1 month ago
የቅዱስ ላሊበላ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ጉዞ
ክፍል ፪
#ethiopia | በባለፈው ክፍላችን — ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ከአንድ አለት የተፈለፈሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መገኛ ብቻ ሳይሆን፣ ወንጌልን በምድር ላይ አውርዶ የተረጎመ ታላቅ የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት የትርጓሜ ማዕከል እንደነበረ ተመልክተናል።
በወቅቱ የነበረው 120 ሊቃውንት የተሰበሰቡበት ታላቅ ጉባኤ፣ የሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን የውጭ ሀገር ተማሪዎችንና የግብፅ ጳጳሳትን ሳይቀር በምስጢርና በትምህርት ይደግፍ እንደነበር፣ ቅዱስ ላሊበላም አብያተ ክርስቲያናቱን ከመስራቱ አስቀድሞ ለአራት ዓመታት በጉባኤው ውስጥ የአዲስ ኪዳን ምስጢራትን ያስረዳ እንደነበር መዳሰሳችን ይታወሳል።
በአሁኑ ክፍላችን ደግሞ — ይህ የቅዱስ ላሊበላ የአዲስ ኪዳን ትርጓሜና ምጥቀት በመሬት ላይ እንዴት ይገለጥ እንደነበር፣ የደብረ ሮሃ መልከአ-ምድርና የስም አሰያየም ከነገረ ድኅነት ጋር ያለውን ጥልቅ ትስስር፣ እንዲሁም በወቅቱ ከነበረው የግብፅ ጳጳስ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የታሪክ አጋጣሚና የትርጓሜ ትምህርት ቤቱን ታሪካዊ ጉዞ አያይዘን እንመለከታለን።
በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የወንጌል ትርጓሜና የነገረ ድኅነት ምስጢር በቀጥታ ከሕንፃዎቹ አሰራርና ከሁለንተናዊው አደረጃጀት ጋር ተያይዞ የቀረበበት መንገድ እጅግ ድንቅና ጥልቅ ነው። ምንም እንኳ በጊዜው የካህናት ቁርባን፣ ጥምቀትና አዲስ ኪዳናዊ ሥርዓታት ሙሉ በሙሉ ይከናወኑ የነበረ ቢሆንም፣ የብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ትውፊት ፈጽሞ አልተተወም ነበረ።
የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ቤት መምህር ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ እንደሚገልጹት፤ ቅዱስ ላሊበላ ደብረ ሮሃ ላይ ሲደርስ ግን አዲስ ኪዳን በገዛ እግሩ በትክክል እንዲቆም አድርጎታል። በቦታው ላይ በብዛትና በልዩ ልዩ ዓይነቶች የሚታዩት የመስቀል ቅርጻ ቅርጾች ደብረ ሮሃ የአዲስ ኪዳን ትምህርትና ምስጢር ዋና ማዕከል ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ናቸው።
የደብረ ሮሃን መልከአ ምድርና የስም አሰየየም ስንመለከትም፣ ቅዱስ ላሊበላ ከዘመነ ዳዊትና ከደብረ ጽዮን የሚጀመረውን የብሉይ ኪዳን ታሪክ በማስታወስ ይጀምራል። በመቀጠልም ወደ አዲስ ኪዳን ታሪክ በመሸጋገር ቢታንያን፣ ደብረ ዘይትን፣ ዮርዳኖስን፣ ደብረ ሲናን፣ ጎልጎታንና ቀራንዮን በደብረ ሮሃ ምድር ላይ በጎላ ሁኔታ አዘጋጅቷል። ይህ የሚያሳየው ቅዱስ ላሊበላ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጻኢው ዘመን ድረስ ያለውን የእግዚአብሔርን የድኅነት ጉዞ፣ ኢትዮጵያውያን ልጆቹ መርምረውና ተጋድለው የደረሱበትን ምጥቀት ሙሉ በሙሉ በምድር ላይ ለማስፈር መጣሩን ነው።
"ቅዱስ ላሊበላ የስነ-ፍጥረት ምስጢርን፣ የመዓዛረ ፀሐይንና የብዕዛረ ፀሐይን መመላለሻ፣ የከዋክብትንና የብርሃኑን እንዲሁም የሙቀቱን መስፈሪያ ጭምር እያጠናን የምንመራመርበትን ጥበብ አስቀምጦልን ነው የሄደው። እስከ ዛሬ ድረስ ትርጓሜያቸውን እንኳን ሳንደርስባቸው፣ እያየናቸው ሳይሰወሩ የተሰወሩብን ብዙ ምስጢራት አሉ፤ በተለይም በአዲስ ኪዳን ላይ የነበረው መረዳት እጅግ ልዩ ነበረ" ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል ያስረዳሉ።
በዚያ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችና መጻሕፍት በቀጥታ ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ቋንቋ መተርጎም የጀመሩበት ጊዜ ነበረ። አሁን በቅዱስ ላሊበላ ወንጌል ላይ ገብተን ብናይ በሦስትና በአራት ቋንቋዎች የተጻፉ ማብራሪያዎችና የትርጓሜ አጻጻፎች ይገኛሉ፤ ይህም ቦታው የትላንትናው የትርጓሜ ሊቃውንት ማዕከል እንደነበረ ህያው ምስክር ብለው ይሞግቷሉ።
ንጉሡ የሰራቸው ሕንፃዎች፣ እዚያ ላይ የተሳሉና የተጻፉ ሐረጎች፣ ከቤተ ማርያም ጀምሮ የተወቀሩት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የአዲስ ኪዳን ማዕከልነትን የሚያበስሩ ናቸው። እመቤታችን ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለች መሰላል መሆኗን የሚያስረዱት እነዚህ ሕንፃዎች፣ በነገረ ድኅነትና በአዲስ ኪዳን ትምህርት ላይ የነበረውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያሉ።
ጉባኤ ቤቱ በተመሠረተበት በዚያ ዘመን፣ ከዛሬው ይልቅ እጅግ በርካታ ደቀ መዛሙርት የነበሩበትና ሙሉዋን ቤተ ክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ ይመራ የነበረ ታላቅ ትምህርት ቤት ነበረ። ቅዱስ ላሊበላ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ከመስራቱ አስቀድሞ፣ ለጉባኤው ሊቃውንት ለአራት ዓመታት ያህል ምስጢሩን ያስረዳ ነበር። ድንጋይና እንጨት ላይ እየሳለ ያቀርብ የነበረ ሲሆን፣ ለምሳሌ ቤተ ጊዮርጊስን ከማዋቀሩ አራት ዓመት አስቀድሞ በእንጨት ላይ ስሎ ለጉባኤው አቅርቦት ነበረ።
በወቅቱ የነበረው የታሪክ ክስተት እንደሚያስረዳው፤ በጊዜው የነበረው የግብፅ ጳጳስ ቅዱስ ላሊበላ ሕንፃዎቹን ከላይ ወደ ታች እየቆፈረ ሲሰራ ባየ ጊዜ ነገሩ ድንገት ስለሆነበትና የሥራውን ምስጢር ስላላወቀ ደንግጦ ነበር። ጳጳሱ ሥራውን እንደ ምሽግና ለጦርነት እንደሚያገለግል መደበቂያ አድርጎ በመመልከቱ ወርቅ መሰብሰብ ጀመረ። ሆኖም ያገለግለው የነበረው አገልጋይ ፍቅረ ንዋይ አድሮበት ከወርቁ በመስረቁ፣ ጳጳሱ አገልጋዩን እስከ መግደል ደረሰ።
ቅዱስ ላሊበላ ግን ለጳጳስና ለሃይማኖታዊ ማዕረጉ በነበረው ታላቅ ክብር ምክንያት ድርጊቱን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ አላሳጣውም። ይልቁንም ለኢትዮጵያ ሊቃውንት ደብዳቤ በመጻፍ፣ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊና ጥበብ የተቀላቀለበት ሥራ የሚመጥን፣ በትምህርቱና በአቀራረቡ የተለየ ሊቅ መርጠው እንዲልኩለት በማድረግ ከጳጳሱ ጎን እንዲሆን አድርጓል።
ኋላ ላይ ጳጳሱ ቅዱስ ላሊበላን ሲከሰስ ከተናገራቸው ምክንያቶች አንዱ "እኔ ሳላውቅ ቤተ ክርስቲያን ይሠራል" የሚል ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ "ሥራው ከተጀመረ አራት ዓመት ሆኖታል" የሚል ነበረ። ሆኖም በመሬት ላይ ሕንፃው መቆፈር ከተጀመረ ገና የመጀመሪያ ዓመቱ የነበረ ሲሆን፣ አራት ዓመት የተባለው ንጉሡ ከሊቃውንቱ ጋር በጉባኤ ቤት ምስጢሩን ሲወያይበትና ሲያስተምርበት የነበረው ጊዜ ነበረ። ይህ የሚያሳየው በወቅቱ የነበረው የትርጓሜ ጉባኤ ቤት ምን ያህል አርቆ አስተዋይ፣ ተሰሚነት ያለውና የቤተ ክርስቲያኒቱን አደራ በአግባቡ መወጣት የሚችል እንደነበረ ነው።
ሆኖም ግን በሂደት መንግሥታዊውና ሃይማኖታዊው መዋቅር መዳከም ሲጀምር፣ የታሪኩና የትርጓሜው ምስጢር አብሮ እየጠፋና እየተሸፈነ እንዲሄድ ሆኗል።
በቀጣዩ ክፍል (ክፍል ፫)፦
የደብረ ሮሃ ታሪክና የትርጓሜ ትምህርት ቤት በሂደት እንዴት ሊጠፋ ቻለ?
የጸሐፊያንና የታሪክ አጠናቃሪዎች ክፍተት ምን ነበረ?
ከብዙ ዘመናት መቋረጥ በኋላ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጥረት ትምህርት ቤቱ እንደገና እንዴት ሊያንሰራራ ቻለ?
የሚሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዘን እንቀርባለን።
ይቀጥላል......
የጉባኤ ቤቱ ሚዲያ ቤዛ ኩሉ ተከታተሉ
በቴሌግራም
https://t.me/lalibelagubab...
በዮቲዮብ
https://youtube.com/channe...
በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@.b...
ጌትነት ተመስገን
ላስታ - ደብረ ሮሃ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #lalibela #debreroha #ethiopianorthodox #orthodoxtewahedo #africanhistory #lalibelachurches #orthodoxhistory #christianhistory

2 months ago
* የቅዱስ ላሊበላን ታሪካዊ እሴትና ገጽታ አጉድፊያለሁ፤ ይቅርታዬን ተቀበሉኝ"
~ ቲክታከር "ጽጌ ሮያል"፤ ጽጌረዳ በቀለ
* ስፍራው የይቅርታና የቃል ኪዳን ምድር ነው፤ ይቅርታዋን ተቀብለናል!
~ የሃይማኖት አባቶቾ
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የቅዱስ ላሊበላን ገጽታና ታሪካዊ እሴት በሚያሳንስ መልኩ የተሰራጨው ትርክት ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሶ የነበረ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመችው በቲክቶክ "ጽጌ ሮያል" በመባል የምትታወቀው ጽጌረዳ በቀለ ወደ ስፍራው በአካል በመጓዝ ይቅርታ ጠይቃለች።
ግለሰቧ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከመንግስት አካላትና ከአካባቢው ተወካዮች ጋር በመወያየት ያደረገችው ድርጊት ስህተት መሆኑን አምናለች።
ወጣት ጽጌረዳ በቀለ የፈጸመችው ድርጊት አሳዛኝና ከባድ ጥፋት መሆኑን በመቀበል፣ ከህዝብና ከእምነቱ ተከተዮች ባሻገር ከፈጣሪ ጋር መጣላቷን በመረዳት ንስሐ እንደምትገባ ተናግራለች።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንዲሁም የቅዱስ ላሊበላ ተወላጆችና ወዳጆች ይቅርታ እንዲያደርጉላት በትህትና ጠይቃለች።
የቦታው የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው ስፍራው የይቅርታና የቃል ኪዳን ምድር መሆኑን በመጥቀስ፣ ጥፋቷን አምና በመምጣቷ ይቅርታዋን የተቀበሏት ሲሆን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቅዱስ ላሊበላ ተወላጆችና ወዳጆችም ይቅርታዋን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የቅዱስ ላሊበላ ደብር ጽህፈት ቤት፣ የቅዱስ ላሊበላ ደብረ ሮሃ ሰንበት ትምህርት ቤት እና የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ በከተሞች አካባቢ በዘፈን እየለመኑ "ላሊበላ" በሚል ስም የሚጠሩ አካላት ከዛጉዌ ሥርዎ መንግስት፣ ከቅዱስ ላሊበላ ታሪክም ሆነ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት የባህልና የኑሮ ግንኙነት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ ላሊበላ ንግሥናን ከክህነት፣ ክህነትን ደግሞ ከቅድስና ጋር አስተባብሮ ሀገር የመራ፣ አለም ያደነቃቸውን 10 ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ያነጸና ታላቅ ታሪካዊ አሻራ ያሳረፈ አባት እንጂ ከልመና ተግባር ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ አሳስበዋል።
የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ተወላጆች ወደፊትም ቢሆን የቅዱስ ላሊበላን ትክክለኛ ታሪክ በትምህርት ካሪኩለምና በብዙኃን መገናኛዎች በትክክለኛው ይዘቱ የማስተዋወቅና የመሞገት ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ስለ ቅዱስ ላሊበላ ለማወቅ በአካል ቦታው ድረስ በመገኘት አባቶችን መጠየቅ እንደሚገባ የጠቆሙት አካላቱ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የታሪክ ጥላሸት የሚቀቡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና መሰል ድርጊቶች ከተደገሙ ቅርሱን ለማስጠበቅ በህግ ደረጃ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
የላሊበላ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ጽህፈት ቤት
#lalibela #lalibelahistory #ethiopianorthodox #ethiopianhistory #zagwedynasty #lalibelachurches #ethiopiaculturalheritage #protectethiopianhistory #faithandforgiveness #rockhewnchurches #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments