እና በኬኤምአርአይ (KEMRI) በተደረገ ምርመራ በቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ (Bundibugyo Ebola Virus) መያዙ ተረጋግጦ ሕይወቱ አልፏል።
ኬንያ ከሟቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን የቤተሰብ አባላት፣ የጤና ባለሙያዎችና አብረውት የተጓዙ መንገደኞችን የመለየትና በለይቶ ማቆያ የማስገባት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ኬንያ ላይ በሽታው መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን እንደሚመስል የጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሰጡን ምላሽ በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ ሁሌም የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች አሉ እነዛን በሙሉ እየተሰሩ የቀጠሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዶ/ር መቅደስ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ማንቂያ ደወል ሲያሰማና ሀገራት በሽታው መግባቱን ይፋ ሲያደርጉ፣ ከእነዚያ ሀገራት በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻና የክትትል ስራዎች ወዲያውኑ እንደሚተገበሩ አመልክተዋል።
"እኛ ሁልጊዜ ዝግጅት ላይ ነን፤ ስክሪን እንሰራለን፣ በአየርም በየብስም ያለው ይሰራል" ያሉት ሚኒስትሯ "ዘ ሞመንት ደብሊው ኤች ኦ (WHO) አክቲቬት ሲያደርግና አገሮች ዲክሌር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ ከዛም አገር የሚመጡት ላይ ተመሳሳይ ነገሮችን ኢንፎርስ ይደረጋል፤ የተለመዱ ስራዎች ስላሉን እነዛን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል" ብለዋል።
ቫይረሱ ከዚህ ቀደም በዲ.አር.ሲ እና በዩጋንዳ በታየበት ወቅት ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፣ አሁን በሽታው ወደ ኬንያ መግባቱ ሲረጋገጥም የዝግጅት ደረጃው ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።
"ገና ዲአርሲ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ዩጋንዳም ሲመጣ፣ አሁን ደግሞ እዚህኛውም(ኬንያ) ሲመጣ ደረጃው እያሻሻለ እየጨመረ የሚሰሩ ስራዎች ጀምረናል። ከባለድርሻ አካላት ጋር፣ የድንበር አካባቢ (ክሮስ ቦርደር) ከሚሰሩት ጋር በመረጃ መነባበብ፣ ቅድመ ዝግጅት፣ ቅኝትና ምላሽ እነዚህን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል፤ በዛ መልክ ላይ ነው ያለነው" ሲሉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ አቋምና ዝግጁነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ።
የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ምድር፣ ትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መግባቱን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ፥ ወታደሮቹ ወደ መቐለ መስመር / አቅጣጫ ሲያመሩ እንደተመለከቱ ገልጸዋል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች " በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ " እየተጓዙ መሆናቸውን በዓዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው ዓዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል።
ወታደሮቹ ከዓዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ መስመር በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የዜና ወኪሉ የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በተመሳሳይ አልአረቢያ የዜና ወኪል የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ደግሞ ከዛላኣንበሳ እስከ የጉሎመኸዳ ወረዳ ዋና መቀመጫ የሆነችው የፋፂ ከተማ የሻዕብያ ወታደሮች ማየታቸውን አመልክተዋል።
ነዋሪዎቹ በፋፂ ከተማ በሚገኘው የመንግስት ኮሌጅ ማረፍያ እንዳላቸው፤ ከፋፂ ወደ ዓዲግራት በሚወስደው ፊያ ቐሺ የተባለ ከፍታ ያለው (በባለፈው የትግራዩ ጦርነት ጊዜ ምሽግ ሰርተው ከትግራይ ኃይል ጋር ሲዋጉበት ነበር) ኮረብታ ምሽግ መስራታቸው ፤ ከዛላኣንበሳ እስከ ምሽግ የሰሩበት ቦታ በፓትሮል ቅኝት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ከቀናት በፊት የፌዴራል መንግሥት ባለስልጣን የሆኑት አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በቅርብ ዳግም ባገረሸው ጦርነት የሻዕቢያ ጦር እንደተሳተፈ አሳውቀው ነበር።
የአፋር ክልላዊ መንግሥትም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶ በነበረው ቃል በጦርነት የተሳተፉ የሻዕቢያ ጦር አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።
በሌል በኩል ፥ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል ከመቐለ በስተሰሜን የምትገኘውን አጉላዕ የተባለች አነስተኛ ከተማ መቆጣጠራቸውን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
ዛሬ ረቡዕ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ማለዳ ላይ በከተማዋ ዙሪያ ከፍተኛ ውጊያ እንደነበረ የገለጹት ነዋሪዎች የትግራይ ኃይል (ህወሓት ኃይል) ከተማዋን ለቅቆ ወደ ዉቅሮ አቅጣጫ ማምራቱን ገልጸዋል።
ባለፈው መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም የመቐለ ከተማን የተቆጣጠሩት የመንግስት ኃይሎች ከመቐለ በስተደቡብ ምዕራብ በተንቤን መስመር በምትገኘው ሀገረ ሰላም የተባለች አነስተኛ ከተማ መድረሳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ፎቶ ፦ ፋይል
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው " - አብርሃም በላይ (ዶ/ር) 👉 " ... ሻዕቢያ ሰሞኑን በጦርነት በአካል ተሳትፏል ፤ መልሱ እጥፍ ሆኖ እንደሚመለስ ምንም ጥያቄ የለውም ! " ዳግም ጦርነት ካገረሸ በኋላ የፌዴራል መንግሥት ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየቱን ሰጠ። የፌዴራል መንግሥትን ወክለው አስተያየት የሰጡት አብርሃም በላይ (ዶ/ር)…

በአዲስ አበባ ከተማ የ2019 ዓ/ም የሁሉም እርከን የተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 30 ቀን እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳሰበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከቅድመ-አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲያካሂድ የቆየው የተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
ቢሮው ለነባር ሆነ ለአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በቂ ጊዜ መስጠቱን በመጥቀስ፣ ከጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም እርከን ምንም ዓይነት የተማሪዎች ምዝገባ እንደማይካሄድ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በጻፈው ሰርኩላር አሳስቧል።
ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://www.facebook.com/s...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከቅድመ-አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲያካሂድ የቆየው የተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
ቢሮው ለነባር ሆነ ለአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በቂ ጊዜ መስጠቱን በመጥቀስ፣ ከጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም እርከን ምንም ዓይነት የተማሪዎች ምዝገባ እንደማይካሄድ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በጻፈው ሰርኩላር አሳስቧል።
ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://www.facebook.com/s...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
19 hours ago
ሳዑዲ አረቢያ
Saudi Arabia
በማኅበራዊ ሚዲያ (ፌስቡክ) ላይ ነቢዩ መሐመድን የተሳደበው ወጣት ሞት ተፈረደበት።
አኖጃን ሲቫራሳ የተባለ የ24 ዓመት ስሪላንካዊ ስደተኛ ሠራተኛ፣ " በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሰጠው አስተያየት እስልምናን እና ነቢዩ መሐመድን ተሳድቧል " በሚል በሳዑዲ አረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል።
አኖጃን ለሞት ፍርዱ የዳረገው ክስ የተመሰረተበት፣ በስሪላንካ በተካሄደ የሂንዱዎች ሃይማኖታዊ ጉዞ ወቅት ከተከሰተ አንድ ክስተት በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ በተነሳ ክርክር ምክንያት ነው።
ይሄውም በሰኔ መጨረሻ አካባቢ አንድ ሙስሊም ወጣት ከሂንዱ አማኞች ጉዞ በኋላ አንድን ውሻ በእርግጫ ሲመታ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት መሰራጨቱ ነው። ይህም ከፍተኛ ሃይማኖታዊ ክርክር አስነስቷል።
በዚያ ክርክር ውስጥ አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ አንድን የሂንዱ አምላክ የሚያጣጥል እና የሚያዋርድ አስተያየት መጻፉን ተከትሎ አኖጃን በታሚል ቋንቋ በሰጠው ምላሽ ነቢዩ መሐመድን የሚዘልፍ ይዘት ያለው ጽሑፍ አስፍሯል።
አኖጃን አስተያየቱን ወዲያውኑ ሰርዞ ይቅርታ የሚጠይቅ ቪዲዮ ቢለቅም፣ የጽሑፉ ቅጂ ለቀጣሪው እና ለሳዑዲ ባለሥልጣናት በመድረሱ በሐምሌ ወር ታስሮ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል።
እናቱ ራሳማኒካም ዮጋላክሽሚ የበኩር ልጃቸውን ሕይወት ለማዳን በእምባ ፍርዱ ቀሪ እንዲደረግለት ተማጽነዋል።
ጉዳዩ በስሪላንካ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ሲሆን፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ አከናውነዋል ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግሥትም ምሕረት እንዲደረግለት ጥረት እያደረጉ ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ቅጣቱ መቼ እንደሚፈጸም በይፋ ባለመግለጿ እና ብዙ ጊዜ ለቤተሰቦች ወይም ለኤምባሲዎች ሳታሳውቅ የሞት ፍርድን ስለምትፈጽም ቤተሰቦች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።
ከአደንዛዥ ዕፅ እና ግድያ ወንጀሎች አንጻር በሃይማኖት ወንጀሎች የሚተላለፉ የሞት ቅጣቶች በሳዑዲ በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ቢሆኑም እስካሁን ለአኖጃን ይቅርታ ስለመደረጉ ከሳዑዲ በኩል የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።
ቢቢሲ

ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
8ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። የስልጠናው ይዘቶች:
👉 English Grammar
👉 Professional English Speaking & Pronunciation
👉 Business & Workplace Communication
👉 Professional Writing & Email Etiquette
👉 Listening & Comprehension Skills
👉 Public Speaking & Presentation Skills
👉 Interview Preparation & Confidence Building
👉 Conversational Fluency Practice
ስልጠናዎቹ በሶስት ደረጃ ተከፍለው መሰረታዊ (A1 and A2)፣ ማዕከላዊ (B1 and B2) እና በከፍተኛ ደረጃ (C1 and C2) ተብሎ የሚሰጥ ይሆናል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...

20 hours ago
🔄 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
@tikvahethiopia #hopr 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል። ለም/ቤቱ በቀረበው ማብራሪያ ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።…

23 hours ago
2ኛ ዙር የጥናታዊ ጽሑፍ አሰራር እና አቀራረብ (Research Methods and Analysis) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 Stata እና SPSS ሶፍትዌሮችን በመጠቀም Quantitative እና Qualitative ሪሰርቾችን መስራትን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰለጥኑበት
👉 ከፕሮፖዛል ቀረፃ ጀምሮ ሪሰርች አሰራር ቴክኒኮችን አካቶ እስከ ሪሰርች ሪፖርት አቀራረብ ያለውን አሰራር የሚሰለጥኑበት
👉 ልምድ ባላቸው የጥናታዊ ፅሑፍ ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Instagram: https://www.instagram.com/...

#hopr
7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል።
ለም/ቤቱ በቀረበው ማብራሪያ ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።
እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ፦
👉 ቀድሞ " የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " የነበረው በአዲሱ " የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር " በሚል
👉 ቀድሞ " የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ " የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር " በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ቀድሞ " የፕላንና ልማት ሚኒስቴር " የነበረው " የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር " በሚል ተቀይሯል።
ቀድሞ " የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር " የነበረው " የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር " በሚል ስያሜው ተቀይሯል።
በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም ነው ተብሏል።
አሁን ላይ በምክር ቤቱ ዝርዝር ማብራሪያ እየቀረበ ነው።

1 day ago
Sit back, relax, take in the view, and snap the moment. Share us your stunning Ethiopian window view photos using #windowviewwednesday for a chance to be featured on our page!
Picture by: SaraYirga #flyethiopian #etmoments
Picture by: SaraYirga #flyethiopian #etmoments
1 day ago
ስለ ወተት የተደረገው ጥናት ምንድነው የሚለው ?
የጥሬ ወተት ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ከእርባታ ሼድ እስከ ሽያጭ ባለው ሂደት አንዳንድ ለጤና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ፣ በከተማዋ 11 ክፍለ ከተሞች ስለወተት ጥራት ደህንነትና የግብይት ስርዓት ጥናት መደረጉን ነግረውናል።
በዚህም " ከእንስሳት እርባታ ሼዶች ጀምሮ እስከ ምርት መሸጫ ድረስ ባለው ሂደት ለጤና ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉ ጥናቱ ጠቁሞናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከውሃ ባሻገር ለጤና ጠንቅ የሆነ "ባዕድ ኬሚካል" ጥሬ ወተት ላይ እንደሚጨመር ስሞታ ይቀርባል፤ "ኬሚካል" እንደሚጨመር ጥናቱ አሳይቷል ? ብለን ስንጠይቃቸው፣ "በጥናት ያረጋገጥነው በዋናነት ከፍተኛ ውሃ የሚጨምሩ አንዳንድ ነጋዴዎችና አርቢዎች እንዳሉ ነው" ብለዋል።
በጥናቱ " ወተቱ ዋናውን ይዘቱን እንዲያጣ የሚያደርጉ ችግሮች እንዳሉ አይተናል። ከማህበረሰቡ በኩል ግን 'ባዕድ ኬሚካል' የሚጠቀሙ እንዳሉ ጥቆማዎች ይመጣሉ። ያንን በቀጣይ ጥናት መመለስ ያስፈልጋል " ሲሉም ተናግረዋል።
ጥናቱ " በተጨባጭ የወተት አያያዛችን ለጤና ስጋት የሚያስከትል ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ቁጥጥር መደረግ አለበት " በሚል ኮሚሽኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያጠናው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ለ " ካንሰር " የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር ወተት ላይ መገኘቱን ጥናቱ በተጨባጭ አሳይቷል ?
ም/ኮሚሽነሩ፣ " በተጨባጭ ጥናቱ ይሄን አመላክቷል ሳይሆን አሁን ላይ ያለው የወተት አያያዝ ስርዓታችን ከሚፈለገው ስታንዳርድ አንጻር ሙሉ አይደለም ፤ ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረግ አለበት " የሚል ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ በዋነኛነት በየሱቁ የሚገዛው ወተት " በሁለት፣ ሦስት ቀንም አይረጋም፤ ችግሩ ምንድን ነው ? " በማለት ህብረተሰቡ ቢሮ ድረስ እየሄደ ጥቆማ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
" በጭምጭምታ ደረጃ ወተቱ ላይ ኬሚካል እንደሚጨመርበት ነው የምንሰማው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ኬሚካሉ ደግሞ በጣም ከባድ ነው ወተቱን እንዳይረጋ ቢያደርግም በጊዜ ሂደት በጤና ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ሀኪሞች ያነሳሉ። በጊዜ ሂደት እነዚህ ነገሮች በከተማዋ በተጨባጭ ካሉ ካንሰር ሊያስከትል የሚችል ስጋት ሊያስከትል ይችላል " ብለዋል።
የተስተዋሉ ክፍተቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?
የወተት አያያዝን በተመለከተ በእንስሳት እርባታ ሸዶች የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ችግር ያለባቸው መሆኑንም ጥናቱ ማሳየቱን ገልጸዋል።
በእርባታ ቦታ ለላሞች የህክምና አሰጣጥ አንዲት ላም ህክምና ካገኘች ከስንት ጊዜ በኋላ ነው መታለብ ያለባት ? የሚለውን በሳይንሱ መሰረት አለመተግበር መስተዋሉን ገልጸዋል።
" የመድኃሃቱ ቅሪት እያለ አብሮ ወተቱን የማለብ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ፣ የግንዛቤ ክፍተትም አለ " ሲሉ ተናግረዋል።
በመታለብ ላይ ያለች ላም በበሽታ ብትጠቃ መድኃኒት እንደሚሰጣት፣ መድኃኒቱ በላሚቷ ሰውነት ውስጥ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር እንዳለ፣ የመድኃኒቱ ቅሪት የሚጠፋው ሀኪሞች በሚያስቀምጡት አግባብ በተለያዩ ጊዜ እንደሆነና የሀኪም ትዕዛዝ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
" የመድኃኒቱ ቅሪት ከላሚቷ አካል ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፋ ወተት ታልቦ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ግን የመድኃኒቱን ቅሪት ሰው እንዲመገበው እያደረግን ነው ማለት ነው " ብለው፣ ይህን በተመለከተ ዝርዝር ማዕቀፍ እየወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም፣ መኖ በተመለከተ በተለይ ከአቀማማጡ ጋር በተያያዘ "አፍላ ቶክሲን" የመፈጠር እድሉ ሰፊ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ረገድ ክፍተቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
" ከምንም በላይ የወተት ማለቢያ መሳሪያዎች ለምግብ ተስማሚ አለመሆናቸውን " የተናገሩት ፀጋ፣ በተለምዶ ወተት የሚገዛው በሃይላንድ፣ የሚጓጓዘውም ለማጽዳት አስቸጋሪ በሆኑ ጀርካዎች መሆኑን አንስተዋል።
በጊዜ ሂደት የፕላስቲኩ ፍቅፋቂ ከፀሐይ፣ ሙቀት ጋር ሲገናኝ የሚለቀቁ ነገሮች እንዳሉና ከፍተኛ የጤና ስጋት እንደሚያስትከሉ ሳይንሱ እንደሚያረጋግጥ ገልጸው፣ " እኛም በጥናታችን እነዚህ ነገሮች እየተተገበሩ እንደሆነ አይተናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
(ተጨማሪ ይኖረናል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም

" ሀሰተኛ ዜና ነው " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ ቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) እየተሰራጨ ያለው ዜና ሀሰተኛ ነው።
" ደሳለኝ (ዶ/ር) ጫኔ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ተደርገው በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል " እየተባለ የሚሰራጨው ዜና ሀሰተኛ መሆኑ ደሳለኝ (ዶ/ር) በፅሁፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ፎቶ ፦ በመቐለ " እንዳ ማርያም ጉግሳ " አካባቢ የሚገኘውና በቅርብ በዋይኤምሲኤ ድጋፍ ታድሶ ለአገልግሎት ተዘጋጅቶ ነበር የተባለ የህዝብ ቤተ መጻሕፍት በዘራፊዎች ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል።
ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተፈጸመው በዚህ አስነዋሪ የተባለ ድርጊት ለወጣቶችና ለአካባቢው ማህበረሰብ ዕውቀት ማግኛ ትልቅ ተስፋ ሆኖ የነበረው ተቋም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጿል።
ድርጊቱ ማኅበረሰቡን ያስቆጣ ነው።
በሌላ በኩል ፤ መቐለ አሁን ላይ ካለፉት ቀናት በተሻለ መረጋጋት ቢሰፍንባትም ለሊት ለሊት ቤት የተገባ የሚፈጸም ዝርፊያ እንዳለ ተጠቁሟል። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ ቀርቧል። ማህበረሰቡም አካባቢውን ሊጠብቅ ይገባል። #ፍጹምብርሃነ
@tikvahethiopia #tigray #mekelle የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል መቐለን ከተቆጣጠሩ በኋላ ስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ቤተሰቦችም እየተገናኙ ነው። የባንክ አገልግሎትም ተጀምሯል። በመቐለ ከተማ የፀጥታ ሁኔታው እና የሚፈጸመው ዝርፊያ ካለፉት ቀናት መሻሻል ቢያሳይም ሙሉ በሙሉ ሊቆም እንዳልቻለ ሁለት ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። " ትላንት ማንነታቸው…

2 days ago
#ads
Ⓜ️ 📱 ቀደም ብለው የከፈቱት LinkedIn Acccount ካለዎት ጥሩ ገንዘብ መስራት ይችላል (5000⭐በሳምንት )።
📱አካውንት ያላችሁ ብቻ በጥሩ ገንዘብ እየተከራየን ነው አውሩኝ ።
(LinkedIn rental service available)
😄accountes above 1 year
✅Rate 👇
🧡100+=1800birr0 p.week
🧡200+=2000 birr p.week
🧡300+=2500 birr p.week
🧡500+=2800 birr p.week
✅1000+=3000 birr p.week
✅1500+=3500 birr p.week
✅2000+=4500 birr p.werk
😄Payment systems all💰
🧡cryptosystem (binance)
🧡CBE
🧡BOA
🧡TELL BIRR
🤑fast payment system available
በቴሌግራም 🔥 coalmon
https://t.me/p2pethiopia12
0982009298

#update
የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ወደ አገልግሎት ለመመለስ አማራጭ የመፍትሔ እርምጃዎች በትይዩ እየተከናወኑ መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
• የተበላሸውን ትራንስፎርመር በሌላ ለመተካት የሚያስችል ተለዋጭ ትራንስፎርመር ከአርባ ምንጭ የማጓጓዝ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ቀናት መቆጠሩንም ተገልጿል።
በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆመውን የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ወደ ሥራ ለመመለስ የሚያስችሉ ሁለት አማራጭ ሥራዎች በትይዩ (ፓራላል) እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
እንደ ተቋሙ መረጃ የተበላሸውን ትራንስፎርመር በሌላ ለመተካት የሚያስችል ተለዋጭ ትራንስፎርመር ከአርባ ምንጭ የማጓጓዝ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ቀናት ተቆጥረዋል።
ተለዋጭ ትራንስፎርመሩ ተፈቶ በሎውቤድና በሦስት አይሱዙ ተሽከርካሪዎች የተጫነ ሲሆን፣ ሎውቤዱ በቀን በአማካይ ከ50 እስከ 70 ኪሎ ሜትር በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተጓዘ ይገኛል ተብሏል።
የማጓጓዝ ሥራው በሰላም እንዲጠናቀቅና በትራንስፎርመሩ ጉዞ ወቅት የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ድልድዮች እንቅፋት እንዳይፈጥሩ የቅየሳ ባለሙያዎች አስቀድመው ከፊት በመንቀሳቀስ መንገዶችን ምቹ የማድረግ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸው ተመላክቷል።
በሌላ በኩል፣ የተበላሸውን ነባር ትራንስፎርመር በአዲስ አበባ ገላን ወርክሾፕ ማዕከል የመጠገን ሥራ በትይዩ እየተከናወነ ይገኛል ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን "የጥገናው ሥራ ወይም ከአርባ ምንጭ እየተጓጓዘ ያለው ተለዋጭ ትራንስፎርመር ከሁለቱ ቀድሞ የደረሰውና የተጠናቀቀው አማራጭ አስቸኳይ ኃይል ለመስጠት ተግባራዊ ይደረጋል" ብለውናል።
ከአርባ ምንጭ የሚጓጓዘው ተለዋጭ ትራንስፎርመር በተወሰኑ የቴክኒክ ስፔሲፊኬሽን ልዩነቶች ምክንያት መጠነኛ የሲቪል ሥራዎችን ሊጠይቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሥራው ሙሉ በሙሉ የሚጠናቀቅበትን ትክክለኛ ቀን ወስኖ ማስቀመጥ አስቸጋሪ የሚያደርገው የቴክኒክ ሥራው ውስብስብነት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በጉዞው ወቅት የሚያጋጥሙ ሁኔታዎችና የቴክኒክ ሂደቶች የሚወስዱት ጊዜ ሊለያይ እንደሚችል አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ በመጓጓዝ ላይ ያለው ተለዋጭ ትራንስፎርመር በቦታው ደርሶ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ያጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ሲፈታ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የሚመለስ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ እስከዚያው ድረስ ደንበኞች በትዕግሥት እንዲጠብቁ ጠይቋል።
በአዲስ አበባ ከላይ በምስሉ የተያየዙ በርካታ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ላለፉት 15 ቀናት በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ችግር እንደሆነባቸው ይገኛል።

" ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ጠንካራ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን " - ጌዲዮን ሳር
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጌድዮን ሳር ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጹ።
ሚኒስትሩ ፤ የኢትዮጵያን አንድነትና ጸጥታ አስጠብቆ ማቆየት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው ሰላም ያለው ወሳኝ ሚና ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎት እንዳላቸውና ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት ከፍተኛ ዋጋ የምትሰጥ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት፣ የሁለቱን አገራት ሁለገብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን በውይይቱ እንዳረጋገጠች አሳውቀዋል።
ይህ ውይይት የተደረገው የእስራኤል ጎረቤት ግብፅ የቀጠናው ሀገራት የሆኑትን የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን መሪዎች ሀገሯ ላይ ሰብስባ ስለ ቀይ ባህር፣ ስለ አባይ ወንዝ ፣ እስራኤል የሀገርነት እውቅና ስለሰጠቻት ሶማሌላንድ ስለሚሰጣት እውቅናና ድጋፍ ማውገዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክራ " የጋራ " ያለችውን መግለጫ ካወጣች ከ2 ቀን በኋላ ነው።
እስራኤል፣ ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በይፋ ወጥተው ከደገፉ እና ከኢትዮጵያ ጎን ነን ካሉ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #egypt በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ በግብፅ ኒው ኤል-አለሚን ከተማ የግብፅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጎረቤታች የሆኑት የሱዳን ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የመሪዎች ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ስብሰባው ላይ የነበሩት ፦ - የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ - የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (በግብፅ አውሮፕላን ተልኮላቸው ወደ ግብፅ የሄዱ) - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ…

በፌስቡክ ገጻቸው የሲዳማ ክልልን ህዝብ በተለይ ወጣቶችን ይቅርታ ጠየቁ የተባሉት የቀድሞ አፈጉባኤ " ፌስቡክ ገጼ ተጠልፎ ነው " አሉ።
በሰሞኑን የሲዳማ ክልል መንግሥት ምስረታ ሂደት ከክልል ፕሬዝዳንት አንስቶ ከፍተኛ የአመራር ለውጦች የተደረጉ ሲሆን፣ በዚህም ሂደት የክልሉ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሌላ ሰው ተተክተዋል።
ይህ ከሆነ በኋላ በወ/ሮ ፋንታዬ የፌስቡክ ገጽ ላይ "ይቅርታ" በሚል ርዕስ በስልጣን ዘመናቸው ለሰሯቸው ስህተቶችና በእሳቸው ዝምታ ለተፈጠሩ ልዩ ልዩ ጥፋቶች የሲዳማን ሕዝብ በተለይም ወጣቶችን ይቅርታ መጠየቃቸውን የሚገልጽ ፅሁፍ ወጥቷል።
በርካቶችም ይህንኑ መረጃ በማጋራት የሳቸው ተከታዮችና የስራ ባልደረቦቻቸው ጭምር አስተያየት ሲሰጧቸው የነበረ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀድሞ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በስልክ አግኝቶ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቋቸዋል።
ወ/ሮ ፋንታዬ " አካውንቱ አሁን ላይ የኔ አይደለም፣ ተጠልፎብኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" እኔ በአመራር ለውጡ ቅሬታ የለብኝም " ያሉት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ " አካውንቱ ከዚህ ቀደም የኔ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ተጠልፎብኛል " ሲሉ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ከሲዳማ ክልል የአመራሮች ለውጥ ጋር በተያያዘ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ፥ " በቀድሞ የክልሉ አመራሮች ጊዜ ከላይ እስከ ታች ለጠፉ ጥፋቶች ፣ በልማት ወደኋላ መቅረት ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ በክልሉ ተንሰራፋ ሙስና እና በዛ ለመጣው ጥፋት ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባ ነበር " ሲሉ እየገለጹ ናቸው።
በተለይ ደግሞ ከወጣቶች የስራ አጥነት ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ የሚነሳው ቅሬታ የበዛ ነው።
አሁን ላይ ክልሉን አዲስ አመራሮች ተረክበው እየመሩት ይገኛሉ። ረጅም ጊዜ የአመራርነት ልምድ ያላቸውና በፌዴራል መ/ቤት የነበሩት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው ወደ ስራ ገብተዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ወደ ፌዴራል ሄደው የፌዴራሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia አቶ ደስታ ሌዳሞን በመተካት የሲዳማ ክልልን በፕሬዚደንትነት እንዲመሩ የተሾሙት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ማናቸው ? በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ከዚህ ቀደም የሲዳማ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። በትምህርት ዝግጅታቸው፦ - የመጀመሪያ ዲግሪ በሕዝብ ጤና ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ…

64ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የድርጅቶች ሒሳብ አያያዝ ስርዓት ሁሉም ዓይነት የቢዝነስ ተቋማትን መሰረት በማድረግ በፒስችሪ ተደግፎ የሚሰጥ
👉 VAT፣ Excise Tax፣ የትርፍ ግብር፣ ዓመታዊ ግብር አሰራር እና ሪፖርት አቀራረብ እንዲሁም ሌሎችም የግብር ዓይነቶችን በተግባር እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉 የፋይናንስ ስርዓት በቢዝነስ ተቋማት እንዴት ማዘመን እንደሚቻል በተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
64ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የድርጅቶች ሒሳብ አያያዝ ስርዓት ሁሉም ዓይነት የቢዝነስ ተቋማትን መሰረት በማድረግ በፒስችሪ ተደግፎ የሚሰጥ
👉 VAT፣ Excise Tax፣ የትርፍ ግብር፣ ዓመታዊ ግብር አሰራር እና ሪፖርት አቀራረብ እንዲሁም ሌሎችም የግብር ዓይነቶችን በተግባር እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉 የፋይናንስ ስርዓት በቢዝነስ ተቋማት እንዴት ማዘመን እንደሚቻል በተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
2 days ago
Enjoy 15% off flights between Moroni and our destinations worldwide.
Book now and take advantage of this offer!
https://www.ethiopianairli...
#ethiopianairlines #traveldeals

Comments