4 months ago
ኢትዮጵያውያን ከአሜሪካ እንዳይባረሩ ፍርድ ቤት ወሰነ
#ethiopia | የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲታገድ ያሳለፈው ውሳኔ በፍርድ ቤት መታገዱ ተሰምቷል፡፡
የትራምፕ አስተዳደር ከ5 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያንን ለማበራር የሚያስችለውን የጊዜያዊ ከላላ ፈቃድ (Temporary Protected Status-TPS) መሻሩ ይታወሳል፡፡ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የተደቀነውን የመባረር ስጋት የሚቀለብስ እግድ በአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት ተጥሏል፡፡
ለ5000 ኢትዮጵያውያን የተሰጠዉው ጊዜያዊ የከለላ ፈቃድ የተሰረዘበትን ውሳኔ፣ የሀገሪቱ ፌደራል ፍርድ ቤት ቦስተን ዲስትሪክት ዳኛ ውድቅ አድርገውታል፡፡ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከአሜሪካ ለቀው እንዲወጡ የተሰጣቸው የሦስት ወር ጊዜ ገደብ እየተገባደደ በመሆኑ አጣብቂኝ ውስጥ ለገቡት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አፎይታ የሚሰጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ውሳኔው የተቀበለበሰበት ክስ የቀረበው በሦስት ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካን ኮሚውኒቲስ ቱጌዘር (African Communities Together) በተባለ ተሟጋች ቡድን ነው ተብሏል።
የቦስተኑ ፍርድ ቤት ዳኛ ብሬይን መርፊይ ትናንት በሰጡት ውሳኔ የትራምፕ አስተዳደር ትዕዛዝ አስቀድሞ የታሰበና የተወሰነ እንጂ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አጥንቶና አገናዝቦ የተወሰነ አይደለም” ብለዋል።
በአሜሪካ በተፈጥሮ አደጋዎች፣ በጦርነትና በሌሎች ልዩ አደጋዎች ምክንያት ከየሀገራቸዉ የሸሹ ሰዎች በጊዜያዊነት የመኖርና የመስራት ፈቃድ ይሰጣቸዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ጨምሮ የጊዜያዊ ከለላ ፈቃድ ፈቃድ የተሰጣቸዉ የ13 ሀገራት ዜጎች በአሜሪካ እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመላክታሉ ሲል አንድ አፍታ ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #ethiopiannews #ኢትዮጵያ #ethiopianinus #diaspora #ustps #andaftamedia #አንድአፍታ

Comments