3 months ago
አብረን እንሩጥ ለሀዋሳ ከፍታ
#ethiopia | ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከታዋቂው አትሌት ገዛኸኝ አበራ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ውድድሩ በመጪው ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
"አብረን እንሩጥ ለሀዋሳ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የሚሰናዳው ይህ ታላቅ ስፖርታዊ ኩነት ላይ ከ15 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ታዋቂ አትሌቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች የውድድሩ አካል ይሆናሉ።
አዘጋጆቹ በመግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት የዚህ ሩጫ ዋና ዓላማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማሳደግና ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን የሀዋሳን ከተማ የቱሪዝም ገፅታ ለመገንባትና የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ለማገዝ የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለቤትነት የተመሰረተውና ለስድስት አስርት ዓመታት የታመነ የሶስተኛ ወገን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከዚህ ቀደም ካከናወናቸው ተግባራት በተጨማሪ መሰል ውድድሮችን በሌሎች ከተሞችም ለማስቀጠል ማቀዱን በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
ውድድር ለሚያሸኑፉ ከፍተኛ የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን መላው የከተማዋ ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት ለሩጫው ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#hawassacityrun #commercialnominees #athleticsethiopia #runforhawassa #communityfitness #ethiopiansports #gezahigneabera

Comments