21 days ago
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ 1,861 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ተመለሱ
#ethiopia | በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ 1,861 ኢትዮጵያውያን በ10 ዙር በተካሄደ የአየር በረራ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ዘገበ።
ከተመላሾቹ መካከል 1,313 ወንዶች፣ 485 ሴቶች እና 63 ሕፃናት ይገኙበታል። ከአጠቃላይ ተመላሾቹ ውስጥም 100 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መኖራቸው ተገልጿል።
ተመላሽ ዜጎቹ በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም፣ በመስከረም 5/2018 ዓ.ም. የተጀመረው ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የመመለስ ሂደት እስከዚህ ወቅት ከ101 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ማስመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ማመላከቱን ዘገባው ገልጿል።
#ethiopia #saudiarabia #ethiopianreturnees #migration #amn #ethiopianews

Comments