3 months ago
''ደቡብ አፍሪካ ሆይ ኢኮኖሚሽን ''ሽባ'' አደርገዋለሁ'' እስራኤል
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት አዲስ መልክ በመያዝ፣ እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ላይ እጅግ ከባድ የሆነ የኢኮኖሚ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። የቴል አቪቭ ባለስልጣናት የደቡብ አፍሪካን ኢኮኖሚ "ሙሉ በሙሉ ሽባ እናደርጋለን" ሲሉ መዛታቸው ተሰምቷል።
የቁጣው መንስኤ ምንድን ነው?
ለዚህ የከረረ ዛቻ ዋናው መንስኤ ደቡብ አፍሪካ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብና "ለማስታረቅ" ያሳየችው ፍላጎት ነው። ሆኖም እስራኤል ይህንን የሽምግልና ጥረት እንደ ቅንነት ሳይሆን፣ ለታሪካዊ ጠላቷ ለኢራን እንደ መወገን እና በእስራኤል ላይ እንደ መቆም ተመልክታዋለች።
"ጸረ-እስራኤል አቋም ዋጋ ያስከፍላል"
የእስራኤል መንግስት ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ደቡብ አፍሪካ የምትከተለው "ጸረ-እስራኤል" አቋም ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላት አስታውቀዋል። ቀደም ሲል በሄግ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (ICJ) እስራኤል ላይ በቀረበው ክስ ሳቢያ የሻከረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት፣ አሁን ደግሞ ወደ ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ጥቃት ሊሸጋገር መሆኑ ተንታኞችን አሳስቧል።
ያልታሰበ ጥይት
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ደቡብ አፍሪካ የሰላም መልእክተኛ ለመሆን ብትሞክርም "ያልታሰበ ጥይት" እየደረሳት ይገኛል።
እስራኤል የምትወስደው የኢኮኖሚ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል በዝርዝር ባይገለጽም፣ በንግድ እና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ የሚኖረው ተፅእኖ ግን ቀላል እንደማይሆን ይገመታል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህ የቃላት ጦርነት ወደ ተግባር ተለውጦ የደቡብ አፍሪካን ደካማ ኢኮኖሚ ይበልጥ እንዳያናጋው በስጋት እየተከታተለ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ehiofm #southafrica #israel #diplomacy #economicwar #globalnews #iran #middleeastconflict #ethiopia