5 months ago
ከህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ጽሕፈት ቤት ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የተላከ ባለ ሁለት ገጽ ደብዳቤ
ሙሉ ደብዳቤው እንደሚከተለው ይነበባል
አፋጣኝ ሰብአዊ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ
ለክቡር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ጉዳዩ፦ በትግራይ ውስጥ በተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የረሃብ እልቂት እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መጣስ
ክቡራን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አስታራቂዎች፤
በትግራይ፣ ኢትዮጵያ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊና ሆን ተብሎ የተደረገ የረሃብ ማባባስ ሁኔታ በተመለከተ ይህንን ደብዳቤ በከፍተኛ አጣዳፊነት እንጽፋለን።
ከህዳር 2013 ዓ.ም (ኖቬምበር 2020) ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ከቀጠለው ሞት በኋላ፣ በታህሳስ 2018 (ዲሴምበር 2025) የሟቾች ቁጥር ከጦርነቱ ጊዜ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
በትግራይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማዕከላት — ህጻጽ፣ ሽሬ፣ ዓድዋ፣ ዓቢይ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ መቐለ እና ሌሎችም — በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የፕሪቶሪያውን ስምምነት አንቀጽ 4 በሚጥስ መልኩ ስልታዊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።
የሰዎች አካል ወደ አፅምነት ተቀይሯል፣ ቁስላቸው ላይ ዝንብ ይወርራል፤ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በ2015-2016 (2023-2024) በሳምንት አንዴ ከነበረበት አሁን በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ወደ መሆን ተሸጋግሯል።
ህፃናትና አዛውንቶች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ ነው።
የፌዴራል መንግስት ጥሰቶች፡-
* ሀሰተኛ መግለጫዎች፡- የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ እንጂ በተግባር ወደ ተፈናቃዮች የደረሰ ትርጉም ያለው ዕርዳታ የለም።
* ቀጥተኛ እንቅፋት መፍጠር፡- መንግስት ማህበረሰቡ የሚያደርገውን የርስ በርስ መረዳዳት ወንጀል አድርጎታል። በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ የሚያሰባስቡ የማህበረሰብ አንቀሳቃሾች ዛቻ እየደረሰባቸው ነው። የቲክቶከሮች በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ወደ መንግስት አካውንት እንዲያስገቡ የተገደዱ ሲሆን የሕዝብ መረዳጃ ሀብቶችም እየተወረሱ ነው።
ከዳያስፖራ የሚላክ የገንዘብ ድጋፍም ታግዷል።
* ያልተፈታው የስር መሰረት ችግር፡- ከ1 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች አሁንም በወረራ እና በ"ፅዳት" ስር ወደሚገኘው ምዕራብ ትግራይ መመለስ አልቻሉም።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ተመላሾችን በሚመለከት የገባው ቃል ሳይፈጸም ቀርቷል።
አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈለጉ ነጥቦች፡-
* አስቸኳይ ሰብአዊ ተደራሽነት፡- የመንግስትን እንቅፋት በመዝለል ምግብ፣ ውሃ እና የህክምና ቁሳቁሶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለሁሉም የተፈናቃይ ማዕከላት እንዲደርሱ መጠየቅ።
* ገለልተኛ ምርመራ፡- የታህሳስ 2018ቱን የችግር መባባስ፣ የአምስት ዓመቱን የሞት መጠን እና ስልታዊ የዕርዳታ ክልከላን የሚያጠና የሐቅ መፈለጊያ ልዑክ በአስቸኳይ መሰማራት። በ60 ቀናት ውስጥም ይፋዊ ሪፖርት ማቅረብ።
* የፕሪቶሪያ ስምምነትን ማስከበር፡- ኢትዮጵያ በአንቀጽ 4 ላይ ለፈጸመቻቸው ጥሰቶች ተጠያቂ ማድረግ። ተፈናቃዮች ወደ ምዕራብ ትግራይ የሚመለሱበትን ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ መጠየቅ።
* ገደቦችን ማንሳት፡- መንግስት በዜጎች እና በዳያስፖራ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረት ላይ የጣለውን ክልከላ እንዲያቆም ጫና ማድረግ። የተወረሱ የዕርዳታ ገንዘቦችን መመለስ።
* ይፋዊ ተጠያቂነት፡- ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ማውጣት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማድረግ፣ እንዲሁም ዕርዳታ በሚያግዱ ባለስልጣናት ላይ የታለመ ማዕቀብ መጣል ይገኙበታል።
ከአምስት ዓመታት እልቂት በኋላ፣ ታህሳስ 2025 (2018 ዓ.ም) የችግሩ ሁኔታ ከከረረ ቀውስ ወደ አስከፊ እልቂት የተሸጋገረበት ወቅት ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያየ ቃል የተገባላቸው ህዝቦች በከፍተኛ ቁጥር እያለቁ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተተገበረ ሊቆጠር አይችልምአሁን ዝምታን መምረጥ ተባባሪነት ነው።
የተፈናቃዮች መጠለያ ማዕከላት የጅምላ መቃብር ሳይሆኑ በፊት፣ የፕሪቶሪያ ተስፋ የትውልድ እፍረት ሳይሆን በፊት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለንጊዜ የሚለካው በየቀኑ በሚቆጠሩ አስከሬኖች ነው አሁኑኑ እርምጃ ይወሰድ።
በአክብሮት እና በአስቸኳይ የቀረበ፣
(ፊርማ)
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ፒ.ኤች.ዲ)
የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር
ለግልባጭ፡-
* ተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UN OCHA)
* ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC)
* ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF)
* ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch)
* አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International)

ማኅበሩ ለቀድሞው ባልደረባው አቶ ሆነልኝ ፈንታው ቤተሰቦች የ5ሺህ የስዊዝ ፍራንክ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽን ባገኘው ድጋፍ ፤ በሰሜን ጎንደር ከተፈጸመበት እገታ ጋር በተያያዘ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ ላለፈው የቀድሞ ባልደረባው ሆነልኝ ፈንታው ቤተሰቦች የ5ሺህ የስዊዝ ፍራንክ (924,000 ብር ገደማ) የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የገንዘብ ድጋፉ በዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን ሬድ ፈንድ(Red Fund) በተባለው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አማካይነት የተሰበሰበ ሲሆን፤ በማኀበሩ ምክትል ዋና ፀሀፊና ቺፍ ኦፍ ስታፍ አቶ ቴዎድሮስ አላምረው አማካይነት ለአቶ ሆነልኝ ቤተሰቦች የተደረገ ሲሆን፤አቶ ቴዎድሮስ ከፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ኬት ፎርብስ እና ከፕሬዘዳንቱ ጃጋን ቻፓጌይን የተላከ የማፅናኛ መልዕክት ለቤተሰቡ አድርሰዋል፡፡
በማኅበሩ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ፍቅረ ሰላም ጋረድ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለበርካቶች እያደረገ ከሚገኘው ሰብዓዊ ድጋፍ ጎን ለጎን ህይወታቸውን ካጡ የሰብዓዊ አገልግሎት ሰራተኞቹ ቤተሰቦች ጎን ለመቆም ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል፡፡ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ላላቸው መደጋገፍና አጋርነትም ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡
በማኅበሩ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል ዋለ እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የቦርድ አባላት፤ የሟች ቤተሰብን ለማጽናናት እና ድጋፋቸውን ለማሳየት በጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
የሟች አቶ ሆነልኝ ፈንታው ባለቤት ወ/ሮ እንዬ የማኅበሩና የፌዴሬሽኑ አመራሮች ላደረጉላቸው መጽናናትና የገንዘብ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡ይህ የገንዘብ ድጋፉ በነሐሴ 2017 ዓ.ም የማኅበሩ ፕሬዘዳንት አቶ አበራ ቶላ አሳዛኙ ክስተት እንደተከሰተ ቤተሰቡን በጎበኙበት ወቅት ያሳዩት ቁርጠኝነት ተግባራዊ ማሳያ ነው ፡፡
ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
ERCS Delivers 5,000 CHF Financial Support to the Family of Late Staff Member Honelign Fentaw
The Ethiopian Red Cross Society (ERCS), with support from the International Federation of Red Cross and Red Crescent Societies (IFRC), has provided 5,000 CHF (approximately 924,000 Birr) in financial assistance to the family of the late Honelign Fentaw, an ERCS staff member who tragically lost his life in late August following a hostage-related incident around North Gondar.
The financial support was mobilized through the IFRC Red Fund and officially handed over by Deputy Secretary General and Chief of Staff, Ato Tewodros Alamrew, who also delivered messages of condolence and solidarity from IFRC President Kate Forbes and IFRC Secretary General Jagan Chapagain.
During the visit, the Vice Chair of the Amhara Regional Branch Board, Dr. Fikreselam Gared, reaffirmed ERCS’s strong commitment to standing with the families of humanitarian workers who lose their lives while serving others. He expressed appreciation to the IFRC and ERCS for their continued support and solidarity.
The visit was attended by ERCS’s Amhara Regional Branch Head Ato Shambel Wale and Regional Branch Board members, who joined in expressing sympathy and support to the bereaved family.
The wife of the deceased, W/z Eneye, expressed her heartfelt gratitude to ERCS and the IFRC leadership for the condolence message and the financial support provided.
This assistance fulfills the commitment made earlier by ERCS President Abera Tola during his visit to the family shortly after the tragic incident in August 2025.
We Live for Humanity!
#ihl #emblem #fundamantalpriciples #ifrc #icrc #rcrc #weliveforhumanity #ercs #humanity #disasterresponse #ethiopia #ethiopianredcross

6 months ago
ቀይ መስቀል ኮሚቴ 2,900 የሚጠጉ የስራ ቦታዎችን ሊቀንስ መሆኑ ተነገረ።
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በለጋሾች አስተዋፅዖ መቀነስ ሳቢያ የ2026ን በጀት በ17 በመቶ በመቀነሱ በዓለም ዙሪያ የሰው ኃይል ቅነሳ አድርጓል።
ኮሚቴዉ በለጋሾች አስተዋፅዖ መቀነስ ምክንያት የ2026 በጀቱን በ17 በመቶ በመቀነስ ወደ 2,900 የሚጠጉ የሙሉ ጊዜ የሥራ ቦታዎችን በዓለም ዙሪያ እንደሚያስወግድ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት ከ18 ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት ኮሚቴው በከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ወቅት ይህን ከባድ ውሳኔ ለመውሰድ ተገድዷል።
ICRC ለ 2026 ዓመት የ1.8 ቢሊዮን የስዊስ ፍራንክ ($2.2 ቢሊዮን) በጀት አጽድቋል—ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ17 በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
ይህ ቅናሽ ድርጅቱ ከ18 ሺህ በላይ ከሆኑ ሰራተኞቹ ውስጥ ወደ 2,900 የሚጠጉ የሙሉ ጊዜ የሥራ ቦታዎችን እንዲቀንስ ያስገድደዋል።
የኮሚቴው ፕሬዝዳንት ሚሪያና ስፖልያሪች፥ "የጦርነት መባባስ፣ የእርዳታ ፈንድ ላይ የሚደረጉ ቅናሾች እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ ጥሰቶች ሥር የሰደደ መቻቻል አደገኛ በሆነ ሁኔታ እየተገጣጠሙ ነው" በማለት የችግሩን አስከፊነት ገልጸዋል።
seledadotio

10 months ago
እስራኤል በጋዛ አዲስ የከፈተችው ጥቃት «ሊታገሱት የማይችሉት» ነው ፤ (ዓለማቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር)
ቀይ መስቀል ዛሬ ባወጣው መግለጫ እስራኤል የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር እና ቀሪ የሃማስ ምሽጎችን ለማጥቃት በሚል የከፈተችው ጥቃት «ሊታገሱት የማይችሉት» ነው ብሏል።
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ዋና ቃል አቀባይ ክርስቲያን ካርዶን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንዳሉት «በጋዛ ያለው ግጭት መባባሱ የበለጠ ግድያ፣ መፈናቀል፣ የበለጠ ውድመት እና ድንጋጤ ማለት ነው።»
«ጋዛ አሁን ማንም ማምለጥ የማይችልበት የተዘጋ ቦታ ናት» ያሉት ቃል አቃባዩ « የጤና አገልግሎት፣ የምግብ እና ንጹሕ ውኃ ተደራሽነት በእጅጉ እየቀነሰ ነው» ብለዋል ። በተጨማሪም በሰርጡ የሰብአዊ ርዳታ ሰጭዎች ደኅንነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አመልክተዋል። ይህ ደግሞ «ሊታገሱት የማይችሉት» እንደሆነ ነው ካርዶን በመግለጫቸው አጽንዖት የሰጡት።
በቀይ መስቀል ሰብአዊ ተግባራት ላይ ንቁ ተስትፎ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ካርዶን በጎርጎርሳዊው ጥቅምት ሰባት ቀን 2023 በሃማስ ታጣቂዎች በተወሰዱ እና በተደረጉ የሽምግልና ጥረቶች በያንዳንዱ የታጋች እስረኛ ልውውጥ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ከተቀሰቀሰ ሁለት ዓመታት ሊደፍን ጥቂት ወራቶች በቀሩት የእስራኤል ሃማስ ጦርነት 62,122 ፍልስጥኤማዉያን ሲገደሉ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፤ በጋዛ ሰርጥ ላይ ደግሞ ብርቱ ውድመት መድረሱን የዜና አውታሩ ገልጿል።
በጦርነቱ ከእስራኤል ወገን አብዛኞቹ ሲቪል የሆኑ 1,219 ሰዎች ሲገደሉ 251 ታግተው ተወስደዋል። አሁንም ድረስ 49 ያህል እስራኤላዉያን በሃማስ እጅ እንደታገቱ ይገኛሉ ።
ጋዛ ውስጥ ባለው የመገናኛ ብዙሃን እገዳ እና በርካታ አካባቢዎችን መድረስ ባለመቻሉ በጋዛ የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲም ሆነ በእስራኤላውያን ወታደሮች የሚቀርቡ ዘገባዎች እና ዝርዝሮችን በተናጥል ማረጋገጥ አለመቻሉንም የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ጠቅሷል።
DW Amharic

Sponsored by
Surafel