14 days ago
"ያሆዴ" በዓል በደማቅ ባህላዊ ድምቀት ተከበረ
#ethiopia | የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀድይ ነፈራ በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ተከበረ።
በዓሉ የሀድያ ማህበረሰብ ባህልና እሴቶችን በማስቀጠል የመተሳሰብ፣ የሰላምና የአንድነት መንፈስን የሚያጎለብት በዓል መሆኑ ተገልጿል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ያሆዴ የመተሳሰብ፣ የሰላምና የአንድነት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ከረጅም ወራት የሥራ ጫናና ድካም በኋላ ዘመድ ወዳጅ የሚጠያየቅበት፣ ይቅርታ የሚደራረግበትና ማህበራዊ ትስስር የሚጠናከርበት ትልቅ በዓል መሆኑንም አስረድተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው መስከረም ወር ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች፣ በተለይም ለሀድያ ብሔር ተወላጆች፣ የመታደስና የአዲስ ተስፋ ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል።
የያሆዴ በዓልም ለሀገር ሰላም፣ ለህዝቦች መከባበርና መፈቃቀር እንዲሁም ለጋራ ልማት የሚመከርበት አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ለ11 ወራት ከትውልድ ቀያቸው ርቀው የቆዩ የማህበረሰቡ አባላት ወደ ቤተሰቦቻቸውና ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው በጋራ የሚያከብሩበት በመሆኑ፣ የማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ በሰላምና በአካባቢ ልማት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።
በዓሉ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መመስረት ጀምሮ በህብረትና በደማቅ ሁኔታ ሲከበር መቆየቱን የጠቆሙት ዶ/ር እንዳሻው፣ ወደፊትም ያሆዴን በይበልጥ በማስፋትና በማስዋብ ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እንዲሁም በሀገርና በክልሉ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ መልካም ምኞታቸውን ማስተላለፋቸውን ሀዲያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
#yahodefestival #hadiyaculture #hadiyapeople #hadiyanewyear #ethiopianculture #ethiopiantradition #culturalheritage #culturalfestival #peaceandunity #communityunity

Comments