Logo
Getu Temesgen
ፔንታጎን በጦር ኃይሉ እውቅና ከተሰጣቸው ሃይማኖቶች ዝርዝር ውስጥ ከ180 በላዩን ቀነሰ
#ethiopia | ፔንታጎን በጦር ኃይሉ እውቅና ከተሰጣቸው ሃይማኖቶች ዝርዝር ውስጥ 180 እምነቶችን መቀነሱን ፎክስ ኒውስ ከውስጥ ማስታወሻ ተመለከትኩት ባለው ዘገባ ላይ ጠቅሷል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴት በወታደራዊ ተቋማት ውስጥ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች የጦር ሠራዊቱን አርበኝነት እና ዲሲፕሊን እየሸረሸሩ ነው የሚል አቋም በመያዛቸው ነው ተብሏል።

ቀደም ሲል ከ200 በላይ ለሚሆኑ ሃይማኖቶች እወቅቅና አግኝተው በሰራዊቱ አባላት ዘንድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ሲባል፣ አሁን ይህ ቁጥር ወደ 31 ብቻ ዝቅ ብሏል።

ውሳኔው ወታደራዊ ተቋሙን ከፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ አክራሪነት ለመከላከል አስፈላጊ እንደሆነ ቢገለጽም፥ በሌላ በኩል በሠራዊቱ ውስጥ የሚያገለግሉ አባላትን የሃይማኖት ነፃነት የሚገድብ እና ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ነው በሚል ቅሬታ ቀርቦበታል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #fox News #tikvahethmagazine

4 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.