ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) አዲሱን የልጆች መጽሐፍ ሊያስመርቅ ነው
#ethiopia | አዲስ አበባ፦ ኮሜዲያን፣ የህፃናት መጽሐፍት ደራሲ እና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ አስረስ በቀለ (ቼሪ) “ኮሚኩ ሙዝ” የተሰኘውን አዲስ የልጆች መጽሐፍ ለማስመረቅ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ይካሄዳል።
አስረስ በቀለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን፣ “ቼሪ” የተሰኘውን የልጆች ካራክተር በመፍጠር በህፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ደራሲው ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን የጻፈ ሲሆን፣ በ2022 እ.ኤ.አ በEthiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ ለህፃናት ሥነ-ጽሑፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና አግኝቷል።
አዘጋጆቹ ምርቃቱ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ገልጸው፣ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመገኘት የልጆችን የንባብ ባህል ለማበረታታት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
✍️ ጌጡ ተመስገን
#getu #getutemesgen #ጌጡ #ጌጡተመስገን #አስረስበቀለ #ቼሪ #ኮሚኩሙዝ #ethiopiareads #የልጆችመጽሐፍ #ንባብ

6 hours ago