2 months ago
የጨረር ፍንዳታው የባህረ ሰላጤው ሀገራትን መቃብር ሊያደርግ ይችላል — ኢራን
የኔታ ሚዲያ
ከኢራን-እስራኤል ጦርነት ጀርባ የተደቀነው አዲሱ የኒውክሌር ስጋት
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እጅግ አደገኛ ወደሆነ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በቡሸህር የኒውክሌር ጣቢያ አቅራቢያ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ድርጊቱ በቀጠናው ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አስከፊ መዘዝ አስጠንቅቀዋል።
ሚኒስትር አራቅቺ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እስራኤልና አሜሪካ የቡሸህር የኒውክሌር ጣቢያን እስካሁን አራት ጊዜ መደብደባቸውን ገልጸዋል። ከኒውክሌር ጣቢያው የሚወጣ የጨረር ብክለት (Radioactive fallout) የሰዎች ህይወትን የሚጨርሰው በቴህራን ሳይሆን በባህረ ሰላጤው ሀገራት ዋና ከተሞች ላይ ነው ሲሉ አስደንጋጭ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢራን በዛሬው ዕለት በእስራኤል ላይ የሚሳይል ጥቃቶችን የሰነዘረች ሲሆን በቴል አቪቭ ምስራቃዊ ክፍል በምትገኘው ራማት ጋን ከተማ በመኖሪያ ህንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል።
የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት (IDF) ህዝቡ ወደ መከላከያ መጠለያዎች እንዲገባ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
በሌላ በኩል በሆርሙዝ ወሽመጥ የባህር ትራንዚት ደህንነትን ለማስጠበቅ እና አባል ሀገራት አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን የሚሰጠው የፀጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ ድምፅ ይሰጥበታል ተብሎ ቢጠበቅም ድምፅ አሰጣጡ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል።
ባህሬን ያቀረበችው ይህ የውሳኔ ሃሳብ በቀጠናው ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
ባህሬን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት የካቲት 28 ጀምሮ ከኢራን የተተኮሱ 453 ድሮኖችን እና 188 ሚሳይሎችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በበኩሏ ዛሬ ሚያዝያ 4 ብቻ 23 ባለስቲክ ሚሳይሎችን እና 56 ድሮኖችን ማክሸፏን ገልጻለች።
በኤምሬትስ እስካሁን በደረሱ ጥቃቶች 13 ሰዎች ሲሞቱ 217 ሰዎች ቆስለዋል።
በሌላ በኩል ኢራን የተከሰከሰውን የአሜሪካ ኤፍ-15 (F-15) ተዋጊ ጀት ሁለተኛውን አብራሪ በቁጥጥር ስር አውያለሁ ማለቷን የአካባቢው ገዥዎች አስተባብለዋል።
ይሁን እንጂ የኢራን ሚዲያዎች አብራሪውን በህይወት ለያዘ ዜጋ 66,100 ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ በማስታወቅ ላይ ይገኛሉ።
ለተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች ገጻችንን ይከታተሉ! #middleeastconflict #iran #israel #nuclearsafety #breakingnews #internationalaffairs